አቡጊዳ – ዞን ዘጠኞችና ጋዜጠኞች የአሥር ቀናት ቀጠሮ ተሰጣቸው፤ እስከዚያው በእስር ይቆያሉ
ከአርብ ሚያዚያ 17 ቀን ጀምሮ ኢሕአዴግ ዞን ዘጠኝ ተብለው በሶማል ሜዲያ ምህበረሰቡ የሚታወቁ ወጣት ጦማሪያንን ( ብሎገርስ) እንዲሆም ሌሎች ጋዜጠኞችን አይሰረ ሲሆን፣ እስረኞቹ ትልናት እሁድ ሚያዚያ 19 ቀን ፍርድ ቤት እንደቀረቡ ታወቀ።
የታሰሩ የዞን9 አባላትና ጋዜጠኞች ትላንትና እሁድ ሚያዝያ 19 አራዳ ፍርድ ቤት አንደኛ ወንጀል ችሎት የቀረቡት ቤተሰብ ሳይወቅ እና የሕጝ ባለሞያ በሌለበት ሁኔታ ሲሆን፣ ፍርድ ቤቱ የዋስ መብታቸውን ሳይመለከተ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጧል።
እስረኞቹ የታሰሩት ውጨ ሃገር ከሚገኙ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ነን ከሚሉ ጋር በገንዘብና በሃሳብ በመተባበር በማህበረሰብ ሚዲያ ሃገርን ታሸብራላችሁ በሚል ወንጀል ወንጀል ተጠርጥረው እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል።
የታሰሪኡት እስረኞች መካከል ሁእቱ ሴቶች ሲሆኑ፣ እስረኞቹ በሶስት ፋይል ለየብቻ ጉዳያችው እንደሚታይም የደረሰን ዘገባ ያመለክታል።
ማህሌት ፋንታሁን አቤል ዋበላ እና በፍቃዱ ሃይሉ ለሚያዚያ 30፣ ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ፣ ጋዜጠኛ አስማማው ሃይለግዮርጊስ እና በአምቦ ዩኒቨርሲቲ የሕግ መምህር የሆነው ዘላለም ክብረት ለሚያዝያ 29 እንዲሁም አጥናፍ ብርሃኔ ኤዶም ካሳየ ናትናኤል ፈለቀ ሚያዝያ 30 ተቀጥረዋል፡፡
“ሁለት ወንድ ልጆቼን በቀይ ሽብር አጥቼያለሁ ። ይሄኛውን ደግሞ በዚህ ላጣው ነው፡፡”ያሉ የአጥናፍ አባት አባት፣ «ኢትዮጵያ እንባችን ካላለቀ ማስቆም አታውቂም?» ሲሉ የተሰማቸውን ሐዘን ገልጸዋል።
የዞን ዘጠኞች እና ጋዜጠኞች መታሰር በሶሻል ሜዲያ ከፍተኛ ተቃዉሞ ያስነሳ ሲሆን፣ በተለይም በበርካት የኢትዮጵያዊያን ፌስቡክ ግሩፖች ትልቅ መወያያ አር፤እስት ሆኗል። ቁጥራቸው እጅግ በጣም በርካታ የሆኑ ኢትዮጵያዊያን አገዛዙ በወሰደው እርምጃ የተሰማቸው ሃዘን እና ብስጭት እየገለጹ ነው።
የዞን ዘጠኝ ስያሜ ለማታዉቁ ፡
“… የዞን 9 የሚለው ስያሜ የመጣው ጋዜጠኛ ርእዮት አለሙን ቃሊቲ እስር ቤት ሊጠይቁ በሄዱበት ሰአት ርእዮት አለሙ ዞን 9 ደህና ነው ? ብላ ስትጠይቃቸው ነበር። ቃሊቲ እስር ቤት ያለው እስከ ዞን 8 ድረስ ነው ከየት አመጣሽው ? አይ ዞን 9 ማለት ከእስር ቤት ውጪ ያለው የኢትዮጵያ ትልቁ እስር ቤትን ነው ብላ መለሰችላቸው።”