በቅማንት ብሔረሰብ አባላት ላይ እየደረሰ ያለዉ እስራትና አፈና
ሙሉውን ጽሁፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ። በቅማንት ብሔረሰብ ላይ እየደረሰ ያለዉ እስራት አፈና
የቅማንት ህዝብ በአማራ ክልል በሰሜን ጎንደር ዞን በስምንት ወረዳዎች በኩታ ገጠምና በተያያዘ መልክዓ ምድር ለዘመናት ሰፍሮ የሚገኝና የራሱ የህዝብ አመጣጥ ታሪክ፣ ቋንቋ፣ ባህልና ወግ ያለው፣ ከአጎራባች ህዝቦች በተለየ መልክ በቅማንትነቱ ተመሳሳይ የሆነ ሥነ-ልቦና አለኝ ብሎ የሚያምን ህዝብ ነው፡፡ በባለፉት የግፋና የሰቆቃ ሥርዓቶች የቅማንት ህዝብ እንደሌሎች ኢትዮጵያዊያን ሁሉ የብሔራዊ ጭቆናውን ገፈት ከጭቆናው መፍለቂያ ምንጭ እየተቀዳ እንዲጋት ተደርጓል፤ በማንነቱ ከመኩራት ይልቅ እንዲሸማቀቅ ፣ በቋንቋው ከመናገር ይልቅ፣ እንዲሰደብበት፣ በባህሉ ከመኩራት ይልቅ እንዲያፍር ተደርጎና በፖለቲካው፣ በአስተዳደሩና በኢኮኖሚው ረገድ በአገሩ ላይ ባይተዋር ሆኖና ተገልሎ ዘመናትን አሳልፏል፡፡
የብሔራዊ ጭቆና ብሶት በወለደው ህዝባዊ ትግል ሚሊዮኖች ታግለው ሽዎች መስዋዕት ሆነው አፋኙንና ጨቋኙን የደርግ ሥርዓት በሀይል በመገርሰስ የተለያዩ የኢትዮጵያ ብሔረሰቦች ይደርስባቸው ከነበረው ብሔራዊ ጭቆና በማላቀቅ የሁላችን ኢትዮጵያን በመፈቃቀድ ለመገንባት የሚያስችላቸው ህገ-መንግሥት ፀድቆ ጉዞው ከተጀመረ ከሁለት አስረተ ዓመታት በላይን አስቆጥሯል፡፡
ይሁን እንጅ የቅማንት ህዝብ በዚያ የመራራ ብሔራዊ ትግል ውስጥ ከሌሎች ኢትየጵያዊያን ጋር በመሆን እኩል ቢሳተፍም ዛሬም በማንነቱ ኮርቶ እንደሌሎች ኢትዮጵያዊያን የህገ-መንግስቱ ቱርፋት ተቋዳሽ ከመሆን ይልቅ ዛሬም በደባል ማንነት ሥር እንዲወደቅ ተገዷል፡፡
ህዝቡ ህገ-መንግሥታዊ መብቱን ለማስከበር ህጉና ሥርዓቱ በሚፈቅደው መሰረት የማንነትና የራስ አስተዳደር ጥያቄ ለክልሉ መንግሥት ከዛሬ አስር አመት በፊት ቢያቀርብም ለጥያቄው የተለያዩ ማደናገሪያችን በማስቀመጥ ሲገፋ ከቆየ በኋላ የአመራ ብሔራዊ ከልላዊ መንግሥት ተወካዮች ምክር ቤት ነሀሴ 03/12/2005 ባካሄደው ዉሳኔ ‹‹ቅማንት የሚባል ህዝብ የለም ያለ አካል ባይኖርም የራስ አስተዳደር ግን ሊፈቀድለት አይችልም›› የሚል ዉሳኔ አስተላለፈ፡፡ ይህ ዉሳኔ ተገቢ አለመሆኑን በቅማንት ህዝብ ተወካይ ኮሚቲዎች አማካኝነት ለፌደሬሽን ምክር ቤት ይግባኝ ተጠይቆ ምክር ቤቱም ይግባኙን ተቀብሎ በመሬት ላይ ያሉ ጥሬ ሀቆችን በራሱ መንገድ ለማጥናት ወደ ቦታዉ በተንቀሳቀሰበት ወቅት በአዲስና በተቀናጀ መልክ የአፈና እና የእስራት ዘመቻዎቸ በህዝቡና በአመራር ኮሚቴዎች በክልሉ አድማ በታኝ እና በመደበኛ ፖሊስ ሰራዊት በታገዘ ሀይል አማካኝነት ከየካቲት 28/06/2006 ዓም አስከ መጋቢት 01/07/2006 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ ቀናት በላይ አርማጭሆ፣ በመተማ፣ በጭልጋ ወረዳዎች 50 የኮሚቴ አመራርና ሌሎች የብሔረሰቡን ተወላጆች በቁጥጥር ስር አውሏል፡፡ በላይ አርማጭሆና በጭልጋ ወረዳ የተያዙት ግለሰቦች ከሌሊቱ 06 ሰዓት አስከ ጥዋቱ 12 ሰዓት በዉድቅት ለሊት በራቸው እየተንኳኳ ሲያዙ በመተማ ወረዳ ደግሞ ህዝባዊ ሰላማዊ ሰለፍ በማካሄድ ላይ እያሉና ሰልፉ በሰላም ከተጠናቀቀ በኋላ ነበር በቁጥጥር ስር እንዲዉሉ የተደረጉት፡፡
ግለሰቦች በተያዙበት ወረዳ የማረሚያ ቤት ችግር ሳይኖር የታሳሪዎቸንና የታሳሪ ቤተሰቦችን ሥነ-ልቦና፣ ኢኮኖሚና ሞራል ለመንካትና ታሳሪዎች የቅርብ ዘመዶቻቸው፣ ወዳጀቻውና ሌሎች የህብረተሰብ ክፈል ሊጎበኛቸው በሚችሉበት ወረዳ መታሰርና መዳኘት ሲገባቸው፣ አርቆ በመዉሰድ ከጎንደር ከተማ በ80ና 100 ኪ.ሜ በሚርቁ ወረዳዎች በዳባትና በደባርቅ ወረዳዎች ተወስደው እንዲታሰሩ ተደርገዋል፡፡
የታሰሩ የቅማንት ህዝብ አባላትና የአመራር አካላት ዝርዝርም ከዚህ እንደሚከተለው ቀርቧል
| ተ.ቁ | የታሳሪ ግለሰብ ሥም | ሥራ | የመኖሪያ አድራሻ አድራሻ | በኮሚተው ውስጥ ያለው ኃላፊነት | ታሰሮ የሚገኝበት ወረዳ | በቁጥጥር ሥር የዋለበት ቀን | ||||
| ክልል | ዞን | ወረዳ | ቀበሌ | ሰ.ቁ | ||||||
| 1 | መቶ አለቃ ጥጋቡ ዘገየ | የመንግሥት | አማራ | ሰ/ጎንደር | ጭልጋ | አይከል | ሰ/ጎንደር (ዳባት) | 28/06/2006 | ||
| 2 | አቶ ነጋ ተሾመ | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ||
| 3 | አቶ ወልዴ ፈረደ | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ||
| 4 | ወ/ሮ የሮም ማለደ | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ||
| 5 | አቶ ታደገ አወቀ | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ||
| 6 | አቶ አበራ ከበደ | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ||
| 7 | አቶ ከፋለ ማሞ | የግል | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ||
| 8 | አቶ አበራ ዘመነ | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ||
| 9 | አቶ አቡሀይ ታደሰ | የግል | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ||
| 10 | አቶ ዘነበ ምትኩ | የመንግስት | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ||
| 11 | አቶ ሰጠኝ ወለላው | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ||
| 12 | አቶ ተስፋሁን አብቦ | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ||
| 13 | አቶ አራጋው አይንሸት | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ||
| 14 | አቶ በረከት አበው | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ||
| 15 | አቶ ንጋቱ ፀጋ | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ||
| 16 | አቶ መካሻው አበው | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | 30/06/06 | ||
| 17 | አቶ አማረ ማዘንጊያው | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ||
| 18 | አቶ አብዩ ፍሥኃ | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ||
| 19 | አቶ ታረቀኝ ገዳሙ | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ||
| 20 | አቶ አቦነህ አለሙ | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ||
| 21 | አቶ ዘርፉ እሸቴ | ላይ አርማጭሆ | ት/ድንጋይ | ሰ/ጎንደር (ደባርቅ) | 28/06/06 | |||||
| 22 | አቶ እሸቴ ነጋ | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ||
| 23 | አቶ ፈቃዴ ምግብ | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ||
| 24 | አቶ ፈቃዴ ማሞ | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ||
| 25 | አቶ አማረ ማዘንጊያው | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ||
| 26 | አቶ ደጉ ገነት | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ||
| 27 | አቶ ጌታነህ ፀጋው | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ||
| 28 | አቶ አበራ ታከለ | የግል | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ||
| 29 | አቶ አየነው አለፈ | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ||
| 30 | አቶ ስማቸው ማዘንጊያ | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ||
| 31 | አቶ ደሴ ደረጀ | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ||
| 32 | አቶ አፈወርቅ ባዩህ | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ||
| 33 | አቶ ሰለሞን ፀጋየ | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ||
| 34 | ፶ አለቃ ደመላሽ ባድማው | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ||
| 35 | አቶ መሰረት ተስፈሁን | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ትክል ድንጋይ | 01/07/06 | |
| 36 | አቶ መልኬ ደልድል | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ትክል ደንጋይ | ›› | |
| 37 | አቶ ኃይሉ ገነነ | ትክል ድንጋይ | ›› | |||||||
| 38 | አቶ እንደሻው ቦጋለ | የግል | ›› | ›› | ጎንደር | ጎንደር | መተማ | ›› | ||
| 39 | አቶ ሙላት ለገሰ | የመንግሥት | ›› | ›› | ጎንደር | ጎንደር | መተማ | 30/06/06 | ||
| 40 | ውበት አለሙ | ›› | ›› | ›› | ›› | መተማ | ||||
| 41 | አቶ መላኩ ተፈራ | የመንግሥት | ›› | ›› | መተማ | ገንዳዉኃ | ›› | ›› | ||
| 42 | አቶ የእኛነው እሸቴ | ›› | ›› | ›› | መተማ | ›› | ›› | ›› | ||
| 43 | አቶ አባተ አስረስ | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ||
| 44 | አቶ መልካሙ ባጫ | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ||
| 45 | አቶ ይስማው በላይ | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ||
| 46 | አቶ አስናቀው መንግስቱ | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ›› | ||
| 47 | አቶ አስቻለው ተፈራ | ›› | ›› | ›› | ›› | |||||
| 48 | አቶ ያቆብ ማሩ | ›› | ›› | ›› | ›› | |||||
| 49 | አቶ ሙላት ታከለ | ›› | ›› | ›› | ›› | |||||
| 50 | አቶ አስማረው አየልኝ | ›› | ›› | .. | ›› | |||||