በጎ ሰዎችን እንጠቁም፣ እናበረታታ፣ እንሸልም
|
የአምናው ተሸላሚ የመቄዶንያ የአረጋውያንና የአእምሮ ሕሙማን መርጃ ድርጅት መሥራች አቶ ብንያም
|
የዓመቱ በጎ ሰዎችን እንድንጠቁም በወጣው ማስታወቂያ መሠረት እስካሁን 43 በጎ ሰዎች ተጠቁመዋል፤ አሁንም ጊዜ አለን፡፡ እንጠቁም፣ መልካም ሰዎችን መሸለም ክፉዎችን ማስተማር ነው፤ መልካም ሰዎችን መሸለም ጀግኖችን መፍጠር ነው፤ መልካም ሰዎችን መሸለም ለልጆቻችን አርአያ መፍጠር ነው፡፡
ለሀገራቸው፣ ለወገናቸው፣ ለአካባቢያቸው መልካም ሠርተዋል፣ ዕውቅና ልንሰጣቸው፣ ልናከብራቸውና ልናበረታታቸው ይገባል የምትሏቸውን በሚከተለው መመዘኛ መሠረት በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ ይጠቁሙ፡፡
መመዘኛውን እዚህ ያንብቡ(click here)
የመጠቆሚያ አድራሻ