የጋራ ላይ ፉጨት!! //ደመቀ ከበደ – ጣና ዳር//
የጋራ ላይ ፉጨት!!
//ደመቀ ከበደ - ጣና ዳር//
‹‹ሀበሽ አባ ደፋር - አባ ሰው አይፈሬ
ጫማ የለም ከእግሩ - ተሰርቶ ጎፈሬ፤
ሀበሽ አባ ሞጋች - አባ ጎበዝ ጤፉ
ጋራ ላይ ያቅራራል - በጎቹ ሲጠፉ››
የሚሉት ቀረርቶ - የሚሉት ሽለላ
ስንት ወንድ ገደለ - ስንት ጎበዝ በላ፤
‹‹ደፋር ነው እያሉ - ጀግና ነው እያሉ
የሞት ሞቱን ሲሞት - ዳር ቆመው ያያሉ፤
ተውት ይሄን ሶታ - ይሄንን ጠንበለል
ጀግና ነህ አትበሉት - እንዲያው ይንጎማለል፤››
የሚሉት የእናት ወግ - የአባት ማስፈራሪያ
ስንት ወንድ አከሸፈ - እንደ ዘመን ድሪያ፤
እኔ ግን እላለሁ፤
ተውት ይኸን ጀግና - ይውጣ ወደ ጋራ
ይሸልል ይፎክር - እንዳሻው ያቅራራ
እንዳሻው ‹‹ቡ!›› ይበል - ያሻውን ይጣራ
ሰው እንዴት ይኖራል - እያየ መከራ!!
//ደመቀ ከበደ - ጣና ዳር//
‹‹ሀበሽ አባ ደፋር - አባ ሰው አይፈሬ
ጫማ የለም ከእግሩ - ተሰርቶ ጎፈሬ፤
ሀበሽ አባ ሞጋች - አባ ጎበዝ ጤፉ
ጋራ ላይ ያቅራራል - በጎቹ ሲጠፉ››
የሚሉት ቀረርቶ - የሚሉት ሽለላ
ስንት ወንድ ገደለ - ስንት ጎበዝ በላ፤
‹‹ደፋር ነው እያሉ - ጀግና ነው እያሉ
የሞት ሞቱን ሲሞት - ዳር ቆመው ያያሉ፤
ተውት ይሄን ሶታ - ይሄንን ጠንበለል
ጀግና ነህ አትበሉት - እንዲያው ይንጎማለል፤››
የሚሉት የእናት ወግ - የአባት ማስፈራሪያ
ስንት ወንድ አከሸፈ - እንደ ዘመን ድሪያ፤
እኔ ግን እላለሁ፤
ተውት ይኸን ጀግና - ይውጣ ወደ ጋራ
ይሸልል ይፎክር - እንዳሻው ያቅራራ
እንዳሻው ‹‹ቡ!›› ይበል - ያሻውን ይጣራ
ሰው እንዴት ይኖራል - እያየ መከራ!!