ወጣቱ ትውልድ
እ.ኤ.አ. የ2013 ዓመት የኢትዮጵያ የአቦሸማኔው (ወጣቱ ትውልድ) መነሳሳት ሲገመገም
ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ)
እ.ኤ.አ በጃንዋሪ 2013 “እ.ኤ.አ 2013 የኢትዮጵያ የአቦሸማኔው ትውልድ ዓመት ይሆናል” በማለት ትንበያ ሰጥቸ ነበር። እንዲህ ስልም ቃል ገብቸ ነበር፣ “የኢትዮጵያ ወጣቶች ለፍትህና ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ የሚያደርጉትን ትግል ለመደገፍ እና ወደ ላቀ ደረጃ ከፍ እንዲል የእራሴን ሙሉ አስተዋጽኦ እንደማደርግ እንዲሁም ትግሉ ወደ አዲስ ምዕራፍ እንዲሸጋገር ወጣቱ ትውልድ እንዲነሳሳ ሳደፋፍር ነበር።”