የኢትዮጵያ መንግሥት፡- በኮምፕዩተር ስለላ ተከሰሰ፤ እንዲህ ዓይነቱን ውንጀላ አስተባበለ
የኢትዮጵያ መንግሥት የተራቀቁ የስለላ ሶፍትዌሮችን እየለቀቀባቸው የኮምፕዩተሮቻቸውን ይዘት እንደሚሠርቅ እና የግል ግንኙነቶቻቸውንም እንደሚከታተል በውጭ የሚኖሩ በርካታ ኢትዮጵያዊያን ስሞታዎችን እያሰሙ መሆናቸው እየተነገረ ነው፡፡
አንድ የዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ ነዋሪ በዩናይትድ ስቴትስ ፌደራል ፍርድ ቤት በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ክሥ መመሥረታቸው፤ ሌላ አንድ ሰው ደግሞ ለእንግሊዝ ፖሊስ አቤቱታ ማስገባታቸው ታውቋል፡፡
ከትናንት በስተያ ማክሰኞ ዋሽንግተን ዲ.ሲ. ውስጥ በሚገኝ አንድ ፌደራል ችሎት የተከፈተ ዶሴ ከዚህ የስለላ አድራጎት ጀርባ ያለችው ኢትዮጵያ እንደሆነች ጠቁሞ ከሣሹ የአሥር ሺህ ዶላር የጉዳት ካሣ እንዲከፈለው ጠይቋል፡፡
እንግሊዝ ዋና ከተማ ለንደን ላይ በቀረበ ሌላ ክሥ እዚያ በስደት የሚኖሩትና የግንቦት ሰባት ሥራ…