የደቡብ ሱዳን ጦርነትና የዉጪዉ ሚና

የደቡብ ሱዳን ጦርነት አዲሲቱን ሐገር እያነደደ ደሐ ሕዝቧን እየፈጀ-በገፍ እያሰደደ ነዉ።ተፋላሚ ሐይላት በምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን ( ኢጋድ ) ሸምጋይነት የተኩስ አቁም ሥምምነት ቢፈራረሙም ሥምምነቱ ገቢራዊ አልሆነም።