” …. ሁሉ ነገር አልቋል (ተውዲኡ ኣሎ)ክፉ፣ ክፉውን ቀብረነዋል!! ” መለስ የኤርትራውያን ነፃነት ቀን
መለስ በመጀመሪያው የኤርትራውያን ነፃነት ቀን ዝግጅት ላይ ለኤርትራውያን እንዲ ብሎ ነበር። «ቁስል እንዳለባችሁ አውቃለው። ለምን? ብትሉ ጀርባችሁ ላይ ያለው ቁስል በእኔ ጀርባ ላይም አለ። ይህንን ያለፈ ምህራፍ እርሱት አልላችሁም። ነገር ግን ቁስላችንን ማከክ የለብንም አሁን ሁሉ ነገር አልቋል (ተውዲኡ ኣሎ)ክፉ፣ ክፉውን ቀብረነዋል!!» ነበር ያለው።
ይህንን የመለስ ዜናዊ አነጋገር አንድምታ ስናይ «ይኸው ደረስንላችሁ! ጠላት ተቀበረ! መቀበር ብቻ አይደለም አስተሳሰቡንም አዛብተነዋል! ያለበት ነበር። እንግዲህ ማነው ጠላት? ኢትዮጵያ? የማን አስተሳሰብ ነው? የኢትዮጵያ! ምን አይነት አስተሳሰብ? እንግዲህ እንደምናውቀው በተለየ ጊዜ የኢትዮጵያን ሳይኮሎጂ የሚያዛቡ ነገሮችን ሲናገሩ ነበር። ለምሳሌ፦ «ባንዲራ እኮ ጨርቅ ነው!» ይሄ አባባልን ለሚያይ ሌላ ሰው በቀላሉ የአፍ ወለምታ ሊመስለው ይችላል።ነገር ግን ሆን ተብሎ የኢትዮጵያውያንን አስተሳሰብ ለማዛባትና ለማሽመድመድ የሚደረግ ሴራ ነው።
በባንዲራችን እንደምንኮራ ያውቃሉ! የሶስት ሺህ አመት ታሪክ አለን ብለን እንደምንኮራ ያውቃሉ! ነገር ግን ይህንንም ታሪካችንን ወደ መቶ አመት ዝቅ ለማድረግ ይጥራሉ፤ ባለፉት መሪዎቻችን በአጼ ምንሊክ ፣ በነ አጼ ቴዎድሮስ፣ በነ አጼ ዩሐንስ፣ በነ አሉላ እንደምንኮራና እንደምንወዳቸው ከእነሱ ጋርም ያለንን ትስስር ያውቃሉ! ወያኔዎቹ ባንዳዎች ግን በየጊዜው ቴሌቭዥን ላይ እየወጡ «የኢትዮጵያ አጼዎች እኮ ጊዜያቸውን ያሳለፉት በጦርነት ነበር።» ይላሉ። ይሄን መናገር በተለይ አቶ መለስ እንደሆቢ ነበር የወሰዱት የሚመስለው። እንግዲህ የኢትዮጵያ ህዝብ መሪዎቹ «ለካ እንዲህ ነበሩ» ብሎ እንዲያፍር! የዛሬውም ቅጥ ያጣ ድህነት «እነሱ ያመጡት ጣጣ ነው!» ብለውም ለመናገር ይሞክራሉ።
እንደዚህ አይነት ቀጣይ ነገሮችን አምጥተን አገጣጥመን «ባንዲራ ጨርቅ ነው!» ካሉበት ጊዜ ጀምሮ ያሉትን ሰብስበን ብናያቸው መለስ የተያያዘው ኢትዮጵያዊ አንገቱን ደፍቶ፣ በኢትዮጵያዊነቱ አፍሮ፣ ድህነትን እንዲቀበል፣ ከኋላ ቀርነት ጋር ተቆራኝቶ እንዲኖርና የበታችነት ስሜት እንዲኖረው አድርገዋል እየተደረገም ነው»