በጋሻው ደሳለኝ በይቅርታ ሚዛን ተመዘነ÷ ቀልሎም ተገኘ – ምእመኑን አስቆጣ አባቶችን አሳዘነ! የ‹ፀጉራሙ በግ› ታሪክ በሐዋሳ ተደገመ

Hawassa St. Gabriel Church

የሐዋሳ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም

  • ‹‹በነበረው ሒደት በተለያየ ምክንያት የበደላችኹንን ኹሉ ይቅር ብለናችኋል›› (በጋሻው ደሳለኝ፣ ኅዳር ፳፱ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም.፤ ለሐዋሳ ደ/ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ምእመናን የተናገረው)
  • ‹‹ይኼ ጉልበት ላይ መውደቅ፣ ይቅርታ መጠየቅ በፍጹም እንዳያደርገው፡፡ ጉልበት ላይ መውደቅ፣ ይቅርታ መጠየቅ ማለት ጥፋተኛ ነኝ፤ ተሸማቅቄ እኖራለኹኝ ማለት ነው፤››   (በጋሻው ደሳለኝ፣ በግንቦት ፳፻፬ ዓ.ም. የክብረ መንግሥት ግብረ አበሮቹን ሲመክር)
  • ይቅርታ ጠያቂ ሳይኾን ይቅርታ አድራጊ እና ይቅር ባይ መስሎ በቀረበው የበጋሻው ደሳለኝ የእብሪት አነጋገር ያዘኑት አቡነ ገብርኤል እና አቡነ ሉቃስ ምእመኑን ይቅርታ ጠይቀዋል፤ ብፁዕ አቡነ ማትያስ ‹‹አለመማር የሚያመጣው በሽታ ነው፤ ያሳዝናል›› ብለዋል፡፡
  • በነሳሒነት የማያምነው በጋሻው ደሳለኝ፣ በሐዋሳው የዕርቀ ሰላም ስምምነት አጋጣሚ ቀልሎ የተገኘበት ሚዛን ያለቀኖናዊ ምርመራ በዕርቅ ሰበብ ወደ አገልግሎት እንዲመለስ የተሯሯጡለት እነወ/ሮ ፋንቱ ወልዴም አካሄዳቸውን እንዲመረምሩ አስገዳጅ ኹኔታ የሚፈጥር ነው ተብሏል፡፡
  • የሐዋሳ ቅ/ገብርኤል ምእመናን የዕርቀ ሰላም ሥነ ሥርዐት የቅ/ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በሠየማቸው ልኡካን ተከናውኗል፤ ለዕርቀ ሰላሙ ዕውቅና እንዲሰጥና ለስምምነቱ መከበር ጥንቃቄ እንዲደረግ ተጠይቋል፡፡

ተጨማሪ መረጃዎችን ይከታተሉ