አራቱ ኃያላን – አዲስ መጽሐፍ – በቅርብ ቀን
click here for pdf
• በቅዱሳት መጻሕፍት ዕውቀትና በቤተ ክርስቲያን ትምህርት የበሰሉ፣
• ዘረኝነትንና ጠባብነትን እስከ መጨረሻው የተዋጉ፣
• የፍቅር መሥፈርታቸው ሰው መሆን ብቻ የሆነ፣
• ቤተ ክርስቲያን የቤተ መንግሥቱ ጥገኛና ተቀጽላ እንዳትሆን በብርቱ የተጋደሉ፣
• ለእምነታቸውና ለአቋማቸው ሲሉ ከነገሥታቱ ጋር ፊት ለፊት የተገዳደሩ፣
• ከእሳት፣ ከግርፋት፣ ከአራዊት፣ ከዘንዶ፣ ከግዞት፣ ከስደት ጋር ተጋፍጠው እምነታቸውን ያስከበሩ፣
• ነገሥታቱ በተሳሳተ መንገድ ሲሄዱ እንደ ዮሐንስ መጥምቅ ያለ ፍርሃት የገሰጹ፣
• በመላዋ ኢትዮጵያ ለስብከተ ወንጌል የተሠማሩ፣
• ቤተ መንግሥትን ለሥልጣንና ለጥቅም ሲሉ ከተጠጉ ሥጋውያን ካህናት ጋር በእምነትና በጽናት ያደረጉት ትግል፤
• ምንኩስና መንኖ ጥሪት(ሀብት ንብረትን መተው) ነው ብለው የተሰጣቸውን የማባበያ ገንዘብ፣ ወርቅና ርስት ላለመቀበልና ሃይማኖታዊ ነጻነታቸውን ለመጠበቅ ያደረጉት ተጋድሎ፣
(አቡነ በጸሎተ ሚካኤል፣ አቡነ ፊልጶስ፣ አቡነ አሮን፣ አቡነ አኖሬዎስ) ታሪክ
• ከበቂ ታሪካዊ ማብራሪያ፣ የፎቶ ግራፍና የሥዕል ማስረጃዎች፣ የቦታና የሰዎች ስሞች መዘርዝሮች ጋር፣
• የመካከለኛው ዘመን ኢትዮጵያ ሃይማኖታዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊና ባሕላዊ ታሪክ በሰፊው የተዳሰሰበት፣
ጠፍተው የነበሩ ቦታዎችን በአሠሣ በመፈለግ፣ የጠፉ መረጃዎችን ከየገዳማቱና አድባራቱ በማፈላለግ፣ በቀደምት ሊቃውንት የተጻፉትን በማጣቀስ፣ የተዘጋጀ የጥናት መጽሐፍ፣
በመጽሐፉ ውስጥ
• የአቡነ ተክለ ሃይማኖት፣ የአቡነ ኤዎስጣቴዎስ፣ የአቡነ ዜና ማርቆስ፣ የአቡነ ኢየሱስ ሞአ፣ የአቡነ መድኃኒነ እግዚእ፣
• በአሥራ ሁለት አህጉረ ስብከት ለስብከተ ወንጌል የተሠማሩት የአሥራ ሁለቱ ንቡራነ ዕድ ታሪክና የሥምሪት ሀገረ ስብከት በስፋት ቀርቧል፤
• በመካከለኛው ዘመን የመጀመሪያ አጋማሽ የኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ሰፊ ቦታ ያላቸው ግብጻውያን ጳጳሳት – የአቡነ ዮሐንስ፣ የአቡነ ያዕቆብ፣ የአቡነ ሰላማ መተርጉምና የአቡነ በርተሎሜዎስ ታሪክ ቀርቧል፤
• በደቡብ ኢትዮጵያና በኦሮሚያ ጥንት የነበሩትን የስብከተ ወንጌል እንቅስቃሴዎች ያሳያል፤
• አቡነ ፊልጶስ ዛሬ ስላለችው ቤተ ክርስቲያን ከ600 ዓመታት በፊት የተነበየውን ትንቢት ያዩበታል
ነገሥታቱና መኳንንቱ ሲያሳድዷቸውና መከራ ሲያበዙባቸው፤ ከነገሥታቱ ጋር የተጠጉ የቤተ መንግሥት ካህናትና መነኮሳት ሲያሳብቁባቸውና ተንኮል ሲሠሩባቸው፤ እግዚአብሔር ደግሞ ቅድስናቸውንና እምነታቸውን በተአምራት ሲገልጥላቸው ያያሉ፡፡
አራቱ ኃያላን – ከአሥራ አምስት ቀን በኋላ በገበያ ላይ ይውላል