ይቺ ባንዲራ!
ተመስገንደሳለኝ
‹‹ተከብረሽ የኖርሽው በአባቶቻችን ደም
እናት ኢትዮጵያ የደፈረሽ ይውደም›› ማን ነበር ያቀነቀነው? …ብቻ ማንም ይሁን ማን፤ እኔም እደግመዋለሁ፡- ሀገሬን የደፈረ ይውደም!! …እነሆ ከፉከራው ወደ አጀንዳችን እንለፍ፡፡ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን፣ በሚቀጥለው ዓመት በብራዚል በሚካሄደው የዓለም የእግር ኳስ ዋንጫ ለመሳተፍ፣ ከናይጄሪያ ጋር የደርሶ መልስ ግጥሚያ ብቻ ቀርቶታል፡፡ በነገው ዕለትም የመጀመሪያውን ጨዋታ በአዲስ አበባ ያደርጋል፡፡ በዚህ ፅሁፍ የማነሳው ሃሳብም፣ ስለጨዋታው ሳይሆን፣ ጨዋታውን
የሚያደምቀው ሰንደቅ-ዓላማን (ባንዲራን) በተመለከተ ይሆናል፡፡