የሊቢያ ፀጥታና ጠቅላይ ሚንስትሯ

አጋቾች ኋላ ላይ እንዳስታወቁት ጠቅላይ ሚንስትሩን ያገቱት፥ ዩናይትድ ስቴትስ በ1990 የናይሮቢና የዳሬ-ሰላም ኤምባሲዎቿን ካጋዩ «አሸባሪዎች አንዱ» ያለችዉን አቡ አነስ አል ሊቢን ባለፈዉ ሳምንት ከሊቢያ አፍና ስትወስድ ጠቅላይ ሚንስትሩ ተባብረዋል በሚል ለመበቀል ነዉ።