የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የርቀት ተማሪዎች አቤቱታ

በርካታ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የርቀት ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በ2005 ዓም ትምህርታቸውን ቢጨርሱም፣ ጊዚያዊ ዲግሪያቸውን ፣ ማለትም የዲግሪያቸውን ቅጂ ባለማግኘታቸው በስራ ፍለጋ ጥረታቸው ላይ እክል እንደደቀነባቸው በምሬት ገልጸዋል።