= ሥልጣንህን አድን = ኢሕአደጋዊ አጀንዳ ወደ = አገርህን አድን = ሕዝባዊ አጀንዳ ይቀልበስ።
በሕወሓት/ኢሕአደግም ይሁን በተቃዋሚዎች በረት እና ማደሪያ …….
እየከፋ ያለን ጉዳይ እየተሻሻለ ነው ማለት = እያወቁ ማለቅ …….
= ሥልጣንህን አድን = ኢሕአደጋዊ አጀንዳ ወደ = አገርህን አድን = ሕዝባዊ አጀንዳ ይቀልበስ።
እየተሻለኝ ነው እያለ ከሚሞት፣ በጣም ጥሩ ምልክት ነው እያለ ከሚገድል ያድነን ፡፡ ደግ ደጉን ማውራት የተሻለ ዓለም ለማየት ይጠቅማል የሚለው ብሂል እንደተጠበቀ ሆኖ፤ እየከፋ ያለን ጉዳይ እየተሻሻለ ነው ማለት ግን እያወቁ ማለቅ ዓይነት ነው፡፡
ምንሊክ ሳልሳዊ ዕውነቱን ተናግሮ የመሸበት ማደር ለአገርና ህዝብ ይበጃል እንጂ ጐጂ አይደም፡፡ የማይሰጋ ተስፋ የሌለው ሰው ነው ፡፡ አይመጣምን ትተሽ ይመጣልን ጨምሪበት” የሚሉት ዓይነት::
በየኑሮ መስኩ ያለውን ህመም፣ በየሙያ መስኩ ያለውን ተወሳክ፣ በየፖለቲካ መስኩ ያለውን ወረርሽኝ በጊዜ መመርመር ዋና ነገር ነው፡፡ እኛ የወደድነውን እያጐላን በየሚዲያው ብንለፍፍ ለሀገርና ለህዝብ ፋይዳ አይኖርም።
ለምርጫ እወዳደራለሁ የሚል ፓርቲም ይሁን ፕሮፓጋንዳ የሚረጭ ሚዲያ ፍትሐዊ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ ሰላማዊና ሕዝባዊ ሥርዓት ለመገንባትና በዚህ መንገድ ለመምራት ከፈለገ፣ ሕዝብን ማክበርና ማዳመጥ ጥበብ መሆኑን፣ አማራጭና ተለዋጭ የሌለው መርህ መሆኑን ለመግለጽና አፅንኦት ለመስጠት ነው፡፡
የሕዝብን ብሶት ማዳመጥና ለሕዝብ ከበሬታ የመስጠት ጉዳይ ጥበብ መሆን ብቻ ሳይሆን፣ ጊዜ የማይሰጥና በእጅጉ አንገብጋቢ ሕዝብ አድን እና አገር አድን አጀንዳ እየሆነ ነው፡፡ሥልጣንህን አድን ከሚለው ኢሕአደጋዊ አጀንዳ በላይ፡፡
በኢትዮጵያችንም እንደዚሁ ሕዝብን የማክበርና የማዳመጥ ጉዳይ ተገቢና አስፈላጊ ተብሎ ብቻ የሚታለፍ ሳይሆን፣ አንገብጋቢ ሆኖ የተግባር ያለህ እያለ በመጮህ ላይ ያለ አጀንዳ ነው፡፡ ላለው ችግር ብቸኛው ፍቱን መድኃኒትና ጥበብ ሕዝቡን ማክበርና ማዳመጥ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ እየጠየቀ ነው፡፡ አቤት እያለ ነው፡፡ እየጮኸ ነው፡፡ ጥያቄው ማነው ሕዝቡን እያከበረና እያዳመጠ ያለው ? የሚል ነው፡፡ ምንሊክ ሳልሳዊ