ሰበር ዜና – በምዕ. ወለጋ በቤተ ክርስቲያን ላይ በሚፈጸመው ግፍ ፓትርያርኩ መንግሥትን አሳሰቡ

  • የቅ/ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ጉዳዩን በጥብቅ ይነጋገርበታል
  • በመንግሥት ባለሥልጣናት ስለሚፈጸሙ በደሎች ከአህጉረ ስብከት የሚቀርቡ አቤቱታዎች የፍትሕ አካሉን አፋጣኝ ውሳኔ ያገኙ ዘንድ ቅ/ሲኖዶሱ ግፊት እንዲያደርግ አጠቃላይ ጉባኤው ዐደራ ጥሎበታል
  • አህጉረ ስብከት ያቀረቧቸውን የአስተዳደር፣ የፍትሕና የጸጥታ አካላት በደሎችና ተጽዕኖዎች አጣርቶ መፍትሔ የሚሰጥ÷ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት፣ ከሃይማኖት ተቋማት ጉባኤና ከፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር የተውጣጣ ኮሚቴ እንዲዋቀር አጠቃላይ ጉባኤው በአቋም መግለጫው ጠይቋል
  • ‹‹ይህ ዐይነቱ ጊዜ የማይሰጠው ችግር ወደ ሌላ ከመዛመቱ በፊት አፋጣኝ መፍትሔ ማግኘት አለበት፡፡›› /የ፴፪ው አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ የአቋም መግለጫና የውሳኔ ሐሳብ/
  • ‹‹ድርጊቱ የመቻቻልን ሕግ እያፈረሰ ነው፤ በአካባቢው ያለው መንግሥታዊ አስተዳደር ሊያስብበት ይገባል፡፡›› /ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ/