አቡጊዳ – “አቶ ገብሩን ለመግደል መሞከር ዉንብድና ነዉ” አሉ የአንድነት ም/ፕሬዘዳንት

የቀድሞ የአራና ትግራይ አመራር አባል፣ አቶ ገብሩ አሥራት፣ ከባለቤታቸው ጋር በመኢካን እይሄዱ እንዳለኡ ድንገት መኪናቸው በእሳት መቃጠሏ በስፋት ተዘግቧል። «የአቶ ገብሩ አስራት መኪና በእሳት ነደደች» በሚል ርእስ ሥር በአስራት አብርሃም የተጻፈ ዘገባ በፌስ ቡክ ተለቋል። ዘገባዉን እንደሚከተለው አቅርበናል፡

የቀድሞው የትግራይ ክልል ፕሬዚደንት እና የዓረና ሊቀመንበር አቶ ገብሩ አስራት ከባለቤታቸው ከወ/ሮ የውብማር አስፋው ጋር በመሆን በመኪና እየሄዱ እያለ ድንገት መኪናቸው በእሳት መያያዟን የተመለከቱ ሰዎች ባደረጉላቸው ጥቆማና ርብርብ ከእሳቱ ቃጠሎ ለጥቂት መትረፋቸውን ማወቅ ተችሏል። በመኪናዋን ግን እዚያ የነበረው ሰው ሁሉ ብዙ ርብርብ ቢያደርግም ከቃጠለው ማተረፍ አልተቻለም። በእውነቱ ይህን መረጃ እንደደረሰኝ አላመንኩም ነበር፤ በመሆኑም ወዲያው ወደ አቶ ገብሩ አስራት ስልክ ደውዬ እውነት መሆኑን ማረጋገጥ ችያለሁ። ነገር ግን ይሄ አደጋ ሆን ተብሎ የተቀነባበረ የግዲያ ሙከራ ይሁን አሊያም በአጋጣሚ የተፈጠረ የእሳት ቃጠሎ ይሁን ማወቅ አልተቻለም። የአቶ ገብሩ ባለቤት ወ/ሮ የውብማር አስፋው ህወሃት ባካሄደው የትጥቅ ትግል ግንባር ቀደም ሚና ከነበራቸው ጥቂት ሴት ታጋዮች ውስጥ የሚመደቡ እና “ፊኒክስዋ ሞታም ተነሳለች፥ ያልተቋጨው የትግራይ ሴቶች ትግል” የሚለውን መፅሐፍ የፃፉ ናቸው።ለማነኛውም ለአቶ ገብሩ አስራት እና ለባለቤታቸው ወ/ሮ የውብማር አስፋው እንኳን በህይወት አተረፋችሁ ለማለት እፈልጋለሁ።

በዚህ ጉዳይ ላይ አስተያየታቸውን ያቀረቡት የአንድነት ተቀዳሚ ም/ፕሬዘዳነት አቶ ተክሌ በቀለ በአቶ ገብሩ ላይ ለደረሰዉ አደጋ በ፣ን ምክንያት እንደሆነ በአስቸኳይ መጣራት እንዳለበት አሳስበዋል።

«አቶ ገብሩና ወ/ሮ የዉብማር እንኳን ከአደጋዉ ተረፋችሁ ወገኖቼ! አቶ ገብሩ የዚህን ድሃ ህዝብና አገር ሀብት ካልመነዘሩ አመራር ነበሮች አንዱ ናቸዉ፡፡በዚህም አርኣያነታቸዉ በበርካታ ሰዎች ክብር አላቸዉ፡፡እሳቸዉን ለመግደል የሚሞክር ፤ ለሞከረዉ ሃይል የሚሰጠዉ ትርጉም ዉንብድና እንጂ ሌላ ሊሆን አይችልም፡፡የሚመለከተዉ አካል አስቸኳይ ማጣራት አደርጎ መልስ ሊሰጥበት ይገባል፡፡”” ሲሉ ነበር አቶ ተክሌ ድርጊቱን ዉንድብና ብለው የጠሩት።

በዚህ አጋጣሚ ለአቶ ገብሩ አሥራት እና ለባለቤታቸው እንኳን እግዚአብሄር በሰላምና በጤና አተረፋችሁ እንላለን።