የፈረደበት ግንቦት 7፤ የፈረደባት ኤርትራ

ለአቶ ያሬድ ኃ/ማርያም አንዳንድ መልሶች

ተከልሚካኤል አበበ – ቶሮንቶ

እንደመግቢያ፤ ያሬድና ጽሁፉ

1-         አቶ ያሬድ ሀይለማሪም (ያሬዶ) ለሰብአዊ መብት መሟገት አመል ሆኖበት (አመሉ፤ አዎንታዊ በሆነ መልኩ ማለቴ ነው)፤ ከጥቂት ቀናት በፊት አንድ ጽሁፍ አውጥቶ ነበር፡፡ ያንን ጽሁፍ ተከትሎ አንዳንድ በብእር ስም ጀርባ የተደበቁ ተቺዎች አበሳጩት መሰለኝ ሌላ ተከታይ ሁለተኛ ጽሁፉም ጽፎዋል፡፡ የኔ አስተያየት በመጀመሪያው ጽሁፍ ላይ ነው፡፡ ከሞላ ጎድል ጽሁፉ፤ ግንቦት ሰባት፤ ለኢትዮጵያ እንታገላለን ብለው ኤርትራ የገቡ ወጣቶች ላይ፤ ከኤርትራ መንግስት ጋር በመተባበር፤ ብዙ ግፍ እየፈጸመ ወይንም እያስፈጸመ ሲሆን፤ መገናኛ ብዙሀን ይሄ ግፍ ሲፈጸም እያዩ ዝም ማለታቸው፤ አግባብ አይደለም የሚል ነው፡፡ የያሬዶ ጽሁፍ ሸጋ ነበር፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ …