የፕሬዝዳንት ትራምፕ የዩክሬንን ጦርነት የማስቆም ዕቅድ DW Amharic January 17, 2025 ተመራጭ ፕሬዝዳንት ትራም እራሳቸውም ሰኞ እለት ለአንድ ሜዲያ በሰጡት አስተያየት ፕሬዝዳንት ፑቲንም ከሳቸው ጋር መገናኛኘቱን እንደሚፈለጉትና ከሰኞው በዓለ ሹመት በሗላ እንደሚገናኙ ያላቸው እመነት በመግለጽ ይህ ሁለቱንም በተለይም ዩክሬንን እያወድመ ያለ ጦርነት ባስችኳይ መቆም እንድላበት እንደሚያምኑ አስታውቀዋል።