የኢትዮጵያ ቴሌኮም አገልግሎቱ በሌቦች እንደሚደፈር ገለፀ

ገቢዬን ከሌቦች ጋር እየተጋራሁ ነው ሲል ያማረረው ኢትዮ-ቴሌኮም በተለይ ከውጭ ሃገር ወደ ኢትዮጵያ የሚደወሉት ስልኮች በሕገ ወጦች በኩል የሚያልፉበት ሁኔታ መኖሩን አስታውቋል።

ከውጭ ሀገር በሚደወሉ ስልኮች ላይ የጥራት ችግር የሚያጋጥመውም በዚሁ የተነሣ መሆኑን የኢትዮ-ቴሌኮም የኮርፖሬት ኮምዩኒኬሽንስ ሥራ አስኪያጅ አቶ አብዱራሂም አህመድ ለአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ አብራርተዋል።

አቶ አብዱራሂምን ያነጋገራቸው እስክንድር ፍሬው ያጠናቀረውን ዘገባ የያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡