ወያኔ ተጨናንቆአል?

ርግጥ ነው ሰሞኑን ወያኔ በጣም ተጨናንቆአል።

ለአመፅ እርሾ ሊሆኑ በሚችሉ ቁጣዎች ተከበዋል። የሶማሊያ ተልእኮ እየከሸፈ ነው። አልሸባብ እያሸመቀ ደጋግሞ አደጋ መጣሉን በመቀጠሉ፣ ከዚህ በላይ ሶማሊያ መቆየት እንደማይችሉ ተረድተው ጓዛቸውን መሸከፍ ይዘዋል። ከኤርትራ ጋር የጀመሩት የጦርነት ድራማ፣ ላይ ላዩን ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ እንደሚያውሉት አለመሆኑ ተባኖበታል። የውስጥ ቀውሱ ተባብሶአል። የመምህራን አመፅ ወዴት እንደሚያመራ አልታወቀም። ቢታፈንም መልኩን ቀይሮ መከሰቱ የማይቀር ነው። የኦርቶዶክስ ቤተክርስትያንን ነባር ቅርሶች የማውደሙ ሴራ አማኙን ህዝብ ያሸማቀቀና ያስደነገጠ ሆኖአል። ገና አልተቋጨም። ከደቡብ ክልል የተፈናቀሉት አማሮች ጉዳይ፣ ሊታፈን ባለመቻሉ ፈንድቶ ወጥቶአል። የኑሮ ውድነቱና የዋጋ ግሽበቱንም ሊቆጣጠሩት አልቻሉም። ሙስናው ጣራ ነክቶአል። ስርቆቱ፣ “ተከተል አለቃህን” የሚል ስያሜ አጊኝቷል። የህወሃት ወገኖች የቅንጦት ህይወት ይሉኝታ አጥቶአል። እና በዙሪያቸው ያለውን የተቆጣ የህዝብ አይን ለማፈን መጨነቃቸውን ማስተዋል ይቻላል። አፈና ግን መፍትሄ ሊሆን አይችልም።

ምርጫው አንድ ብቻ ነው። ከራስ ጋር እና ከእውነታው ጋር መታረቅ!

(“የቅዳሜ ማስታወሻ” እስከ ትናንት ኢትዮጵያ ላይ ይጎበኝ ነበር። ዛሬ ማለዳ ስመለከት ግን “ኢትዮጵያ” በሚለው ስር ምንም አያሳይም። በፌስቡክ በኩል የኢትዮጵያ አንባቢዎቼን ጠይቄ፣ ከዛሬ ማለዳ ጀምሮ የእኔና የአቤ ቶክቻው ብሎጎች መዘጋታቸውን አረጋግጠውልኛል። በርግጥ ደብረፅዮን ብሎግ እያሳደደ መዝጋት ከጀመረ ስራ በዝቶበታል ማለት ነው።)

6 Comments on “ወያኔ ተጨናንቆአል?”

  1. Guys I tried to make a phone text to all my friends in Ethiopia it doesnt work. I tried a number of friends phone but not working.
    Woyane is smelling the smoking gun. Pls in anyway try to help you teacher families, friends and whom you knows teachers to keep up the strike. That will pull the rotten root out to be hit by heat then the tree will be history.

  2. ክቡር ተስማ እሸተ “ስዎቸ ግፉ ግፉ: ግፉ ገና ነው!” ብለው የለ:: ስለሆነም ትቃዋሚዎች ትግሉን መግፋት ብቻ ነው ያለባችው::

  3. የሚስሩት ግፍ እጅግ በዝቶል ሕዝብን ንቀዋታል አዋርድውታል በተራችው ትብያ የሚሆኑበት ጊዚ ሩቅ አይሆነም

  4. ወይ ልጅ ተስፋዬ ገ/አብ የካህን ልጅ ነህ መሰለኝ ምነው ግማሽ ሚሊዮን ሙስሊም ሕብረተሰብ አዲስ አበባን ሲያናውጥ አንተ ጋዜጠኛው መተንፈስ ቀፈፈህ። ነው ወይንስ ይህ የሃይማኖት ወገኝተኛነት ካንሰር አንተምጋ ደርሶዋል? እንደዚያ ከሆነ እንግዲህ በማንኛውም ርእስ ዙርያ የምትፅፈው ፁሑፍ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ኮሶ ኮሶ ይበለው
    ብለን ተራግመናል። ለርግማን ደግሞ አሚን ማለት አትገደድም።

  5. It is too early to the woyanes to face the hardship, the worest is not yet. I hope we will see when they will face court for the masacar of youg Ethiopians.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*