በኒዘርላንድ ወንጀለኛ በመጥፋቱ 8 ማረሚያ ቤቶች ተዘጉ፡፡

በኒዘርላንድ ወንጀለኛ በመጥፋቱ 8 ማረሚያ ቤቶች ተዘጉ፡፡
ከዚህ ቀደም 19 ማረሚያ ቤቶችን ኒዘርላንድ መዝጋቷ ይታወሳል ፡፡ፆመኛ ማረሚያ ቤት የፈጠረችው ኒዘርላንድ ታድያ ማረሚያ ቤቶቿን ለኪራይ እየተጠየቀች ነው፡፡በተለይም ጎረቤቷ ቤልጂየም እስር ቤት እንድታከራያት ደጅ እየፀናቻት ነው፡፡ኒዘርላንድ ዜጎቿ የደረሱበት የጎነ ማህበራዊ የአስተሳሰብ ልዕልና ከወንጀለኝነት እንደታደገላት ተገልጿል፡፡ከሱስ የራቀ፣ባለ ዓላማ፣ራሱን በራሱ የሚዳኝ ማህበረሰብ በመፍጠርም ዓለምን እየመራች ነው፡- ኒዘርላንድ ፡፡
CCTV

10 Comments on “በኒዘርላንድ ወንጀለኛ በመጥፋቱ 8 ማረሚያ ቤቶች ተዘጉ፡፡”

  1. ቤልጅየም ሳትሆን መማፀን የያዘችው ኢትዮጵያ ናት።ገንዘብ ሳይሆን እስር ቤቱ በነፃ እንዱሰጣት እየለመነች ነው።ይባላል

  2. May be woyane is the first to ask for rent inorder to jail tens of thousands ethiopian prisoners

  3. አውሮፓ እስረቤቶቻቸውን ሲዘጉ በአፍሪካ አህጉር ግን ምን እየሰሩ ነው?
    ጎንታናሞ በኢትዮጵያ፣በሴኔጋል፣በጋና ተከፈተ
    በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው እስርቤት በወሎ፣በጎንደር፣በጅማ፣በወለጋ ይገኛሉ
    የሚፈለገው ይህ አይደለምን!
    በውነቱ

  4. እባካችሁ ተውን! እስቲ ብላችሁ ብላችሁ ኔዘርላንድ እስር ቤት ተመኛችሁልን:: እዚህ ሀገር ከመኖር ኔዘርላንድ ሀገር መመታሰር እንደሚሻል አታችሁት ነው:: በምን እድላችን ኔዘርላንድ ሄደን እንታሰር:: ወያኔ በእርግጥም የኔዘርላንዱን እስር ቤት የሚከራይ ከሆነ የመጀመሪያው አመልካች ነኝ ለመታሰር:: ምነው እውነት ባደረገው:: እዚህ ሀገር የወያኔዎችን ህንጻዎች እያየሁ ከመዋል ኔዘርላንድ ሄጄ ብታሰር እመርጣለሁኝ:: እናንተስ እዚህ ሀገር ያላችሁ ምን ትላላችሁ?

  5. እየበላሁ ልታሰር ካላሉ በቀር እስር ቤት እስርቤት ። ይቅርታ ክኛው ጋር ማወዳደሬ አይደለም ። የኛማ ከነስሙም ወህኒ ቤት ነው። ግን የትም ሆነን በተለይም የፖለቲካ እስረኛ ካለ የትም ይሁን የትም በሆዳምነትና በምቾት አንጻር አንየው።
    ትልቁ ነገር የሚታሰር ሰው በመታጣቱ እስር ቤት ተዘጋ ደስ የሚል ዜና ነው ። ግን መዋዕለ ህጻናትም እየተዘጋ ነው ሰምቻለሁ። የምታውቁ እውነት ይሆን? ከሆነስ ለምን ? በወሊድ ቁጥጥር ምክንያት ወይስ የማይወልዱ እየተጋቡ? ማለቴ መብት ትርጉሙ ጣራ በመድረሱ የሰዶማውያን ጋብቻ በመብዛቱ በናኖ ቴክኖሎጂ ልጅ እስኪያመርቱ የልጅ ድርቅ መታቸው?

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*