በሙሥና የተጠረጠሩ ክሥ ተመሠረተባቸው

በሙሥና የተጠረጠሩ ክሥ ተመሠረተባቸው
የኢትዮጵያ የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን አቃቢ ሕግ በሙስና የተጠረጠሩ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትና ዕውቅ ነጋዴዎች ላይ ትናንት ክሥ መሥርቷል።

በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አሥራ አምስተኛ የወንጀል ችሎት ትናንትና ዛሬ በዋለው ችሎት የቀድሞ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ ፈንታና ምክትላቸው የነበሩት የአቶ ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስ፣ የሃገር ውስጥ ደኅንነት ኃላፊ የነበሩት አቶ ወልደሥላሴ ወልደሚካኤል፣ እንዲሁም አንዳንድ ከፍተኛ ነጋዴዎች በሃገሪቱ ላይ በመቶዎች ሚሊዮን ብር የሚገመት ጉዳት በማድረስ ተከስሰዋል።

የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን በሦስት የተለያዩ መዝገቦች፤ ባጠቃላይ በአርባ ሁለት ተጠርጣሪዎች ላይ ከመቶ በላይ ክሦችን መመሥረቱ ታውቋል።

ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትና …