- በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ከሠላሳ ዓመታት በላይ አገልግለዋል
- ‹‹በጌቴ ሰማኔ፣ በጎልጎታ፣ በዴር አብርሃም ሁሉ ሰፊ ይዞታ እንዳለን በታሪክ ሰፍሯል፡፡ ግብር ለመገበር አቅም ስላነሰን ዴር አብርሃምን ግሪኮች ወሰዱብን፤ ቤተ ልሔም ያለውን ርስታችንን አርመኖች ወስደውታል፤ በዚያ ላይ ያለንን መረጃ በሙሉ ቀደም ሲል አርመንና ግብጾች ወስደው አጥፍተውታል፡፡››
- ‹‹ግብጾች በጣም ነው የሚከራከሩት፡፡ በዴር ሡልጣን ጉዳይ ግብጾች ያቋቋሙት ትልቅ ኮሚቴ አላቸው፡፡ ኢትዮጵያውያንም የእኛ ነው ካልን ዴር ሡልጣን ከእጃችን አይወጣም፡፡ ለዚህ ቦታ መርጃ የሚኾን አንዳንድ ፕሮጀክት መዘርጋት አስፈላጊ ኾኖ ሲገኝ ምእመናን እጃችኹን መዘርጋት ያስፈልጋል፡፡ ዴር ሡልጣን አለን ማለቱ ብቻውን በቂ አይኾንም፡፡››
- ‹‹ሕዝቡ ከገዳሙ ጎን ቆሞ፣ ገዳሞቻችን እንደ ሌሎቹ በልጽገው ፈጣሪ እንዲያሳየኝ ጸሎቴ ነው፡፡ የዴር ሡልጣን ክርክር ፍጻሜ አግኝቶ፣ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን መብቷ እስከ ኾነ ድረስ የኢትዮጵያ ምእመናን ለዴር ሡልጣን መርጃ እንዲኾን አስቦ እንደ ግብጾች አንድ ድርጅት አቋቁሞ ለዚያ ሒሳብ ተከፍቶ እንዳየው እመኛለኹ፡፡›› /ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ በ፲፱፻፺፮ ዓ.ም. ለጋዜጠኞች የተናገሩት/
ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ
(ከ1923 – 2006 ዓ.ም.)
