ኢሳት ገለልተኛ ይሆን ዘንድ እንደገና ይዋቀር
አማኑኤል ዘሰላም
“ስልክ ጠላፊው ሰላይ ‘ጋዜጠኛ'” የሚል አንድ ጽሁፍ አነበብኩ። ሲያትል የሚኖር አንድ ኢትዮጵያዊ ናቸው የጻፉት። የአውራምባ ታይምስ ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደን አጠንክረው ይተቻሉ። በቅርቡ በድረ ገጾችና ፌስቡክ የተለቀቀው፣ አቶ አበበ ገላው የተናገሩትን አንዳንድ አባባሎችን የያዘ ኦዲዮ ነው። ይህ ኦዲዮ አቶ አበበ፣ ሳያውቁት የተቀዳ ነው። ይህ አይነቱም ንግግርን በሚስጠር የመቅዳት የፓፓራዚ ተግባር በጣም አሳዛኝ ከመሆኑም በተጨማሪ ነውርም ነው።