የአሜሪካን የበጀት ውዝግብና መዘዙ DW Amharic October 17, 2013 Tagged with Amharic, amharic news, Ethiopia, ethiopian news in amharic, Ethiopians, News in Amharic የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት የሃገሪቱን የበጀት ጣሪያ ከፍ ለማድረግ የሚያስችለውን ስምምነት ትናንት ማታ ካፀደቀ በኋላ ለ16 ቀናት የተዘጉት የተወሰኑ የፌደራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶች ዛሬ ሥራ ጀምረዋል ። የሃገሪቱ የበጀት ጣሪያ ከፍ እንዳይል ሲሟገቱ የቆዩት ወግ አጥባቂ ሪፐብሊካኖች ውሳኔውን ሊያስቀሩት ባለመቻላቸው ሽንፈታቸውን አምነዋል ።