ፓትርያርኩ: ወደ ኋላ ለማይመለሰው የተቋማዊ ለውጥ አደረጃጀትና አሠራር አገልጋዩ የለውጥ ሐዋርያ እንዲኾን አሳሰቡ፤ የሥራ ጊዜያቸው ያበቃውን ተጠባባቂ ሥራ አስኪያጅ ‹‹በዘላቂነት እናስቀጥላለን›› በሚል ጥቅመኝነት የተሳሰሩ ጎጠኛና ሙሰኛ የተቋማዊ ለውጥ ተቃዋሚዎች በፓትርያርኩና በረዳት ሊቀ ጳጳሱ መካከል ክፍተት ለመፍጠር እያሤሩ ነው admin November 27, 2013 Tagged with Amharic, amharic news, Ethiopia, ethiopian news in amharic, Ethiopians, News in Amharic ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ በጥናታዊ የውይይት መርሐ ግብሩ ላይ ተገኝተው ቃለ ምዕዳን በሰጡበት ወቅት (ፎቶ: የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት) የለውጡ ቀንደኛ ተገዳዳሪዎች፣ ‹‹ጠላቶች ነበርን፤ ዛሬ የሰማነውና ያየነው ጥናት ግን መልካም ኾኖ አግኝተነዋል፤›› ሲሉ ራሳቸውን ሒስ አድርገዋል፤ ‹‹ቤተ ክርስቲያኒቱ የተወለደችው ዛሬ ነው፤›› ሲሉም የመዋቅርና አሠራር መመሪያ ጥናቱን አድንቀዋል፤ ጥናታዊ ውይይቱ በላቀ የለውጥ መነሣሣት ቀጥሏል፤ ከፍተኛ አመራሩ የተሳተፈበት የቀዳማይ ዙር ጥናታዊ ውይይት መርሐ ግብር ዛሬ ይጠናቀቃል፡፡