አባዱላ: ምንድነው ጩኸቱ???!!!!!

አባዱላ: ምንድነው ጩኸቱ???!!!!! ቴዲ: ልምምድ ላይ ነን አሁን "አላምን አለና….." እሚለውን ዘፈን ስጨርስ መምጣትህ ነው አባዱላ: ወይ ልጅ ቴዲ ልባም ነህ እኮ!! እንግዲህ አዝናለሁ…. በጅማ: በአዳማና…. ቴዲ: ይዘንባል? ከፊል ደመና? ጸሃያማ? አባዱላ: አንተ ልጅ ምንድነው ዛሬ ያጨስከው?!!…..ገና እሚያስጨስ ነገር ልነግርህ ነው! ቴዲ: ሌላ ልጅ ገጨህ ልትሉኝ እንዳይሆን??!!!!! አባዱላ: ወደ ገደለው ስንገባ ኦሮሚያ ውስጥ አትዘፍንም:: አሻፈረኝ ካልክ ሌላ መለስን ተማምኖ በረንዳ ያድር የነበረ ምስኪን ገጭቶ አመለጠ እንላለን ቴዲ: ምን አጥፍቼ ነው ይሄ ሁሉ መአት አባዱላ: ያው የሰሞኑ ክስ ነው …ቅዱስ ጦርነት….ሆሊ ዋር ቴዲ: አምለሰት ትሙ…ት አላልኩም!! ይህው መጽሄቱ አንብበው: በተጨማሪ ፌስቡክ…ፌስቡክ አለህ እንዴ?….ብቻ አሳውቄአለሁ..ሌላው የመጽሄቱ ኤዲተር በኢሜይል ለላከላቸው ሰዎች ስህተቱ የራሱ እንደሆነና ይቅርታ እንደጠየቀ ሳትሰማ አልቀረህም…እኔ ምን ማድረግ አለብኝ ከዚህ በላይ? አባዱላ: እንዲህ አይነት ስህተት የለም የቴክኒክ ችግር ያለውን ያጎድላል ቃላት ያባዳል ወይንም የሌላ ሰው ጽሁፍ አሳስቶ አንተ ውስጥ ይከታል…ተመሳሳይ ይሁፍ ደግሞ አልነበረም…ግን ደግሞ መጽሄቱ ተነባቢነቱ በእትም ስለሆነ ታትሞ በተበተነው ላይ የተባለው ስህተት የለም…ብቻ ግፊት አለብን ቴዲ: አያድርስ ነው አባዱላ አባዱላ: ግን አይገርምህም ህወሃቶች even በተመሳሳይ ሚዲያ ውስጥ ያሉት ድርቅ ብለው ጉዞ ወደቅዱስ ጦርነት ምናምን ነው እሚሉት ቴዲ: እነሱ ፖለቲካም ………ቆይ ለምን አልዘፍንም ምክኒያቴ አሳማኝ አይደለም?? አባዱላ: "ግፈኛውን ሚኒሊክ ያሞካሻል ይሄ ለኦሮሞ ህዝብ ያለውን ጥላቻ ያመላክታል" ይሉሃል ቴዲ: ይሄ ኮሜዲ ነው:: እኔኮ "ሚኒልክ ሚኒሊክ; ደግ አደረክ" እሚል ዘፈን አልዘፈንኩም:: ምኒሊክ የሚመሰገንበትን ከአድዋ ጋር ያለውን ስብእናውን ነው የዘፈንኩት እንደውም አድዋ የሁሉም ኢትዮጽያዊ ደም እና አጥንት ዋጋ መሆኑን ለመዘከር …… አባዱላ: ለማንኛውም እኛ ስፖንሰር እሚያደርገውን አካል ስምምነታችሁን እንድታፈርሱ ማስገደድ አንችልም ግን በሙዚቃ ዝግጅቱ ላይ ለሚፈጠር ማንኛውም ችግር ሃላፊነት እንደማንወስድና የጥበቃ ስራ እንደማንሰራ እናሳውቃለን… ቴዲ: ታዲያ ይሄ ዝግጅቱ አይካሄድ ብሎ ከመከልከል በምን ይለያል? አባዱላ: አራዳ እኮ ነሽ ቴዲ: ቀመርና አጫሉ በሚኒሊክ ለተፈጁ ሰዎች መታሰቢያ ዘፈን ሊለቁ ነው አባዱላ: እና ምን ለማለት ነው….ወዴት ወዴት ነው? ቴዲ: ኖ አባዱላ እኔ አስተሳሰቡን ነው…እኔ ሚኒሊክ ደግ አደረጉ ብዬ ሳልዘፍን የሳቸውን መልካም ስራ ስላሰብኩ ብቻ በክልሉ ሙዚቃ እንዳልጫወት ፈረዳቹ…እነ እጫሉ የሳቸውን ክፉ ስራ አሰባችሁ ብሎ ሰፈሬ አትምጥ የሚል የልጅ ስራ ተመሳሳይ ትርጉም አይዝም? አባዱላ: እኔ እንደዛ አስቤው አላውቅም በዚህ አይነት እነ እንትና በዚህ ሰፈር እነ እንትና በዚህ መንደር ሙዚቃ ማቅረብ አይችልም የፖለቲካ ትርጉሙ ሲሰፋ ደግሞ ሌላ ነው… ቴዲ …… አባዱላ……. ቴዲ…… አባዱላ……. as I clearly put in the note entitled "what is Oromofirst doing ?" I only stand against the campaign logo. evidences revealed so far dont support the claim given over there. however I enjoyed the mesmerizing vibe oromo ethiopians showed.