የንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ ሁለት የፖሊስ መኮንኖችንና የወረዳ የወያኔ ስራ ኣስፈጻሚ ተገደሉ። ፖሊስ ወደ ሕዝቡ ሲተኩስ ነበር።

የንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ ሁለት የፖሊስ መኮንኖችንና የወረዳ የወያኔ ስራ ኣስፈጻሚ ተገደሉ። ፖሊስ ወደ ሕዝቡ ሲተኩስ ነበር።
#Ethiopia #AddisAbaba #StateTerrorism #MinilikSalsawi
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) ወያኔ ሕዝቡን ወንጅሎ ከቀየው ለማፈናቀል እና ለማሰር እያደረገ ያለው ሴራ የሰዎች ሕይወት ቀጥፏል፥ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የህዝብን ቤቶች ለማፍረስ እቅድ በተመለከተ የክፍለ ከተማው አስተዳደር ከአካባቢው ህብረተሰብ ጋር ሲወያይ የነበረበትን ስብሰባ ከደህንነት ቢሮ የተላኩ የወያኔ ኣባላት በፈጠሩት ግርግር ሁለት የፖሊስ መኮንኖችን እና በክፍለ ከተማው የወረዳ አንድ ስራ አስፈፃሚ አባል ህይወትን አጠፉ። ፖሊስ ወደ ሕዝቡ ሲተኩስ ነበር።

የደህንነት ኣባላቱ ወንጀሉን ከሰሩ በኋላ በመጡበት መኪና ተሰውረዋል። የደህንነት ሃይሎቹ በፈጠሩት ግርግር ምክንያት የወያኔ መስተዳደር ኣባላት ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን ይህ ሁሉ ችግር ሕዝብን ለመወንጀል የተደረገ መሆኑ የኣከባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ። እስካሁን በኣከባቢው የሞቱ ሰላማዊ ሰዎች ቁጥር ኣልታወቀም። #ምንሊክሳልሳዊ