የአንቶኒ ብሊንከን የአውሮጳ የጥድፊያ ጉብኝት አንደምታው ምንድን ነው?

በመጪው ጥር ከኃላፊነታቸው የሚሰናበሩት የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚንሥትር አንቶኒ ብሊንከን በዩክሬን ጉዳይ ከአውሮጳ መሪዎች ጋር ዛሬ ብራስልስ አስቸኳይ ውይይት አድርገዋል ። አንቶኒ ብሊንከን የአውሮጳ መሪዎችን እንዲህ በጥድፊያ ያነጋገሩት በዘንድሮ የአሜሪካ ምርጫ ያሸነፉት ዶናልድ ትራምፕ የፕሬዚደንትነት መንበረ-ሥልጣኑን ከመረከባቸው አስቀድሞ ነው ።