አፍሪካ ከአይሲሲ ጋር ያላት ግንኙነት

አረንጓዴ - የሮማ ደንብን ስምምነት ፈርመው በፓርላማዎቻቸው ያፀደቁ፤ ቢጫ - የሮማን ደንብ የፈረሙ ግን በፓርላማዎቻቸው ያላፀደቁ፤ ቀይ - የሮማን ደንብ ያልፈረሙና የአይሲሲ አባል ያልሆኑ ​​ አፍሪካ ከአይሲሲ ጋር ያላት ግንኙነት ሥራ ላይ ያሉ የሃገሮች መሪዎች እንዳይከሰሱ የሚያደርግ ከለላ ዓለምአቀፉ የወንጀል ችሎት - አይሲሲ እንዲሰጣቸውና በኬንያ መሪዎች ላይ የተከፈተው ክስም ላልተወሰነ ጊዜ እንዲዘገይ እንዲደረግም የአፍሪካ ሕብረት ሰሞኑን ጠይቋል፡፡ መሪዎቹ ባለፈው ቅዳሜ፣ ጥቅምት 2/2006 ዓ.ም አዲስ አበባ ላይ ባደረጉት ስብሰባ ጉዳዩን ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሚያቀርብና የሚከታተለ ኮሚቴ አቋቁመዋል፡፡ ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም /ፎቶ ፋይል/ በሌላ በኩል ደግሞ ይህ የመሪዎቹ ጥያቄ አግባብነት የሌለው ነው ሲሉ የፖለቲካ ሣይንስ ምሁር እና የሕግ ...