በአፍ የመጣ በሽታ – ከአደፍርስ ተሰማ

ጊዜው ቆየ እንጂ የአንደኛ ደረጃ ተማሪ እያለሁ “አብሮ መኖር በዓለም ዙሪያ” የሚል መጽሃፍ እንድንማርበት መመደቡ ትዝ ይለኛል። ዛሬ አብረን የምኖረው ዓለም በፈጠረችው የጊዜው ቁሳቁስ ሆነና ሃሎ ስንባል አንዴ ያዝልኝ በማለት ሰውን መስመር ላይ እያስጠበቅን ፌስቡክ፤ ስካይፕ ሌላም ሌላም ነገር ላይ ልባችን ተሰክቶ ዓይናችን አጥርቶ ማየት ተስኖታል። በዚሁ ሳቢያ በሚመጣ ትውውቅም በሩቅና በቅርብ በወሲብ ፍላጎት ተቀይደን ከኮምፒውተርና ከመስል የኤሌክትሮኒክስ መገልገያ ነግሮች ጋር አለቅጥ ተላምደናል። ሰለጠንኩ አውቄአለሁ የሚለን የምዕራቡ ሃገር ቆሻሻ ባህር ተሻግሮ ሃገርችንንም ያምሳል። የደላው ሙቅ ያኝካል እንዲሉ ሆነና እኛም እንደ ፈረንጆች ለመሆን ውታፍ አሰራራቸውን ተላመድነው። ሰዶማዊው ሥራ እንደነጻነት ተቆጥሮ ሰው ሰልፍ ይወጣበታል። ያው እውቁ ጻሃፊ ጆርጅ ኦርዌል በ 1984 መጽሃፉ ላይ እንዳለው ነገር የተገላቢጦሽ ሆኖአለ። ነጻነት ባርነት ነው። ባርነትም ነጻነት ነው።
በቅርቡ አንድ የቆየ ወዳጄ ከራቀ ቦታ ደውሎ ያጫወተኝ ነገር ነው ለዚህ ጽሁፍ መነሻ የሆነኝ። አንዲት በጋራ የምናውቃት የቤተሰብ ልጅ ሃፍረተሥጋዋ ገቢያ ላይ ወጣ ቢለኝ ከው አለኩ። የዘመድ ሞት እንደተረዳ። ተደረገ የተባለውን ድርጊት ከዝህ መዘርዘር ባይመቸኝም ጉዳዩ ሱባኤ ያስገባል። በነጻነት ስም ባርነት። በፍቅር ስም ጥላቻ። አሳዛኝ ድርጊት። ይህች ልጅና ዲያብሎስ የተጠጋው ሰው ፍቅረኛ ሆነው ሲኖሩ ልጅ በድብቅ በፊልም፤ አልፎ አልፎም እርስዋ ፈቅዳ በፎቶ ምንም ሳትለብስ ያነሳት ነበር። ከጊዜ በህዋላ ሲጣሉ በጊዜው የወሲብ ግንኙነት ሲያረጉ የነበረውን ፊልም ለፖርን ሳይት ይሸጠዋል። ራቁቱዋን ሆና ያነሳትን ደግሞ ፌስ ቡክ ላይ ይለጠፈዋል። ልጅትዋ በድንጋጤ ታማ ሆስፒታል ትገባለች። የሚወድዋትና ቤተሰብ እንዲያነሳ ካላነሳ ብቀላ እንደሚፈጽሙበት ዝተው ይነግሩታል። ነገሩ ውሃ ከፈሰሰ አይታፈስም ነበርና እርሱም ሆነ ድርጊቱን የለጠፈበት ዌብፔጅ ቢያነሱትም ነገሩ በአለም ዙሪያ ይበተናል። ለምን ይሆን እንዲህ አይነት አረመኔዎች የሆነው? እንዴት ሰው በወገኑ ላይ እንዲህ ይጨክናል። መልሱ አንድ ነው። የሥልጣኔ ምልክት ነው። የነጭ ቆሻሻ ሥራ እንደልማት መመን ነው። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ሲጋራ ከሚያጨሱ ይልቅ በአፍ ወሲብ የምያደርጉ በጉረሮ ካንሰር በሽታ እንደሚጠቁ አንድ የሳይንስ ምርምር አስረግጦ ያስረዳል። ትርፋቹህን ቁጠሩት። ምንድነው ተርፉ? ተፈጥሮ ባለፈቀደው ከፍት ነገር ሁሉ ወሲብ ማረግ? እንደዚህ ዓይነት የወሲብ መንገድ አሁንም ባይሆን ቆይቶ ዋጋ ያስከፍላል። በቀናው መንገድ ያረካው የወሲብ ጥማታቹሁ በተሽመደመድው መንገድ እርካታ ይመጣል ብሎ ማሰብ ራስን ማታለል ነው።
በአለም ዙሪያ ተበትናቹ ለምትገኙና በሃገር ውስጥ ለምትገኙ ሃበሾች የምለው አንድ ነው። እርቃናቹህን ፎቶም ፊልምም አትነሱ። ዋ በህዋላ ችግሩን አትወጡትም። ዛሬ ሞትኩልሽ የሚለው የልብሽ ሌባ ነገ ገቢያ ላይ የጋራ ድርጊታቹህን ያወጣዋል። አንቺም አንተም በአፍ የመጣ በሽታ ወደ መቃብር ሳያወርዳቹህ ንቁ። በወገናችን በተለይም በእህቶቻችን ላይ ግፍ ማረግን አቁሙ።
ሰላም እንቆይ