የኑሮ ውድነት 40% ይጨምራል የሚል ጥናት ለጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ ቀረበ:: በሃገሪቱ የኢኮኖሚ ውንብድና ተስፋፍቷል::
የኑሮ ውድነት 40% ይጨምራል የሚል ጥናት ለጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ ቀረበ::
በሃገሪቱ የኢኮኖሚ ውንብድና ተስፋፍቷል::
የስራ አጦች መስፋፋት ሃገሪቱን የወንጀል መናኸሪያ እያደረጋት ነው::
የኢሕኣዴግ ኢኮኖሚስቶች በወረደላቸው መመሪያ በጋራ እና በተናጠል ባደረጉት ጥናት መሰረት በአገሪቱ በተለይ በከተሞች አከባቢ የኑሮ ውድነት በ40% ይጨምራል ሲሉ ለጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት የፖሊሲ ጥናት ቡድን የጥናት ሪፖርታቸውን ያቀረቡ መሆኑን የውስጥ አዋቂ ምንጮች ተናግረዋል::
የጥናት ሪፖርቱን ያቀረቡት የወያኔው ኤክስፐርቶች መንግስት የኢኮኖሚ ፖሊሲ በድጋሚ እንዲፈተሽ እና ማሻሻያዎች እንዲደረጉ ሲያሳውቁ በአገሪቱ የተንሰራፋው የሙስና እንቅስቃሴ ዋነኛው የኢኮኖሚው ማነቆ ከመሆኑም በላይ የፍትህ እና የንግድ ስርኣቱ መላሸቅ የኢኮኖሚ ቁጥጥሩን ስላላው ለዋጋ ንረቱ መንስኤ ናቸው ብለዋል::መንግስት ለግሉ ዘርፍ ያለው አመለካከት ደካማ መሆኑ እና ከፖለቲካ ባለስልጣናት ጋር ቁርኝት ያላቸው ነጋዴዎች ለመክበር የሚያደርጉት ሩጫ የህዝቡን የኑሮ ውድነት ጣራ እንዲነካ አድርገውታል::እንዲሁም የኢኮኖሚ ውንብድና በሃገሪቱ ላይ እየተፈጸመ ነው::የስራ አጦች ቁጥር መጨመር ሃገሪቱን የወንጀለኞች መናኸሪያ እያደረጋት ነው::
በአላቂ እቃዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ንረት ይከሰታል በሃገር ውስጥ ምርቶች ላይም ከፍተኛ የሆነ ጭማሪ በሚቀጥለው አንድ አመት ይመጣል ያለው ጥናት የግሉ አምራች ዘርፍ ጥሬ እቃዎችን ወደ ሃገር ውስጥ በሚያስገባበት ጊዜ የተወሰነ የቀረጥ ክፍያ አለመኖሩ እና የመንግስት ባለስልጣናት እንዳሰኛቸው በየጊዜው እየቀያየሩ የህገር ውስጥ ምርቶች እንዲጎዱ የማኑፋክቸሪውም ዘርፍ እንዲዳከም በማድረግ ችግር እንዲፈጠር አድርገዋል::
ጥናቱ የባንኮችን መዳከም የስራ አጥነትን የስደትን የፖለቲካ ተጽእኖን የህዝቡን አስተያየት እና የገበሬውን ምሬት አጠቃሎ የያዘ መሆኑ የጠቆሙት ምንጮቹ መንግስት በሞኖፖል ንግዱን ይዞታል የውጪ ዜጎች ህገወጥ የኢኮኖሚ ስርኣት ዘርግተዋል ከፍተኛ ብዝበዛ በሃገሪቱ ምጣኔ ሃብት ላይ እየተደረገ ነው የሚሉ ዝርዝር ጥናቱን አቅርቧል:: ጥናቱ ይፋ ለውይይት ይቅረብ አይቅረብ የሚለው ገና ያልተወሰነ ሲሆን የጥናቱን ዝርዝር መረጃው ከምንጮቻችን እንደደረሰን የምናቀርበው መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን::