ዝክረ ፕሮፌሰር ታደሰ ታምራትና ፕሮፌሰር ዶናልድ ክራሚ
በኢትዮጵያ ታሪክ ጥናት ታላቅ ቦታ ያላቸውን ፕሮፌሰር ታደሰ ታምራትንና ፕሮፌሰር ዶናልድ ክራሚን ለማሰብ ሰኞ ጥቅምት 18 ቀን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ራስ መኮንን አዳራሽ መርሐ ግብር ተዘጋጅቶ ነበር፡፡ በወቅቱ የሁለቱም ደቀ መዝሙር የነበረው ዶ/ር ውዱ ጣፈጠ ያቀረበውን ማስታወሻ እንብቡት፡፡
ዝክረ ፕሮፌሰር ታደሰ ታምራትና ፕሮፌሰር ዶናልድ ክራሚ
ዉዱ ጣፈጠ( ዶ/ር)
ከተማሪዎቻቸው አንዱ
ፕሮፌሰር ታደሰ ታምራትና ፕሮፌሰር ዶናልድ ክራሚ ሁለቱ በዩነቨርስቲ የትምህርት ቆይታዬና ብሎም በህይወቴ ላይ ቀና ተፅእኖ ያሳደሩ ታላቅ መምህሮቼ ነበሩ፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ውስጥ የቅድመ-ምረቃ የታሪክ የአራተኛ ዓመት ተማሪ በነበርኩበት ጊዜ ከፕሮፌሰር ታደሰ ጋር የመጀመሪያን ትውውቅ አደረግን፡፡ ለቅድመ ምረቃ (ለቢ.ኤ.) ዲግሪ ማóማóያ የምረቃ Òሁፍ ምርምር ለማድረግና ውጤቱንም ለመፃፍ እንድችል እርሳቸው አማካሪዬ ሁነው ተመድበው ነበር፡፡ በወቅቱ እርሳቸው የማህበራዊ ሳይንስ ኮሌጅ ዲን ስለነበሩ እርሳቸውን አግኝቶ ለማነጋገር ትንሸ ችግር ፈጥሮብኝ ነበር፡፡ ከትንሸ መመላለስ በኋላ አግኝቸ ራሴን ሳስተዋውቅ ትኩር ብለው እየተመለከቱ በርጋታ አዳመጡኝ፡፡ ከዚያም እስኪ ወደ ሌላ ነገር ከመግባታችን በፊት የራስህን ታሪክ፤ የቤተሰብህን፤የአስተዳደግህንና የትምህርትህን ነገር ግለፅኝ ብለው ጠየቁኝ፡፡ በጊዜው ይህ ሁሉ ምን ያደርጋል ብየ በየዋህነት ራሴን ጠይቄ ነበር፡፡ የርሳቸው አካሄድ የገባኝ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ነበር፡፡
ለቅድመ ምረቃ የምርምር ስራ የሰራሁበት ርእስ ስለ ራጉኤል አብያተ ክርስቲያናት ታሪክ ነበር – እንጦጦና አዲስ አበባ መርካቶ ስለሚገኙት መንትያ አብያተ ክርስቲያናት፡፡ ፕሮፌሰር ታደሰ በጣም ረጋ ያሉ፤ በተመስጦ የሚያዳምጡ፤ ቀስ ብለው የሚናገሩና እንዲህ አይነቶቹን ዋና ዋና ፍሬ ነገሮች አስተውለሀዋል ብለው በማስታወሰ መንገድ የሚያሳዩ ነበሩ፡፡ በዜያ ጊዜ እኔን ለመሰለው ገና ጀማሪ በማበረታታትና በሚቀጥለው ጊዜ ስንገናኝ አዲስ መረጃ እንደምታመጣ ተስፋ አለኝ ብለው የሚሸኙ ነበሩ፡፡ የሚያውቁትን መረጃ ጠቅሰው ፈልግ የሚሉ፤ መረጃ ሊሰጡ የሚችሉና ያውቃሉ ብለው የሚገምቷቸውን ሰዎችን ስም የሚነግሩና ሲቻልም የሚያስተዋውቁ ነበሩ፡፡
በዚያ ጊዜ እጅግ ያስቸገረኝ ነገር ቢኖር ጽሕፈታቸውን ማንበቡ ነበር፡፡ ይህም ቢሆን ዲኑ ቢሮ ትሰራ የነበረች ወ/ሮ እልፍነሽ እንዳለ ተረር አድርጋ እያነበበች ችግሬን ታቃልልኝ ነበር፡፡ ብዙ ጊዜ አብራቸው ስለሰራች ጽህፈታቸውን ያለችግር ማንበብ ችላ ነበርና፡፡
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የመቀጠር እድል ባጋጠመኝ ወቅት ሁል ጊዜ ያለማቋረጥ ድጋፋቸውንና አበረታች ቃላቸውን ያለ ምንም ስስት ይነግሩኝ ነበር፡፡ ይህም የታሪክ ትምህርት ክፍል በርሳቸው ስር ሆኘ ምክራቸውን እጠየቅሁ እንዳነብና ልምድ እንዳገኝ መድቦኝ ነበርና፡፡ የመካከለኛውን ዘመን የኢትዮጵያ ታሪክ ለማጥናት የሚረዳኝን የግእዝ ቋንቋ ትምህርት ሁለት ኮርስ እንድወስድ አበረታቱኝ፡፡ በጊዜው ኮርሱን ይሰጡ ለነበሩት ለዶ/ር አምሳሉ አክሊሉ አስተዋወቁኝ፡፡ ብዙ አልገፋሁበትም እንጅ የፈረንሳይኛና የጣሊያንኛ ቋንቋ ትምህርት እንድማር አበረታተውኝ ነበር፡፡
ቀጥሎም የታሪክ የማስትሬት ትምህርት በምማርበት ጊዜ ትልቅ ድጋፍ በማድረግ የተለመደ የማማከር ሀላፊነታቸውን ተወጥተዋል፡፡ ለዚህ ዲግሪ ማóማóያ የምርምር ጥናቴ ርእስ የነበረው የዋግና የላስታ ታሪክ የሚል ነበር፡፡ እርሳቸው እንደነገሩኝም የላስታ መሪዎች የዛጉዌን ታሪክ ለመፃፍ እቅዳቸው እንደነበርና ይህንን ታሪክ ለመፃፍ በማሰቤ፤ የትምህርት ክፍሉም ሆነ እርሳቸው ሰለገፋፉኝ፤ በመቀበሌ ደስ እንዳላቸው ገልፀውልኛል፡፡
የምሰራበት የታሪክ ዘመን ራቅ ያለ በመሆኑና ታሪኩን ለማያያዝና መስመር የያዘ የታሪክ ዳራ እንዲኖረው ለማድረግ ያለ መሰልቸት ይመክሩኝ ነበር፡፡ ከሁሉም በላይ ስራየ ደከም ያለ ሲመስላቸው በራሳቸው ፅፈው ይህንን ጨምረው እያሉ ታሪኩ ወጥነት ኖሮት እንዲተረክ እጅግ ለፍተዋል፡፡ በምሳ ሰአት ጭምር ቁጭ ብለው እያረሙና እያስተካከሉ ይህ ነው ተብሎ የማይገለጽ ድካም አሳልፈዋል፡፡ በዚያ ጊዜ የማስተርስ ድግሪ ትምህርት አራት አመት ይወስድ ስለነበር የማስረከብያ ጊዜው እንዳያልፍብኝ ብለው አሜሪካን አገር ትኖር የነበረች የልጃቸውን የቀለበት ቀን በኔ ምክንያት ሳይሳተፉ ቀርተዋል፡፡ “ችግር የለም አንተም ልጄ ነህ እንዳሉኝ” አስታውሳለሁ፡፡ በ|ላም በአሉ እዚህም ተከበረ፡፡
በተለይም ደግሞ የታሪክ የዶክተሬት ትምህርት እንድማር በማሰብ፤ ለሌሎች እንዳደረጉት ሁሉ፤ እኔንም ከÝሮፌሰር ክራሚ ጋር አስተዋወቁኝ፡፡ በ1991 —.ም. ወደ ኢሊኖይ ዩኒßርስቲ – ኧúርባና aምፔይን – በሄድኩ ጊዜ Ýሮፌሰር ክራሚ እንደ Ýሮፌሰር ታደሰ ሁሉ አገሩን በማስተዋወቅ፤ በማበረታታት፤ የሚቸግረኝን ነገር ሁሉ በማደረግ ትልቅ ድጋፍ አድርጎልኛል፡፡ እኔ በሄድኩበት አመት ከኬንያ የመጣውን ሌላ ተማሪ አይሮፕላን ጣቢያ ድረስ በመሄድ ተቀበለው፡፡ እኔንም እንደዚሁ፡፡ ሁለታችንም እቤቱ ወስዶ አሳረፈን፤ አስተናገደን፡፡ ቤት ተከራይተን ራሳችንን እስክንችል ድረስ ለሳምንት ያክል እቤቱ ተቀመጥን፡፡ እንግድነት በጣም ሳይሰማንና ተሳቀንም በችኮላ ቤት እድንከራይ ሳንሆን፡፡ አሜሪካ በደረስኩበት ጊዜ ምንም ገንዘብ አልነበረኝምና ገንዘብ እስካገኝ ድረስ ቤቱ እንድቀመጥ ጋብዞኝ ነበር፡፡ በተለይም ባለቤቱ ሚስ ሎሬይን ክራሚን እንደ እናት ነበር የምንመለከታት፡፡
አገርን ለቅቆ፤ ባህርን ተaግሮ በሌላ አገር መኖር የሀገርና የወገን ናፍቆት አስቸጋሪ ቢሆንም በአመት በአል ቀናት ማለትም የአሜሪካን የምስጋና ቀን፤ ገናና፤ ፋሲካ በደረሰ ቁጥር Ýሮፌሰር ክራሚ ቤት እየተጋበዝን በአላቸውን በአል አድርገን ውለናል፡፡ ምናልባት በአጋጣሚ በከተማው ካልኖሩ በስተቀር፡፡ በእነዚህ በአላት ሌላ ከተማ የሚኖሩ ልጆቹና ¹ደኞቹ ስለሚሰባሰቡ በአላቸውን ደመቅ አድርገን ተደስተን አብረን አሳልፈናል፡፡ የኢትዮÉያ ቡና ተፈልቶ፤ የኢትዮÉያ ቱሪስት አስጎብኚ ድርጅት በሰራቸው የንግስተ ሳባ ስእል ባላቸውና በሚያማምሩት የቡና ስኒዎች አገራችን ያለን እስኪመስለን ድረስ ተጋብዘናል፡፡ ቢራና ወይንም ተጎንጭተናል፡፡
በዩኒቨርስቲው የትምህርት መርሀ ግብርና ሌሎች ችግሮች በተከሰቱ ቁጥር እንደ አባታችንና እናታችን ቤት ሳንሳቀቅና ሳንፈራ ቢሮው ሄደን የገጠመንን ችግር አማክረን መፍትሄ አግኝተናል፡፡ በተቻለው ጊዜ ሁሉ እኛን ለማረጋጋትና ችግራችንን ለማቃለል ከልቡ ጥ[ል፡፡ አንዳንዴም ንዴታችንን ለማስረሳት ቢራ እየጋበዘ፡፡ ያውም ከሚያውቃቸው አንዳንድ ቀልዶች ጋር እያዋዛ፡፡ “ባርባ አራቱ የጎንደር ታቦታት’ እና ‘ነው እንዴ” ከሚሉ ሀገርኛ ቀልዶች ጋር፡፡
በዚሁ የአሜሪካ ቆይታየም Ýሮፌሰር ታደሰም እዚያው ስለነበሩ የሁለቱ አማካሪዎቼና መምህሮቼ በአንድ ከተማ መገኘት ለአኔ ጥሩ አጋጣሚ ነበር፡፡ የዶክተሬት ዲግሪ ማóማóያ የጥናት ሰራየ በኢትዮÉያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ላይ ስለነበር በቂ የሆነ ድጋፍና ምክር ለማግኘት ችያለሁ፡፡ ቀደም ብሎ ሁለቱ መምህሮቼና Ýሮፌሰር ሁሴን በኢትዮÉያ የሀይማኖት ጉዳዮች ላይ ምርምር ለማደረግ እቅድ ስለነበራቸው፤ እኔም በዚሁ እቅድ ውስጥ ተካትቸ ስለነበርና፤ የጥናት ርእሴም የዚሁ አካል ስለነበር የሁለቱ መምህሮቼ ድጋፍ አልተለየኝም ነበር፡፡
ከሁለቱ መምህሮቼ ጋር የነበረኝ ቅርርብ በምርምር ስራ ላይ ብቻ የተወሰነ አልነበረም፡፡ ቤተሰባዊ ጭምር እንጅ፡፡ የÝሮፌሰር ታደሰ ሁለት ሴት ልጆች – ህይወቴና ህሊና ታደሰ – የቀለበት ስነ-ስርአታቸውን በተለያየ ወቅት ባደረጉ ጊዜ መጋበዝ ብuሳይሆን እኔም ሆንኩ የታሪክ ትምህርት ክፍል አባሎች እንደ ቤተሰብ አባል ንቁ ተሳታፊ ነበርን፡፡ ምንም ጊዜ የማይረሳኝና ምን ያህል Ýሮፌሰር ታደሰ እንደሚያቀርቡኝ የተረዳሁት በጊዜው ¹ደኛየ የነበረችውን ያሁኗን ባለቤቴን ይŸት እንድገኝ በጋበዙኝ ጊዜ ነበር፡፡ እር]óን በአካል አያውkትም ነበር፡፡ ነገር ግን መጠየቅ ይወዳሉና በማስተርስ ዲግሪ ማóማóያ Îሁፌ ውስጥ ስማóን አይተው ጠይቀውኝ ነበርና አስረዳሁዋቸው፡፡ ታዲያ የግብŸ ጥሪ ወረቀት ሲሰጡኝ “¹ደኛህን ትተሀት እዳትመጣ፡፡ ልብ በል እር]ó ካልመጣች እዳትመጣ” ያሉኝ ነበር፡፡ የቀለበቱን ስነ-ስርአት አንስተን ባወራንቁጥር እኔና ዶ/ር አበበ ፍስሀ የተጫወታችሁት አይረሳኝም ይሉ ነበር፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን በተለያዩ ጊዜያት ከውጭ ለመጡ ቀደምት ¹ደኞቻቸው ግብŸ ባደረጉ ጊዜ እኔና የአሁኗ ባለቤቴ ተጋብዘን የባለቤታቸውን የወ/ሮ አልማዝን የተዋጣ የባልትና ሞያ ተkድሰናል፡፡
Ýሮፌሰር ክራሚ የ60ኛ አመት የልደት በአሉን ባከበረበት ጊዜ በወዳጅነት ተጠርተን ተጋብዘን ነበር፡፡ ከባለቤቴ ጋር ምን እንስጠው ተባብለን ተመካከርንና ወይን እንግዛለት ተባባልን፡፡ መቸም የተማሪ አቅም ነው ብለን አነስ ያለች የጣሊያን ወይን ወሰድንለት፡፡ ከጥቂት ቀናት በ|ላ በÑፈልኝ ማስታወሻ ሌሎች ለልደቴ ከላኩልኝ ነገር ሁሉ እንደናንተ የሚጥም ወይን ያመጣልኝ የለም የሚል ቃል ነበረው፡፡
በጉዞ ላይ ምንጊዜም መምህራችን ከማለዳ ጅምረው እያጫወቱን እን¹ዘለን፡፡ በማንኛውም ጉዳይ ላይ በርከት ያሉ ቀልዶችና ወጣቶች የሚያወሩትን ወሬ ሁሉ እያወጉ ያስቁናል፡፡ ከአራት ሰአት በ|ላ “እንግዲህ የኔን ጨረስኩ፤ በሉ አሁን ደግሞ የናንተን አምጡ” ይሉንና ከዚያ በ|ላ ተራቸውን አድማጭ ይሆናሉ፡፡ እኛም ምንም ሳንፈራ ማንኛውንም ነገር እናወራለን፡፡ ሀብታይ ዘራይ የተባለ ወፈር ያለ ተማሪ ከ|ላቸው ይቀመጥ ነበርና አጫጭሮቹን አላሳይ ብሎ ሲከልላቸው ጊዜ “መገዘዝ ዘወር በል አጫጭሮቹን ልይበት” እያሉ ያስቁን ነበር፡፡ መገዘዝ ቡልጋ ውስጥ የሚገኝ ግዙፍ ተራራ ነው፡፡ ከወራት በ|ላ የማጠቃለያ ስራየን ጽፌ ስሰጣቸው በአጋጣሚ ቡልጋን መÍፍ ረሳሁት፡፡ ቡልጋ ደግሞ የርሳቸው አገር ነው፡፡ ቁም ነገር መርሳቴን ለመግለጽ ‘poor Bulga ምስኪኗ ቡልጋ’ ብለው ስህተቴን በቀልድ አዋዝተው አስገረሙኝ፡፡
ከቀን ጉዞአችን በ|ላ ማታ ወደ ማደሪያችን ስንመለስ ሁልጊዜም ቅድሚያ የሚሰጡት ስልክ ደውለው ባለቤታቸውን ማነጋግር ነበር፡፡ ይህ ምንም ቢሆን የማይቀር፤ስልክ አይሰራም ካልተባለ፤ በቀር የምይዘነጋ የእለቱ ስራ ነበር፡፡ እውነትም Ýሮፌሰር ሽፈራውእንዳለው “ምሳሌ ሊሆኑ የሚገባቸው አፍቃሪ ባል” ነበሩ፡፡ በ1990 —.ም. ለ13ኛው የኢትዮጵያ ጥናት ጉበኤ ወደ ቶክዮ፤ ጃፓን፤ በሄድንበት ጊዜ Ýሮፌሰር ባህሩ የጋበዘንን ውስኪ አንድ ምሽት እየጠጣን እንዴት የትዳር ¹ደኛችሁን እንደተዋወቃችሁ አውሩ ተባለ፡፡ መጀመሪያ በእድሜ የምናንሰው አወራንና ቀጥሎ ደግሞ ትላልቆቹ አጫወቱን፡፡ በመጨረሻም Ýሮፌሰር ታደሰ ከባለቤታቸው ጋር እንዴት እንደተዋወቁ ሲያወሩን ፍቅር እስከ መቃብርን የሚወዳደር የፍቅር ጥምረት፤ እውነተኛና አስገራሚ ታሪክ ነበር፡፡ Ýሮፌሰር ታደሰና ወ/ሮ አልማዝ ፍቅራቸው እንደÐናና እንደ ደመቀ አብረው በፍቅር ኖረው አንድ አመት ባልሞላ የጊዜ ርቀት በሞት ተከታትለው አረፉ፡፡
ዶ/ር ተካልኝ እንደሚያጫውተን Ýሮፌሰር ታደሰ ተማሪዎቻቸውን ይዘው ወደ መስክ የምርምር ስራ በየአመቱ ሲወጡ በጣም የሚያቀርቡአቸው ተማሪዎች አሉአቸው፡፡ ቦርሳቸውን የሚይዝላቸው፡፡ እነዚህን ተማሪዎች ‘ዳዊት’ የሚል ስም ተማሪዎቹ ያወጡላቸዋል፡፡ የመንፈሳዊ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የመምህራቸውን ዳዊት ተሸክመው እንደሚከተሉ ሁሉ፡፡ ታዲያ ዶ/ር ተካልኝ አንድ ጊዜ ይህንን ለÝሮፌሰር ታደሰ ሲያጫውታቸው “ለዚህ ነበር እንዴ ጉሉማን ዳዊት ትሉት የነበር፤ እኔ እኮ እስካሁን አላወቅሁም ነበር” ብለው ሳቁና አሳቁን፡፡ ዶ/ር ጉልማ አሁን የሚኖረው አሜሪካን አገር ነው፡፡ እኔም በወቅቱ ዳዊት መባሌን አልሰማሁም እንጅ የአመቱ ዳዊት ነበርኩ ማለት ነው፡፡
Ýሮፌሰር ታደሰና Ýሮፌሰር ክራሚ ብዛት ያላቸውን የቅድመ ምረቃ፤ ማስተሬትና ዶክተሬት ተማሪዎች አማክረው አስመርቀዋል፡፡ ከድሮ ተማሪዎቻቸውም ጋር እንደ ስራ ባልደረባና እንደ ¹ደኛ ሁነው ብዙ ዘመናትን አሳልፈዋል፡፡ ተማሪዎቻቸውም እነዚህን የእወቀት አባቶቻቸውን አክብረው ኖረዋል፡፡ ሁለቱም ለንደን የዶክተሬት ድግሪ ተማሪ ከነበሩበት ጊዜ ጀምሮ በፍቅርና በመግባባት አብረው ሰርተዋል፤ ኖረዋልም፡፡ በሞትም ቢሆን ሁለት ወር ባልበለጠ ጊዜ በሞት ተከታትለው አልፈዋል፡፡ Ýሮፌሰር ታደሰ በግንቦት እንዲሁም Ýሮፌሰር ክራሜ በነሀሴ 2005 —.ም.፡፡ ሞት አይቀሬ ነውና ሞት አለያይቶአቸዋል፡፡ እግዚአብሄር ነፍሳቸውን በአብርሀምና በያ˜ቆብ ቦታ እንዲያሳርፍ እንመኛለን፡፡ ለቤተሰባቸውም መÒናናትን ይስጣቸው፡፡
ሰኞ፤ ጥቅምት 18/2006 —.ም.