የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር IOM ILO እና UN Human Rights Commissionሀላፊዎች ጋር በሳውዲ ስለሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ጉዳይ ላይ ሰፊ ውይይቶችን አደረጉ

SHARE:

የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ፓርቲውን በአውሮፓ እና በአሜሪካ የማስተዋወቅ ስራቸውን ቀጥለው በዛሬው እለት በስዊዘርላንድ ጀኔቫ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኢትዮጵያዊያን በሳውዲ መንግስት ላይ በሚያደርጉት ተቃውሞ ሰልፍ ላይ በመገኘት መልእክት አስተላልፈዋል፡፡ ከሰልፉም መጠናቀቅ በኋላ ከአለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት( IOM ) ከአለምአቀፍ የሰራተኞች ድርጅት (ILO) እና ከተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ( UN Human Rights Commission) ሀላፊዎች ጋር በሳውዲ ስለሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ጉዳይላይ ሰፊ ውይይቶችን አድርገዋል፡፡ በነገው እለትም በጂኔቫ የመሸኛ የእራት ፕሮግራም የተዘጋጀላቸው ሲሆን ቅዳሜም ወደ ሆላንድ አምስተርዳም በመብረር እዛ ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ማህበረሰብ ጋር ውይይት ያደርጋሉ፡፡