ኢህአዴግን እከስሳለሁ
ደራሲ፤ ዓለማየሁ ገላጋይ
ቅኝት፤ መስፍን ማሞ ተሰማ
መንደርደሪያ
ሰቀቀን ጭንቀታቸውን እንደ ተጋቦ የሚያጋቡ፤ ግፍና በደሉን ጠኔና ጣዕሩን እንደ ሾተል አሹለው፤ ከልብ የሚቸክሉ ከአእምሮ ጓዳ የሚቀብሩ፤ አዝነው የሚያሳዝኑ፤ ተቃጥለው የሚያሳርሩ…ፍትህ ተሟጋች፤ ነፃነት ተፋራጅ፤ ጧፍ ነዳጅ…ደራሲያን፤ ቀመረ ቃላት ጠቢባን…ቢኖሩም…የብዕር ትሩፋታቸው ጨለማን ተጋፍቶ ጨለማን ተዋግቶ የወጣው – ‘ኢምንቱ’ ነው። እነርሱም ቢሆኑ ታዲያ፤ በጨለማ እንደሚተኮስ ርችት ወጋጋናቸው አድማስ ካድመስ የሚያሳይ ብርሃን ሆኗልና፤ እሰየው!!