የአስተሳሰብ እንጅ የዓመት አዲስና አሮጌ የለውም!

በአዲስ ዓመት የኃይማኖት፣ የፖለቲካ አስተሳሰብ፣ የብሔር ልዩነትቶች፣ ድህነት፣ ሁከት፣ ጦርነት፣ ስደት፣ ምቀኝነት፣ ጭንቀትና ልመና ተወግደው ሰላም፣ ጤና፣ ህብረት፣ እኩልነት፣ ነጻነት፣ ብልጽግና፣ ዕድገት፣ ለውጥና ደስታ አዲስ ይሆንለት ዘንድ ተስፋ የማያደርግና የማይመኝ የለም። በምኞት የሚሆን ነገር የለም እንጅ ቢሆን እኔም ደስ ባለኝ። በእርግጥ  አዲስ መንፈስ/አዲስ ህልም አዲስ ዓመት እየተባለ ከሚከበረው በዓል ጋር ምንም ግኑኝነት የለውም። ይህ ብቻም አይደለም አርጅቶ የሚያልፍ አዲስ ሆኖ የሚወልድ ዘመን የለም። እንደ ሣር እንደ ዱር አበባም እንዲሁ አብቦ ነፋስ በነፈሰበት ጊዜም የሚያልፈው የሰው ልጅ ብቻ ነው (መዝሙረ ዳዊት 103፥ 15)።  ዓመት “ስለ ሄድ” ዓመት “ስለ ስለመጣ” የሚለወጥ አንዳች ነገር የለም። ቁልፉ/መፍትሔው ያለው ኮንትራታችን ጨርሰን እስክንሸበለል ድረስ አንዱን ‘እየሸኘን” ሌላውን “እየተቀበልን” በምንገኘው በእኔና በእናንተ እጅ ነው ያለው።  እውነቱን ለመናገር አንዱ እየተቀበለ አንዱን የሚሸኝ ዘመን እንጅ ሰው ዘመን ተቀብሎ ዘመንን አይሸንም። የአቅጣጫ ለውጥ ለማድረግ ቆርጠው የተነሱ እንደሆነ ከዓመት “መባቻ” ሆነ ከዓመት “መጨረሻ” ምንም የሚያገናኝ ዓመትም የምያስጠብቅ  አንዳች ምክንያት የለንም። አይመስሎትም?

እኔ እስከማቀው ድረስ ለበሽታቸው መድኃኒት ፍለጋ ወደ ቤተ ሳይዳ የማጥመቂያ ስፍራ ይወርዱና የውኃውን መንቀሳቀስ እየጠበቁ ይንቦጫረቁ የነበሩ የኢየሩሳሌም ዕውሮች፣ አንካሶች፣ ሰውነታቸውም የሰለለ ነው። የእርስዎስ? ከሰው በታች ያደረገን የአእምሮ ፈውስ ያስፈልገናል ነው የምሎት።

ሙሉ የጽሑፉ ይዘት ለማንበብ የሚቀጥለውን ሊንክ ይጫኑ 

http://salsaywoyane.wordpress.com/