ኢትዮጵያ ሌላ ባለአራት ቢሊየን ዶላር የኃይል ማመንጫ ሥራ ልትጀምር ነው

ሬይክያቪክ ጂዖ-ተርማል ​​ ኢትዮጵያ ሌላ ባለአራት ቢሊየን ዶላር የኃይል ማመንጫ ሥራ ልትጀምር ነው የኢትዮጵያ ጂዖ-ተርማል ኢነርጂ መገኛ የስምጥ ሸለቆ ክልል ​​የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ሬይክያቪክ ጂዖ-ተርማል ከሚባል ኩባንያ ጋር የኩርቤቲን የከርሰ-ምድር እንፋሎት ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ለማከናወን ውል ተፈራርሟል፡፡ ፕሮጀክቱ አራት ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ወይም ወደ ሰማንያ ቢሊዮን ብር እንደሚፈጅ ተገልጿል፡፡ ጂዖ-ተርማል ኢነርጂ ​​ ሬይክያቪክ ጂዖ-ተርማል በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ግዙፍ የውጭ ቀጥታ መዋዕለ ነዋይ እና የግል የኤሌክትሪክ ኃይል አመንጭ ኩባንያ መሆኑ ነው፡፡ ይህንንና ሌሎችም በተፈጥሮ አካባቢ፣ ሣይንስና ሕይወት ላይ የተቀናበሩ ዘገባዎችን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡