ምርጫ ቦርድ አዳራሹን ለአንድነት ጠቅላላ ጉባኤ ከለከለ – ፍኖተ ነጻነት
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ታህሳስ 19 እና 20 ለሚያከናውነው ጠቅላላ ጉባኤ የመሰብሰቢያ አዳራሽን ሆቴሎች እንዳያከራዮት ገዢው ፓርቲ የሆቴል ቤት ባለቤቶችንና አስተዳደሮቻቸውን ማስፈራራቱን ተከትሎ ክፍያ በተፈጸመባቸው አዳራሾች ጭምር ፓርቲው መጠቀም እንደማይችል በመነገሩ የቀረው አማራጭ የምርጫ ቦርድን አዳራሽ መጠየቅ በመሆኑ ፓርቲው አዳራሽ ለመከራየት ያጋጠሙትን ችግሮች በመግለጽ ለምርጫ ቦርድ ጥያቄ አቅርቧል፡፡ጥያቄው የቀረበለት ምርጫ ቦርድ በበኩሉ አዳራሹን ለመስጠት እንደሚቸገር በመጥቀስ አዳራሹ ለስብሰባ የሚፈለግ በመሆኑ አንሰጣችሁም ብሏል፡፡