የአዲስ አበባ መስተዳድር ለአንድነት ፓርቲ ምላሽ ጻፈ! መስተዳሩ ፍቃድ ለመስጠት የተቸገረው እውን ለሕዝብ አስቦ ነው? ከመቼ ወዲህ?

መጋቢት 28 ቀን 2006 ዓ.ም አንድነት በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ የያዘውን ፕሮግራም እንዲያራዝም መጠየቁን ተከትሎ አንድነት ሰልፉን ለሚያዚያ 5 ቀን 2006 በማራዘም የእውቅና ደብዳቤ ጠይቆ ነበር፡፡ መስተዳድሩ በዕለቱ ሌላ ፕሮግራም መየዙን በማውሳት ሰልፉ ሚያዚያ 4 ቀን 2006 ሊደረግ እንደሚችል የእውቅና ደብዳቤ ለፓርቲው ጽፎ ነበር፡፡
ፓርቲው በበኩሉ ዕለቱ ለሰላማዊ ሰልፍ አመቺ አለመሆኑን አስረድቷል፣ መስተዳድሩ ፓርቲው ሰላማዊ ሰልፉን ማድረግ መብቱ መሆኑን በመግለጽ ነገር ግን አመቺ ይሆናል ያለውን ቀንና ቦታ በቀጣዩ ሳምንት እንዲያሳውቀው በደብዳቤ ጠይቋል፡፡ የፓርቲው አመራሮች ተለዋጩን ቀን ለማሳወቅ ለነገ ቀጠሮ ወስደዋል፡፡1947365_10201820445253707_7107089483870285363_n