አቡጊዳ – የአንድነት ፓርቲ እና መኢአድ ሊዋሃዱ ነው
በምርጫ ዘጠና ሰባት ወቅት ጠንካራ ፓርቲ ይባሉ የነበሩት መኢአድ እና ኤዴፓ ነበር። ሁለቱን ፓርቲዎች የአንድነት ብሔራዊ ምክር ቤት እና የመኢአድ ላዕላይ ምክር አባላት ቤት መጋቢት 7 ቀን 2006 ዓ.ም አባላት በጋር ባካሔዱት ስብሰባ፣ ሁለቱ ፓርቲዎች የፊታችን ሐሙስ መጋቢት 11 ቀን 2006 ዓ.ም የቅድመ ውህደት ፊርማ እንዲያደርጉ መመሪያ ማስተላለፋቸውን ፍኖት ነጻነት ዘገበ።
በምርጫ ዘጠና ሰባት ከመደረጉ በፊት የፓርቲዎች ዉህደት ተፈጽሞ እንዳልበረ ይታወቃል። ምርጫዉ ከመደረጉ ከስድስት ወራት በፊት ብቻ ፣ በፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም፣ ዶር ብርሃኑ ነጋ ሸምጋይነት በወቅቱ ጠንካራ የነበሩት መኢአድ እና ኤዴፓ ፣ ዉህደት ሳይሆን ለምርጫዉ ዘመቻ ወቅት እንዲቀናጁ መደረጉ ይታወሳል። ቅንጅቱንም ከምርጫ በኋላም ወደ ዉህደት ለማሸጋገር የተሞከረው ሙከራም በተለያዩ ምክንያቶች ሳይሳካ መቅረቱ የሚታወቅ ነው።
አሁን በመኢአድ እና በአንድነት ሊደረግ ያለው ዉህደት፣ ከሁለት አመታት በላይ ፣ በርጋታና በጥንቃቄ ሰፊ ዉይይቶች እንደተደረገበት የገለጹት ያነጋገርናቸው የአንድነት አመራር አባላት፣ የዉህደቱ እንቅስቃሴ ከላይ ወደ ታች ሳይሆን ከታች ወደ ላይ እንደሆነ ይናገራሉ። «በቅንጅት ጊዜ ከላይ ወደ ታች ነበር ዉህደቱን ለማድረግ የተሞከረው። አሁን ግን ካለፉት ስህተቶች በመማር መቀራረብኑና የዉህደት እንቅሳሴ የተጀመረዉ በወረዳ ደረጃ ነው» ያሉት የአመራር አባላቱ፣ ለዚህ ቀን መደረሱ በዋናነት ምክንያት የሆኑት ከታች ያሉ የመኢአድ እና የአንድነት አባላትና ደጋፊዎች እንደሆኑም ለማሳየት ሞክረዋል።
የአንድነት ፓርቲ ከመኢአድ ሌላ ለሰማያዊ፣ ለአረና፣ ለኢዴፓም ሳይቀር አብሮ የዉህደት አሊያም የትብብር ጥሪ ማቅረቡ በስፋት የተዘገበ ነው። የአረና ፓርቲ ከአንድነት ፓርቲ ጋር የመዋሃድ ፍላጎት ያለው ሲሆን፣ በዉህደቱም ረገድ ዉይይቶች እየተደረጉ እንደሆነም ይታወቃል። የሰማያዊ ፓርቲ ከዚህ በፊት የነበሩ ተምክሮዎችን ከግምት በማስገባት፣ ነገሮችን በርጋታ ለማየትና ለጥንቃቄ ሲሉ፣ ለጊዜዉ በተናጥል መንቀሳቀሱን የመረጡ ቢመስልም. የአመራር አባላቱ ሰማያዊ ፓርቲ የአገርን ጥቅም ከሁሉም በላይ እንደሚያስቀድምና፣ ተባብሮ በመስራት እንደሚያምን ይናገራሉ።
ሌላው በተወሰኑ ክፍሎች የአገዛዙ ተለጣፊ ተደረጎ የሚቆጠረው ኢዴፓ አመራርም ፣ በተለያዩ ጊዜያት ይፋ ያደረጋቸው የፖለቲካ ፕሮግራሞቹና አቋሞቹ በብዛት ከአንድነት ፣ መኢአድ ካሉ ጋር እንደሚቀራረብ በመገልጽ፣ የኢሕአዴግ የዘር ፖለቲካን፣ የሰብአዊ መብት ረገጣን፣ ሙስናን የመሳሰሉት አጥብቆ ሲቃወሙ እንደነበረና እንደሚቃወሙም ይናገራሉ። በቅርቡ በሰንደ ጋዜጣ ላይ እንደተዘገበው የኢዴፓን የኢዴፓን የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ ወጣት ኤርሚያስን ፣ ፓርቲያቸው በቅርቡ ጉባኤ አድርጎ አዲስ አመራር በመረጠበት ወቅት ጉባኤው ካሳለፋቸው ውሳኔዎች መካከል በ1997ቱ ምርጫ የተፈጠሩ ስህተቶችን በማረምና ሌሎች ተቃዋሚ ፓርቲዎች ለአዴፓ የፖለቲካ እውቅና የሚሰጡ ከሆነ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር አብሮ ለመስራት ዝግጁነት መኖሩን አስታውቀዋል።