አገር እንዲህ ኾናም አትቀርም (ሊያነቡት የሚገባ)
ጽዮን ግርማ – አዲስ አበባ
ዘወትር እንደምታደርገው ሁሉ በምታዝበት ሬዲዮ ጣቢያ ጓደኞቿን ሰብስባ ወደ ስቱዲዮ የገባችው ሚሚ ስብሃቱ ከትናንት በስቲያ ጀምሮ ስለታሠሩት ሁለት ጋዜጠኞችና ሰባት ጦማሪዎች ከፖሊስ አገኘኹት ያለችውን መረጃ ጠቅሳ ስታወራ ነበር። ኢትዮጵያን ለማተራመስ ከሚሠራው አርቲክል ዐሥራ ዘጠኝ ከሚባል ድርጅት ጋር ሲሠሩ ነበር፣ትልልቅ ሆቴል እየተገናኙ ይወያዩ ነበር፣ኢትዮጵያ ውስጥ ሰዎችን ያደራጁ ነበር፣ ከሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅትና ከአምነስቲ እንዲሁም ከግብጽና ከኤርትራ ገንዘብ ይቀበሉ ነበር፤ የሚሉ ውርጅብኞችን በማውረድ እነርሱን የኢትዮጵያ ጠላት እራሷን ደግሞ የኢትዮጵያ ወዳጅ አድርጋ በመሳል ውንጀላዋን ስታዥጎደጉደው ነበር።