የማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክ ዕልቂት

ያዩ እንደሚሉት በርግጥም ዘግናኝ ነዉ።የሰዉ አንገት በገጀራ ይቀነጠሳል።እጅ፥ እግር፥ በጎራዴ ይቆረጣል።ሌላ አካል በጩቤ ይጨቀጨቃል። መንገዶች በደም አበላ ጨቅይተዋል-እየጨቀዩም ነዉ።አስከሬን በየጉርጓዱ ይከመራል።ከተንቀሳቃሽ ሥልክ እስከ ምግብ፥ ከሐብል እስከ ብስክሌት ያሉ ቁሳቁሶች ይመዘበራሉ። ቤቶች፥ መደብሮች፥ ቁሳቁሶች፥ መሳጂዶች ይነዳሉ።