የሃውልት ጉዳይ (ከተስፋዬ ገብረአብ)
ሰሞኑን “አዲስ ነገር – ድረገፅ” የለጠፋቸውን የዜና ጭማቂዎች ሳነብ ትኩረት የሚስብ ርእስ ገጠመኝ። ይህም ካርል ሄንዝ ለተባሉ ጀርመናዊ አዲሳባ ላይ ሃውልት ሊቆምላቸው የመወሰኑ ዜና ነበር።
ለመሆኑ እኒህ ሰው ማናቸው? ማነው የወሰነላቸው? በምን መለኪያ? ከማን ጋር ተወዳድረው? ለኢትዮጵያ ምን በጎ ቢሰሩ ይሆን፣ ለሃውልት የበቁት? የሚታወቅ ዝርዝር ነገር የለም።
ታሪካቸውን ለማንበብ ስሞክር፣ “ሰዎች ለሰዎች” የተሰኘ የበጎ አድራጎት ድርጅት መስርተው ብዙ ሰዎችን ህይወት ለውጠዋል ተባለ። የሰሩት መልካም ነው። ግን በመንግስት ደረጃ “እግዚአብሄር ይስጥልን” ቢባሉ አይበቃም?
በርግጥ መለስ ዜናዊ በጣም ያደንቃቸዋል። በመሆኑም ከሳር ቤት ወደ መካኒሳ በሚወስደው መንገድ ላይ አንድ አደባባይ ሸለማቸው። አደባባዩ ላይ የሚቆምላቸውን ሃውልት የመሰረት ድንጋይ ለማኖር ኩማ ደመቅሳ መታዘዙም ተዘግቦአል።
እንግዲህ ሌላ ያመለጠኝ ዜና ከሌለ በቀር፣ ኢህአዴግ በ20 አመታት ውስጥ እንዲገነቡ ካፀደቃቸው ሃውልቶች ውስጥ የካርል ሄንዝ 5ኛ መሆኑ ነው። ቀደም ሲል፣ የጄኔራል ሃየሎም፣ የአቡነ ጳውሎስና የአሉላ አባነጋ የተገነቡ ሲሆን፣ የአፄ ዮሃንስ በግንባታ ላይ መሆኑ ተሰምቶአል። ከቀዳሚዎቹ አራት ሃውልቶች አከራካሪው የአቡነ ጳውሎስ ብቻ ነው። 5ኛው ካርል ሄንዝ የሚያከራክር ሳይሆን የሚያስተዛዝብ ነው።
ሃውልቶች የአካባቢውን ህዝብ ስነልቦና ግምት ውስጥ ማስገባት አለባቸው። ለምሳሌ መለስ ዜናዊ የራሱን ሃውልት አዲሳባ ላይ ሊተክል አይችልም። ለመትከል ከወሰነ 24 ሰአት በታንክና በመትረየስ ማስጠበቅ አለበት። በመሰረቱ ግን በሃገር ደረጃ ሃውልት የሚተከልለት ሰው ማን መሆን እንዳለበት ጥናት ማድረግ ጠቃሚ ይመስለኛል። መለስ ስለፈቀደ ብቻ የተተከለ ሃውልት፣ የአካባቢው ህዝብ ድጋፍ ከሌለው ውሃ እንዳጣ ችግኝ መድረቁ አይቀርም።
በቅን ልቦና እናስብ ከተባለ ካርል ሄንዝ ከበአሉ ግርማ እና ከአፄ ቴዎድሮስ በፊት ሃውልት እንዲሰራለት መወሰኑ ለኢትዮጵያ ህዝብ ስድብ ነው። ለነገሩ የጥበብ ሰዎቻችን የተረሱ ናቸው። ከበደ ሚካኤል ከፑሽኪንና ከቦድሌር የሚያንሱ አልነበሩም። ጥላሁን ገሰሰና ፀጋዬ ገብረመድህን ሃውልቱ ቢቀር የመንገድ እና የሙዝየም ስም እንኳ ቢሰጣቸው መልካም ነበር።
ወያኔ በነበርኩበት ዘመን፣ “መቱ” የተባለችው ከተማ በበአሉ ግርማ ስም እንድትሰየምና ከሞጆ እስከ ዱከም ያለው መሬት “መዳወላቡ” የተባለ ስም ተሰጥቶት የኦሮሚያ ዋና ከተማ ሆኖ እንዲታወጅ የሚጠቁም አሳብ እፎይታ ጋዜጣ ላይ ፅፌ ነበር። ስለበአሉ ግርማ ሃውልት ማንሳቴ፣ ኩማን በጣም እንዳበሳጨው ትዝ ይለኛል። በስልክ “መነሻህ ምንድነው?” ብሎ ሲጠይቀኝ፣ በአሉ ግርማ ለእውነት ሲል ህይወቱን ስለከፈለ ይገባዋል። መቱን የመረጥኩለት ስለተወለደባት ነው። በአናቱ ደግሞ በአሉ ግርማ ኦሮሞ ነው” አልኩት። የመጨረሻዋ ነጥብ የኩማን ቀልብ ከሳብኩ በሚል የጨመርኳት ነበረች። አልተሳካልኝም። ምክንያቱም የኩማ ጆሮ ከበላይ አካል የሚመጣን አሳብ ብቻ ነው የሚያዳምጠው። ይኸው አሁን ኩማ ለካርል ሄንዝ ሃውልት እንዲተክል ሲታዘዝ በደስታ መቀበሉን ሰማን። ርግጥ ነው፣ህዝቡ ተባብሮ ለበአሉ ግርማ ሃውልት ለመስራት ቢጠይቅ እንኳ፣ አዲሳባ ላይ አደባባይ እንደማይፈቀድ ግልፅ ነው። በአሉ ግርማ ለኤርትራ ህዝብም ውለታ የሰራ እንደመሆኑ፣ አስመራ – ፓራዲዞ የተባለው ሰፈር ላይ ሃውልት እንዲያቆምለት ሻእቢያን በደብዳቤ የመጠየቅ አሳብ አለኝ። ምክንያቱም መቃብሩ ያልታወቀው በአሉ ሃውልት ሊኖረው የግድ ይላል። ወጣቶች የበአሉ ግርማን ሃውልት ሲመለከቱ፣ የመንፈስ ብርታት እንደሚያገኙ ምንም ጥያቄ የለውም። በርግጥም በዚያ በጨለማው ዘመን በአሉ ግርማ ጭል ጭል የምትል የሻማ ብርሃን ነበር። የኤርትራ እና የኢትዮጵያ ጉዳይ ወዴት እያመራ እንደሆነ ማየትና ያየውን መናገር የቻለው፣ ሻእቢያ ገና ናቅፋ ተራራ ላይ ሳለ መሆኑ ሲታሰብ በአሉ ነቢይ ነበር ያሰኛል።
ከ15 አመታት በፊት “እፍታ” በተባሉ የመፃህፍት ቅፆች ላይ ይህንኑ የሃውልት ጉዳይ አንስቼ በጠነከሩ ቃላት መተቸቴን አስታውሳለሁ። ለመጪው ትውልድ አርአያ ሊሆኑ ለሚችሉ ሰዎች ሃውልት ለማቆም የሚወሰነው በምን መለኪያ ነው?
የግጭት ሰበብ መፍጠሪያ ፈንጂ ለመቅበር ካልሆነ በቀር፣ የአቡነ ጳውሎስ ሃውልት አስፈላጊ አልነበረም። ሃውልት የሚተከልለት ሰው አበባ ሲቀመጥለት ነው የምናውቀው። በዚህ ዘመን “በሽብርተኞች” እንዳይመታ ጥበቃ የሚደረግለት ሃውልት ቢኖር የአቡነ ጳውሎስ ሳይሆን አይቀርም። ወደፊት የአቡነ ጳውሎስ ሃውልት መፍረሱ እንደማይቀር ወያኔ ያውቃል። ያን ጊዜ ግን፣ “አቡነ ጳውሎስ ትግሬ ስለሆኑ አማራዎች ሃውልቱን አፈረሱት” በሚል ሊቀሰቅስበት ይሞክር ይሆናል።
እየቆየ የሚፈነዳ ፈንጂ የሚባለው እንግዲህ እንዲህ ያለው ነው። ነገር ፍለጋ ካልሆነ፣ ሰውየው እንዲህ በህዝብ እንደተጠሉ እየታወቀ ሃውልታቸውን አዲሳባ መሃል መትከል ምን አመጣው? የልዩነት ሰበብ እንዲሆን?
በሺህ ዘመን ትውልድ ህያው የሚሆን ታሪክ ሰርተው ያለፉ፣ ሃውልታቸውን የተከሉት በሰው ልጅ መንፈስ ውስጥ ነው። በጎ ተግባር እንጂ ሃውልት ህያው አያደርግም። መለስም ቢሆን፣ በባከነ ሰአት ተጠቅሞ፣ ከእልህ ፖለቲካ ወጥቶ፣ አንድ ጎል ቢያስቆጥር በመትረየስ የማይጠበቅ ሃውልት መገንባት በቻለ ነበር። ለዚህ ግን የታደለ አይመስልም። ከህዝቡ ፍላጎት በተቃራኒው ጎዳና መጓዙን ቀጥሎበታል።
በመጨረሻ በአለም ፀሃይ ወዳጆ አንዲት የምወዳት ግጥም ልሰናበት፣
አክሱም ላሊበላን – የቀየሰ አእምሮ፣
ያነፀው አዋቂ – ዛሬ ቢኖር ኖሮ፣
ይወቀስ ይሰደብ – ይወገዝ ነበረ፣
እንኳን እሱ ሞቶ – ስራው ብቻ ቀረ።
ፀሃፊውን ለማግኘት፡ [email protected]———————————————————————
Hi Tesfaye,
We are living in a time when one oromo is against another oromo,one amhara is against another amhara etc. just to serve the ruling party and their pocket ignoring what the future can bring because of their poor judgement , narrow minded attitude and lack of historical fact.Anyway thank you for inserting some simple logics and facts to their narrow minded world !!
Good bless !!
i don’t agree with your point, i think he has done a lot of things to Ethiopia,and do not politicize everything! and he deserve! but i agree with the point you raise, other Ethiopian also need this kind of recognition such as Kebede Mechael, bealu girma, etc.
የተስፋዬን ችሎታ የማደንቀው እንዴት ኣድርጎ ሰዎችን Mislead እንደሚያደርግ ያውቅበታል፡፡ ወያኔ እስከ ኣሁን ሃዉልት እንዲሰራላችው የፈቀደላቸው ብሎ ዋሽቶ የጠቀሳች ሰዎች ኣሉ- የት ነው የተሰራላቸው ? መቼ ነው የተሰራላቸው ? የሚል ጥያቄ እንደማይቀርብለት ስለሚያውቅ ብቻ ነው፡፡ ለዚህም ማረጋገጫው ከላይ ያሉ ኣንዳንድ ኣስተያየቶች የሱን ዘገባ ኣምነው ስለ ሃዉልቶቹ ኣስተያየት ሰጥተዋል፡፡ ሃቁ ግን ለ ኣፄ ዮሃንስም ይሁን ለራስ ኣሉላ የተሰራ ሃዉልት የለም (ቢገባቸው እንኳን) ፡፡ የ ሃየሎም ኣርኣያ ኣንዲት ሚጥጤ ሃውልት በትውልድ ስፍራው (ገጠር ኣዲ ነብርኢድ ) በኣካባቢው ሰዎች ተሰርታለች (በቤተሰቦቹ ይዞታ ቦታ)፡፡ የ ኣቡነ ጳውሎስ በመንግስት ሳይሆን በራሳቸው በቤተከርስያን ቅጥር ጊቢ ሰዎች ኣሰርተዋል – ትክክል ላይሆን ይችላል፡፡ ከ መንግስት ጋር ግን ምንም ኣይያያዝም፡፡ ተስፋዬ ኣሁን ኣሁን ያለቀበት ይመስላል፡፡ ወያኔን የምንወቅስበት ብዙ ጉዳዮች እያሉ ይሄ ጉዳይ ማንሳቱ በጣም ይገርማል፡፡ ደግሞስ ሚስተር ካርል ሄንዝ የሰሩት ስራ ሃውልትም ሲያንሳቸው ነው፡፡ ለነገሩ መንግስት መንገድ በስማቸው ይሰይማል እንጂ የማንንም ሃውልት ኣሰርቶ ኣያውቅም፡፡ የካርል ሄንዝም ቢሆን የተሰራው እሳቸው ባቋቋሟቸው ድርጅቶች ኣድገው፣ ተምረው ትልቅ ደረጃ በደረሱ ሰዎች ነው፡፡ ሌላው ተስፋዬ በየፅሁፎቹ ታርጌት ያደረጋቸው ትግሬዎችን ይመስላል፡፡ ዘር ከዘር ለማጋጨት ካልሆነ በስተቀር ብእሩ ኣይሰራም እንዴ ? በትክክል የናት ኣገሩ (ኤርትራ) ፀሃፌ ትእዛዝ የሆነ እስኪመስል ድረስ እያስፎገረ ነው፡፡ እባክህን ስለ ራስህ ኣገር ተጨነቅ፡፡ በኛ ጉዳይ ላይ ባትገባ ጥሩ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ለኢትዮጵያውያን፡፡
Karl Heinz deserves a for his genuine humanitarian work in Ethiopia since 1985. You simply are not familiar with his work. In his good deeds he is more Ethiopian than anyone I have known in my life time. There are already 2 Karl Heinz in Ethiopia. The people whom he had helped would probably nominate him for sainthood, if there was such a thing. He has also been nominated for the Nobel Peace Prize few times. DO NOT in any shape or form connect this good man with the dirty, low-down tribalist Woyane psycopath.
Selam Tesfaye,
I have enjoyed your books in the past. I just wanted to say something after reading your recent post on eritreanreview stating your disappointment over the standing of a monument for Karl Henze. But why? Because Meles likes him?
Unless you say the statue of Balu Girma would mean a lot to the Oromo youth (since you are ye Bishoftu lij of Eritrean origin are more qualified for concern) I will bet you a Dollar (or a Euro for Holland or a million Nakfa) that the Oromo youth in Metu , the youth in Harar will surprise you with their pick. Ask your old friend Awraris. Did Balau write any book that an Oromo kid can quote? Sorry for my lack of knowledge on Bealu Girma. I am not that of a book reader per se. The only few books I read and liked are books by Tesfaye Gebreab who is also the only one I know who is influenced by Bealu. Unfortunaly, you don’t seem to choose to live and die in Ethiopia like your mentor. Is it Bealu or Birhanu your mentor? By the way on a different note, why did you have Birhanu review your last book?
I like your thought of writing (from a distance that isJ) to shabia’s government to have Balu’s statue in Asmara. I emphasize the distance, because I don’t want you to get to close and end up in a container-for-life somewhere in Eritrea. While you are at it I might have a suggestion on what else to include in your letter that I thought of more significance.
Tesfaye, I was thinking of a statue for Dr. Catherine Hamlin. You know the one at Addis Ababa Fistula Hospital. She has saved several of my sisters and aunts in Ethiopia who had suffered obstetric fistula. What do think? After Balu’s and Dr. Berihanu’s of course. I hate to call this two in the same breath.
Looking forward to your new book.
Stay well.