ሕጋዊው የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሲኖዶስ የጵጵስና መዐረግ ሰጠ

በስደት የሚገኜው የኢትዮጵያ ሲኖድስ በካሊፎርኒያ ግዛት አዲስ ሊቃነ ጳጳሳትን የጵጵስና መዐረግ ሠጠ።

1ኛ. አባ ወልደ ትንሳኤ – የጵጵስና መጠሪያቸው – ብፁዕ አቡነ በርናባስ የካሊፎርኒያ ጳጳስ
2ኛ. 
አባ ጽጌ – የጵጵስና መጠሪያቸው – ብፁዕ አቡነ ቴዎፍሎስ የመንበረ ፓትርያርክ ጽ/ቤት ጳጳስ
3ኛ. አባ ገብረ ሥላሴ – የጵጵስና መጠሪያቸው – ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የአውስትራልያ ጳጳስ
4ኛ. አባ ሳሙኤል ብፁዕ – የጵጵስና መጠሪያቸው – አቡነ ናትናኤል የደቡብ አፍሪካ ጳጳስ
5ኛ. 
አባ ሳሙኤል – የጵጵስና መጠሪያቸው – ብፁዕ አቡነ አብርሃም የኤድመንተን ጳጳስ
6ኛ. 
አባ ገብረ ስላሴ – የጵጵስና መጠሪያቸው – ብፁዕ አቡነ ማርቆስ የኦሪገን ጳጳስ

በቀጣይ 7 ቆሞሳት የተመረጡ ሲሆን 
በኮሎቦስ ኦሃዮ በጥቅምት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ስርአተ ሲመቱ ይፈፀማል::

15 Comments on “ሕጋዊው የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሲኖዶስ የጵጵስና መዐረግ ሰጠ”

  1. Abba Wolde Senebet Adaheno /Abuna Mekatiose / what is his position he is? He is just nomande he is in London.

  2. Amen !!!may God bless their service l am personnaly happy. for Aba Samuel of South Africa and Aba Weldetnsae of California

  3. እምነት አለ እንደ ዛሬ አታምኑም፣አትሰግዲም፣አታስቡም እምነት የለሽ ሁኑ ነው እያሉና እየገደሉን ያሉት!

    ሳላድን

  4. እንኳን ደስ አላችሁ እግዚያብሔር አገልግሎታችሁን ይባርክ

  5. እንደ አባ ወልደተንሳይ ያለ የለየለት መናፍቅ በጵጵስና ማዕረግ በቤተ እግዚአብሔር መመረጥ በእውነት የቤተክርስቲያንን ፈተና መወሳሰብ ያሳያል፡፡ አባቶችን የማጣት እርግማን ደርሶብናል፡፡ ባለቤቱን እግዚአብሔርን ብቻ መመልከት ነው ያለብን፡፡ እግዚአብሔር ቤ/ያንን ይጠብቅልን ይህን የኑፋቄ መንፈስ ከቤ/ያን ነቅሎ በሲኦል ይጣልልን፡፡ አሜን!

  6. መጀመሪያ በራሳችን አይን ውስጥ ያለውን ግንድ እናውጣ በሰው አይን ያለውን ስንጥር ለማውጣት ከመሮጥ ። ለመሆኑ ትንሽ አናፍርም በእውቀት፣በእድሜ፣ወዘተ ከእኛ በላይ የሆኑ አባቶችን ለመዝለፍ ወያኔ ላይ የተመረገ አፋችን ለመክፈት የተነሳነው።ኧረ በፈጠራችሁ ከወያኔ ባሳነሳችሁት ሁሉን በፈጠረ በአንድዪ ልለምናችሁ የተፈቀደልንን ብቻ እናድርግ ሌላውን ለእርሱ እንተወው።

  7. Eneko algebagn yalew. Ye Ethiopia orthodox new ye America orthodox new? Haymanot lela poletica lela. Ezih yalew sinodos ye Ethiopia hizb almeretewm malet and neger new. Yalew sinodos ye weyane selehone new and neger new. America kuch belo meto shih yemaymola “amagn” anja fetero engna nen tekekel malet min aynet neket new? Ezih yalew be million yemikoter amgn sehetet enante lek mehonachihu new? Tekekel yemihonew america lay ende shifta meshego makrarat sayhon ezih metetachehu amagnun yemiwokel sinodos hizb asamenachu asmeretu. Alezia gin engna enawkalen atebelu. America selehonachihu new? Dinkem!!

  8. እግዚአብሔር ይመስገን ለዚህ ያበቃን እሱ የሚሳነው ነገር የለምና አንድ ያድርገን ያብዛን ለአንድነት መፅልይ ይሻላል።

  9. ወይ ጉድ ኦርቶዶክስ መቀለጃ ሆነች።
    የውጭ አባቶች ሁሉም ጰጰስ መሆን አለባቸው ተባለ አፈቸወን የሚያሾሉ ታሐድሶ የኦርጋን እና አርጋኖ አፍቃሪ እና የስድብ መንፈስ ዲያቢሎስ ያጠመቃቸው ከጎንደር ብቻ ተሾሙ።

    የአገር ውስጥ ደግሞ አባ ማትያስ ደግም ከአደዎ ብቻ ጉበኞችን እና ተሐድሶዎችን እየሰበሰቡ ሰሞኑን ሊሾሙ ነው። ለመሾም የህዝቡን ገንዘብ ስብስቦ ጉቦ መስጠት ያስፈልጋል። ውሸት በ እውነት ላይ አንግሻለሁ እያለ ነው ማን ዲያቢሉስ እየሳቀባቸው ነው።
    አቡነ መርቆርዮስ ሆኑ አቡነ ማትያስ ዲያቢሎስ በውሸት ሰንሰለት አስሮአቸዎል። አባካቹ ፀልዪላቸወ!!!
    እናንተ ወገኖቼ ስለ ሐይማኖታቹ ስትሉ ቆም ብለው እግዚአብሔር እንዲረዳቸው ፀልዪላቸው። እውነቱን ይዘው የሞቱ አባቶቻችን አምላክ ይርዳን አይ ክፍ ትውልድ ኢትዮጵያዊ እግዚኦ ማረን ከመጥፈታችን በፈት። ለእዚች አጭር ህይወት ከሥጋ ስም ድሎት አይ ቀልድ በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ስራው ረቂቅ ነው ትዕግሥቱ ሲያልቅ ወላፈኑን ይዞ ይመጣላችሀል። ለራሳችሁ ወየሁ በሉ

  10. Whenever there is spiritual revival and the work of the Holy Spirit is revealed the devil will roar like devouring lion.who cares for the devil except woyane and it’s agents?On the day of the Pentecost and Arch-Angel Michael God have given us additional Apostles like the then Aba Wolde Tensae and the now “Abune Bernabas”

  11. አንተ መቼም የተጠመክ ይመስለኛል ታድያ በሜሮን ከታተመው አፍህ እንዲህ አይነት ርኩሰት፤እንዲህ አይነት ስድብ እንዲህ አይነት ፍርድ እንዲህ አይነት ክፋት እንዴት ወጣ ወይስ ማህተሙን አፈረስከው?አባ ወልደ ትንሣኤን መናፍቅ ያላቸው የትኛው ጉባኤ ነው ወይስ የትኛው ሲኖዶስ ነው፡፡እንደ ዲያብሎስ ለምን ውሸት ትናገራለህ?(ዮሐንስ 8:44)መናፍቃን እኮ ሲወገዙ ጉባኤ ተጠርቶ ስላስተማሩት ኑፋቄ ተጠይቀው አባቶች መጽሐፍ ገልጸው አስተምረዋቸው እምቢ ብለው በኑፋቄ ትምህርታቸው ሲቅጥሉ ተወግዘው ይለያሉ፡፡የነአርዮስ፤የነንስጥሮስ፤የነ መቅድንዮስና የሌሎችም መናፍቃን ውግዘት ከላይ የተጠቀሰውን መንገድ የተከተለና የኦርቶዶክስ አስተምህሮም ነው፡፡ታድያ አንተ የየዋሁን የአቤልን ስም ይዘህ ለምን ወደዚህ ጥላቻና ነፍስ ግድያ ውስጥ ገባህ?ወንድሙን የሚጠላ ነፍሰ ገዳይ ነው ተብሎ ተጽፎአል (1ኛ ዮሐንስ 3:15)ስለዚህ መናፍቅ ያልካቸው አባት ያስተማሩትን ኑፋቄ መጽሐፍ ጠቅሰህ አቅርብ እንጂ በጥላቻ ተነሳስተህ ለቤዛ ቀን የታተምክበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔርን መንፈስ አታሳዝን፡፡አቤል ሆነህ የቃኤልን ስራ አትስራ ተቅበዝባዥ እንዳትሆን፡፡
    እግዚአብሔር ለንስሐ ሕይወት ያብቃን

  12. አባቶቻችን ከሰቀመጡት ትውፈት፣ ቀኖና እና ዶግማ ውጪ የሆነ በራስ ፈልስፈና ተነስቶ ቃላት እየሰነጣጠቁ በኦርጋን ማስጨፈር በአጠቃላይ ከኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ደንብ ውጪ የሚካሄድ ሁሉ ኑፈቄ እና ሕዝባችንን ግራማጋባት ነው። ከስርአት ውጪ ከሆነ ህዝቡ አሁን ስለ ሐይማኖት የነቃ ስለሆነ መሽወድ አይቻልም። እውነት ዛሬም ነገም እውነት ነች ሰለዚህ በአገር ውስጥም ሆነ ውጪ ያላችሁ መስቀሉን ለጌጥ የተሸከማቹ ተመለስ የወላፈን እሳቱ ከእናንተ ከምላሳችሁ ላይ ይጀምራል ባለቀ ሰአት ህዝቡ እየተቀወማቹ ዲያቢሎስ እየተሳለቀባቹ ነው ቆም ብላችሁ ለነፍሳችሁን አድኑ። ስድብ ሁሉ ከዲያቢሎስ ወገን ነው። ሕዝባችን
    ግን ጠልቶአችሁ ሳይሆን ገንዘብን ንዋይ አርጋችሁ በአገር ውስጥ እና ውጭ በተሐድሶ ጎዳና የገባችሁ ተመለሱ እያለን ነው። በክርስቶስ ደም ላይ ቆመን መሾፍ አይቻልም።

  13. ማንኛውም ክህን አለማዊ ትምህርት ቢማረ ቢመራመር ተምሯል ለማገናዘብ ለስጋው ተብሎ ነው የሚነገርለት ግን እንጂ ከላይ እስከ ታች የሉት የቤተ ክርስቲያን ማዕረግ እና እውቀት በሙሉ አባቶቻችን እግር ስር ቁጭ ብለን የተማርናት ትምህርት አይቀየርም። ዶግማ እና ቀኖናውን መቀየርም ሆነ ጥቅስ እየጠቀሱ አሁን የነቃውን የኦርቶዶክስ አማኝን በድጋሚ መሸወድ አይቻልም። ዱሮ ከህኑ ትክክለኛ ስለነበረ እንደዚህ ስተት የምትስሩ ከሆነ አውግዣለሁ ይሉ ነበር። አሁን አሰመሳዪች ሰርፀው በሐይማኖቱ ውስጥ ስለገቡ ቢያወግዝ እንኳን አሰመሳዬቹ ከእነሱ ጋር ዲያቢሎስ እንጂ መንፈስ ቅዱስ ሰለሌላቸው፣ ለማውገዝ ቢሞክሩ እንኳን ማንም አይቀበለም።
    እራሳችሁን ምርምሩ እኛ የእናንተን ሐጥአት ማመላለስ አንፈልግም ቀና ብላችሁ ወደ ፈጣሪያችን ተመልከት። ለማን ማድላት ይበልጣል ለነፍስ ወይስ ለነዋየ ስጋ?
    Watch ከቻላቹ?
    https://youtu.be/SOKcPeAux-M

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*