አቡጊዳ – ሕወሃት ገፍቶ ያስወጣቸው የሕግ ባለሞያ

አቶ ብርሃኑ በርሄ ይባላሉ። እስከ 1994 ድረስ የሕወሃት አባል ነበሩ። የሕግ ባለሞያ ናቸው። በትግራይ ክልል የፍትህ ቢሮ ሃላፊ ነበሩ። « የፍህት ቢሮ አደረጃጀት እና አቃቢ ሕግ ከፖለቲክ ገለልተኛ መሆን አለባቸዉ » በሚል አማራጮችን አቀረቡ። « አቃቤ ሕግ ተጠሪነቱ ወይም ለካቢኔ ወይንም ለምክር ቤት መሆን አለበት» የሚል የጥናት ወረቀት አቀረቡ። ያቀረቡት ሃሳብ በሕወሃት አመራሮች ዉድቅ ተደረገ።

«የትግራይ ከተሞች እንዴት ይተዳደሩ » በሚል የሚያጠና አንድ ቡድን ተቋቋመ። እዚያ ቡድን ዉስጥ አባል ሆኑ። በከተሞች የነበሩትን የአስተዳድር ብልሹነት ቡድኑ ተገነዘበ። የከተማ አስተዳደሮች በፓርቲ ስብሰባ ጊዜ የሚያጠፉ መሆኑን፣ በወር ዉስጥ ካለው የስራ ቀናት ቢሯቸው የሚቀመጡት ግማሹን እንኳን እንደማይሞላ በጥታቸው ሪፖርት አሰፈሩ። ከተሞች በፓርቲ ካድሬዎች ሳይሆን በባለሞያተኞች እንዲተዳደሩ ሃሳብ አቀረቡ። «ኢሕአዴግ በከተማ ሥር እንዳይሰድ እያደረጋችሁ ነው» በሚል ተቃዉሞ ገጠማቸው።

«ሕወሃት የዲሞክራሲ ስርዓት ያረጋግጣል ብዬ የነበረኝ እምነት አሁን ስለሌለኝ ከፓርቲዉ ተሰናብቻለሁ። የመንግስትም ሃልፊነት አልፈልግም» ብለው በጽሁፍ ፓርቲዉን ተሰናበቱ።

በ1997 ምርጫ በግላቸው የመቀሌ ከተማ የግል ተወዳዳሪ ሆነዉ ነበር። ከዚያም ከሌሎች ሕወሃትን ከለቀቁ ኢትዮጶያዉያን ጋር አረናን መሰረቱ። በወቅት የአረና አቶ ገብሩ አሥራትን ተክተው የአረና ሊቀመንበር ናቸው።

አቶ በርሄ አረና ሲቋቋም የክልል ሆኖ ቢቋቋምም በፖለቲካ ፕሮግራሙ የኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ብቻ እንዳተኮረ ያስረዳሉ። ከጀምሩ የሁኔታዎች አለመመቻቼት እንጂ በአገር አቀፍ ድርጅት ሥር መስራት ፍላጎት እንደነበራቸው የገለጹት አቶ ብርሃኑ፣ አረና ቢቻል መድረክ እንዳለ ወደ ዉህደት እንዲመጣ፣ ካልተቻለ ግን ከመድረክ ዉስጥ ካሉ ድርጅቶች ጋር በተናጥል ለመዋህድ እንደሚፈልጉ ይናገራሉ። ለመድረክ አባል ድርጅቶ በሙሉ የዉህደት ጥያቄ እንዳቀረቡ የጠቀሱት አቶ ብርሃኑ፣ ከኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ በስተቀር፣ ከሌሎቹ ፣ ከአንድነት ፓርቲ፣ ከደቡብ ሕዝቦች እና ከሶሻል ዴሞክራቲክ ኮንግረስ አዎንታዊ ምላሽ እንዳገኙ የገልጸዋል።

አቶ ብርሃኑ በርሄ፣ ከሲ.ቢ.ኤስ ራዲዮ ጋር ያደረጉትን ቃለ ምልልስ ለማዳመጥ እዚህ ይጫኑ !