የጀርመን ወታደሮች የሶማሊያ ዘመቻ DW Amharic April 4, 2014 Tagged with Amharic, amharic news, Ethiopia, ethiopian news in amharic, Ethiopians, News in Amharic የጀርመን ፌደራል ጦር እጎአ ከ2010 አንስቶ የሶማሊያ ወታደሮችን በማሠልጠን ይሳተፋል። እስካሁን ሥልጠናው የሚሰጠው ዩጋንዳ ነበር። የጀርመን የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ትናንት ባካሄደው ስብሰባ ባሳለፈው ውሳኔ መሠረት ከአሁን በኋላ የጀርመን ወታደሮች ስልጠናውን ሶማሊያ ውስጥ መስጠት ይጀምራሉ።