ይሄ ነው የሚጮህለት ኢትዮጵያዊነት? ምን ነው በሞትኩ!

  • እስክንድር ነጋ ቢሰማ አንዱዓለም አራጌ ቃለ ኢሳይያስ አፈወቂ ቢያደምጥ አስችሏቸው ዝም ይሉ ነበር ወይ? ወደ እስር የተወረወሩበት ምክንያት የሰው አጥር ሲዘሉ ተይዘው እስካልሆኑ ድረስ ማለቴ ነው።
  • ሽግግር እንበለው ግርግር፣ ሰማያዊ እንበለው ምድራዊ፣ አንድነት እንበለው ልዩነት/ምቀኝነት፣ ጥምረት እንበለው ጭንቀት  በአጠቃላይ ሥልጣን ላይ የሚገኘው መንግሥት በመክሰስ የሚታወቁ የፖለቲካ ፓርቲዎቹና ጉጅሌዎችስ ምን አሉ? “በኤርትራ የሚኖሩ ኢሳይያስ አባታችን እንዳሉት እንዲሁ ነው ታሪካችን!” አሉ? ዝምታው ከዚህ አልፎ ሌላ ሊሆን አይችልም። እኔምለው ግን በቃ ይሄ ነው ዲሞክራሲ? ይሄ ነው ፍትሐዊነት? ይህች ናት በየኢምባሲው በር እንደ ብቅል የምንሰጣላት ኢትዮጵያ? ይሄ ነው ወይ ምላሳችን ከትናጋችን እስኪጣበቅ ድረስ የሚጮህለት ኢትዮጵያዊነት? ምን ነው በሞትኩ። ይህን ሳይሰሙ ያለፉ ኢትዮጵያውያን ፈጣሪያቸው እንዴት ቢወዳቸው ነው በጊዜ የሰበሰባቸው። ታድለው! በአማርኛ ቋንቋ ሲጻፍ፥ ወይ ተያይዘን እንለማለን ወይንም ደግሞ ተያይዘን እንጠፋለን። ይህ ትውልድ በእኩልነትና በፍትሐዊነት የሚያምን የራሱ የሆነ አመራርና አስተዳደር አጥብቆ ይሻል። ከዚህ ያለፈ “በጃንሆይ ዘመን አስር እንቁላል በአምስት ሳንቲም፣ ኩንታል ጤፍ በብር 25 ይሸጥና ይሸመት ነበር” የሚል ከቅርስነት አልፎ በዚህ አዲስ ትውልድ የፖለቲካ አስተዳደር ቦታ የለውም። …  አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከአውሮፓና ከአሜሪካ ድረስ የዘመተ በአስር ሺሕ የሚቆጠር ሠራዊት “አለን” አሉ። ደግ! እንደ አፋቸው ያርግላቸውና አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ይህ “አለኝ” የሚሉትን  ወታደር መርተው እግራቸውን ያነሱ ዕለት ግን አቶ አንዳርጋቸው በነፍስ ከተረፈ በቁሙ ውርደትን እንደሚያይ ቅንጣት ታክል አልጠራረርም። ሙሉ የጽሑፉ ይዘት ለማንበብ

http://salsaywoyane.wordpress.com/ ይጨቁኑ!

 

ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል

E-mail: [email protected]

Sep. 13, 2013