የፎቶ ኤግዚቢሽን

ፎቶዎች ከቃላት በላይ ይናገራሉ እንዲሉ ባለፈው ዓመት ወዲያ ወዲህ ስል መንገዴ ላይ አጋጥመውኝ ካነሳኋቸው ፎቶዎች ላካፍላችሁ ወደድኩ:: እነሆ:-

ፒያሳ – ራስ መኮንን ግርጌ


የቴኒክ ብልሽት:-  መጽሔቱ በአንድ እትሙ ሽፋን ገጹ ላይ ኢትዮጵያ ከስንዴ ኢምፖርት አድራጊነት አልተላቀቀችም ይላል፡፡ የውስጥ ገጹን ጽሑፍ ደግሞ በቀጣዩ ምስል ይመልከቱ፡፡

የቴኒክ ብልሽት (ቀጣይ):-  መጽሔቱ በውስጥ ገጹ ላይ ኢትዮጵያ ከስንዴ ኤክስፖርት አድራጊነት አልተላቀቀችም ይላል፡፡ (የሽፋን ገጹን ጽሑፍ ከላይ ይመልከቱ፡፡)




Not Yet Arrived in 2014. In front of Bole Friendship Building


ሁሉም ሰዎች አንድ ጋዜጣ (ልዕልና ከመታገዱ በፊት) – አሁን እነዚህ ካፌዎች በረንዳቸው ላይ አገልግሎት እንዳይሰጡ ታግደዋል::


ይህ ማስታውቂያ ተዘቅዝቆ ነው ወይስ ተልጦ ወይስ ግራ ቀኝ ተዛውሮ ወይስ ሁሉም? (ራስ መኮንን አለፍ ብሎ)


የቤተልሔም ሕንፃ /መገናኛ/ (ጀርባ – ፊቱን ከታች ይመልከቱ)
ቤተልሔም ሕንፃ ከፊቱ (በነገራችን ላይ ይህ ሕንፃ መስታወቱ አንፀባራቂ በመሆኑ እንዲቀየር ማስጠንቀቂያ ከተጻፈበት ወራት አልፈዋል::)
Guess Where? You got it right; it is in front of Bole Medhanialem – የጄኔራሎቹ ሰፈር
ለልማቱ ነው – ምናለበት?



ቃሊቲ (የጠጠር ማምረቻውን ስም ሳየው ያስቀኛል:: አንድ ሰሞን

ሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅን ድንጋይ ማምረቻ ይሉት የነበረው ይመጣብኛል፡፡)

Got it Wrong: የኮሌጁ የመጽሔት ማስታወቂያ ኮሌጅ የሚለውን ጠንቅቆ አልጻፈውም!

“ኢ-ልማታዊ መጽሐፎች” (ግልጽ በሆነ ምክንያት የትምህርት ቤቱን ስም ከመጥቀስ እታቀባለሁ)

“የልማት መስዋዕት” – ለገሃር ከለታት አንድ ቀን

Legend making: ቦሌ ቴሌ

ሶኒክ ስክሪን – ፒያሣ

Legend Making: ቦሌ – ሰን በርድ ካፌ (አሁን ጀግና አይሞትም የሚለው ቅርጽ ተነስቷል)

ሐዋሳ አውቶቡስ ተራ – “ከኤድስ ለማምለጥ በየሱስ ማመን ነው” Really?!

ሻሸመኔ – “የረዳኝ እግዚአብሔር ነው መኝታ ቤት” (ይህን ሳየው “እህቴ የላክሽልኝን ገንዘብ ቁም ነገር ላይ አዋልኩት ሬስቶራንት” ብሎ አብርሃም አስመላሽ የቀለደው ቀልድ ይታወሰኛል::)