አበራ የማነአብ እና ገነት ግርማ
በአበራ ለማ (ደራሲ፣ ጋዜጠኛና ባለቅኔ)
አንጋፋው የዲሞክራሲና የለውጥ አርበኛ አበራ የማነአብ የሰባ ሁለት አመት አዛውንት ናቸው። ከዚህ እድሜያቸው ውስጥ የወያኔ/ኢህአዴግ መንግስት ባፈላማ ይዟቸው ሃያ አምስቱን አመታት ባለም በቃኝና ወህኒ ቤቶች ቀርጧቸዋል። ከዚህ ውስጥ ባመክሮ ጥቂት አመታት አራግፈው አስራ ስድስት አመት ከስምንት ወራት በህሊና እስረኝነት አሳልፈዋል።