የጆቤ በጥናት ላይ የተመሰረተ ምሁራዊ ትንታኔ በወፍ -በረር ሲፈተሽ// Girma Bekele

የጆቤ በጥናት ላይ የተመሰረተ ምሁራዊ ትንታኔ በወፍ -በረር ሲፈተሽ// (በተለይ ለአዲስ አድማስ ከተሰጠው ቃለምልልስ) Girma Bekele

የእኔ ድምዳሜ—ጆቤ እነ ሪፖርተርና አዲስ አድማስ ሊሰብኩን እንደሚሞክሩት፣ እርሳቸውም ሊያሳምኑን እንደሚታትሩት ቅንጣት የፖለቲካ አመለካከትም ሆነ የአቋም ለውጥ አላደረጉም፤ የጽሁፎቹ ዓላማ ህወኃት/ኢህአዴግ ተጠናክሮ እንዲቀጥል፣ በህዝብ የተነሳውን ፖለቲካዊ የለውጥ ትግል ለማዘናጋት አቅጣጫ የማስቀየሪያ ስልት ምክረ ኃሳብ ነው፡፡ መነሻዬ — ጆቤ ጽሁፉን በጥናት ላይ የተመሰረተ ምሁራዊ ትንታኔ ለማስመሰል ያደረጉት ጥረት በግልጽ ይታያል፡፡ግን አልተሳካም፡፡ እንዴት ቢሉ ከሁሉም በአጭሩ ‹‹ …እንግዲህ 25 ዓመት ነው የቆየነው፡፡ በእነዚህ ጊዜያት ውስጥ የሰራዊቱ የብሄር መመጣጠን እየተስተካከለ መጥቷል የሚል ግምት ነው ያለኝ።›› የሚለው የአደባባይ ምስጢር የሆነውን ጥናቱ ያለመመልከቱን ‹‹ ግምት›› በመስጠት ሊሸፍኑ መሞከራቸውን በግልጽ ያሳያል፡፡ ሌላ ዝርዝር ውስጥ መግባት አያስፈልግም፡፡ ምክንያቱም ይህን እንኳንስ ‹ጄ/ል› ጆቤ እኔስ/ማንም በእርግጠኝነት አይናገረውም ? ከ95 % በላይ ጄነራሎች እነማን መሆናቸው ጆቤ ጠፍቶኣቸው ከሆነ ይህን ያሉት /የገመቱት አንባቢ ይፍረድ፡፡ የመነሻና ድምዳሜዬ ማሳያዎች ለዛሬ በጥቂቱ ፡- 1. ጆቤ ለማስተርስ ድግሪ መመረቂያ ጥናት እስከሚያደርጉ በአሰብ ላይ የኢትዮጵያኝ ህጋዊ ባለመብትነት አያውቁም ነበር፣ በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት (በአልጀርሱ ስምምነት ወቅት) ከፍተኛ ወታደራዊ ሃላፊ መሆናቸውንና በዚያን ጊዜ ዛሬ ላይ የተረዱትን ሃቅ የሚናገሩና በሙያቺን እናግዛችሁ ይሉ የነበሩ ኢትዮጵያዊ የህግና ታሪክ ምሁራን እነ ዶ/ር ያዕቆብን የመሳሰሉ ምን እንዳደረጉ፣ ሊያደርጉ ይችሉ እንደነበር ነው ጥያቄው፡፡ ጆቤ የዶ/ር ያዕቆብን ‹አሰብ የማን ናት›› መጽሃፍ ለማስተርስ ጥናት ማጣቀሻ አላነበቡ ይሆን? ያስብላል፡፡ ‹‹አውቆ የተኛን….››፤ 2. ጆቤ በሥልጣን በነበሩበት ዘመን ማንም ሌላ መንግስት አድርጎ የማያውቀውን ‹‹ከራሱ ለተገነጠለ አገር ›› ከሁሉ ቀድሞ ዕውቅና የሰጡበትን እውነት ክደው ፣ዛሬም የህወኃት አቋም መሆኑ በይፋ እየተነገረ ባለበት በኮንፌደረሽንም ሆነ በፌደረሽን አንድ ሊሆኑ የሚችሉበትን ዕድል/ ሊኖረን የነበረውን ግንኙነት ያመከነው ሻዕቢያ ነው ይሉናል፡፡ ‹‹ካፈርኩ አይመልሰኝ›› ፤ 3. የአገር መከላከያ ሠራዊት ዛሬም የሚከተለው የጫካ ጎሬላ ውጊያ ትግል ልምዱን ነው፡፡ እንዲህ ገልጸውታል ‹‹ ከትጥቅ ጊዜ ጀምሮ ያለው ልምድ፣ በክብር የሚያርፉት እዚያው በተሰዉበት አካባቢ ነው፡፡ በየሄዱበት የመቅበር ነገር ነው የነበረው፡፡ ትክክል ይሁን አይሁን ባላውቅም የተሰዉ ወታደሮች ቁጥር መግለፅ ከሞራል አንፃር አስቸጋሪ ነበር የሚል አመለካከት ነበር፡፡ ይሄ ልምድ እስካሁን ዝም ብሎ የቀጠለ ይመስለኛል፡፡ እኔ ግን ትክክል አይመስለኝም። ምክንያቱም የኢትዮጵያ ህዝብ የተከፈለውን ዋጋና የተገኘውን ድል አውቆ ማመዛዘን ይኖርበታል፡፡…›› ሲሉ ሂስ አዘል በሆነ መንፈስ በድርጊቱ የተፈጸመውን ሰብዐዊነትና መንግስታዊ ኃላፊነት የመወጣት ውድቀት ይከላከላሉ፡፡ ‹፣ድመት መንኩሳ…›› 4. ዛሬም በ1997ቱ ምርጫ የዲ/ሲን ግንባታ ቅልበሳ ለህወኃት/ኢህአዴግና ተቃዋሚ ያልተመዘነ (የእኩል) ድርሻ ይሰጣሉ፣ እንዲህ በማለት ‹‹ ግን በቅርቡ እንኳ ያለውን የ10 ዓመት ጊዜ ብናይ፣ 97 ምርጫ ለኛ አንድ ወርቃማ እድል ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ወደ ዲሞክራሲያዊ ጉዞ በከፍተኛ ደረጃ የገባበት አጋጣሚ ነበር፡፡ በገዥው ፓርቲም በተቃዋሚውም በኩል በነበሩ ችግሮች ምክንያት ያ ተኮላሸ፡፡›› ማን ነበር ዋናውን/ወሳኙን የቅልበሳ ሚና የተጫወተው ? ትልቁ ድርሻ የማን ነበር ? የሚለውን ሳይመልሱ በደፈናው ሁለቱንም በእኩል ይከሳሉ፡፡ ‹‹የበላ ዳኛ….›› 5. በአንድ በኩል ከመቼ ጀምሮ እንደሆነ ባይነግሩንም ‹‹ ….ኢህአዴግ ውስጥ መተጋገል የለም፡፡›› ካሉ በኋላ ከዩኒቨርስቲ ‹ኤ› የኢህአዴግ ‹ሲ› ይሻላል በሚል አስተሳሰብ ላይ የቆመ ሲቪል ሰርቪስ መኖሩን አክለውበት፤ በሌላ በኩል ‹‹ በመጀመሪያ ከህግ አኳያ ሲታይ፣ ሜቴክ ወታደራዊ ተቋም አይደለም፡፡ ወታደራዊ መሪዎች ያሉበት የሲቪል ተቋም ነው፡፡ ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ነው፡፡ ስለዚህ ወታደራዊ ተቋም ሳይሆን የራሱ ሰውነት ያለው ተቋም ነው፡፡ ግን በህብረተሰቡ ዘንድ ይህ ግንዛቤ የለም፡፡ አብዛኛው ሰው የመከላከያ ተቋም እንደሆነ ነው የሚያስበው፡፡ ለሰው ሜቴክ ተጠሪነቱ ለመከላከያ ነው የሚመስለው፡፡ በእርግጥ የመከላከያ ታንክና የሜቴክ ገንዘብ ከተጨመረበት በጣም አደጋ ነው የሚሆነው፡፡›› በማለት….. ያልቸገረንን የሜቴክ አደረጃጀት፣ ህጋዊ ሰውነትና ተጠሪነት ነግረውን 100 ከመቶ/100%/ የተመረጠውንና ዲሞክራሲን በላው በማለት የከሰሱትን የምርጫ ውጤት ተከትሎ የተቋቋመ ፓርላማና የሥልጣን ቁልፉ የት ነው በሚባልበት ጊዜ ላይ እያለን እና .ኢህአዴግ ውስጥ መተጋገል የለም፡፡›› ብለው ተነስተው ‹‹ ….ስለዚህ ከፓርላማው ብዙ እንጠብቃለን። ከጠቅላይ ሚኒስቴር ፅ/ቤት ብዙ እንጠብቃለን፡፡ ተጣርቶ ለህዝብ መቅረብ አለበት። ለመሆኑ ፀረ- ሙስና ኮሚሽን ይሄ ሁሉ ሲሆን የት ነበር? ከዚህ ጉዳይ በመነሳት ጠቅላላ ስርአቱንም መገምገም ያስፈልጋል፡፡ ሌሎች ፕሮጀክቶችን ማየት ይጠይቃል፡፡›› ሲሉ ትልቅ ኃላፊነት ይጥሉበታል፡፡ ‹‹የቸገረው እርጉዝ …. ›› 6. ጆቤ ዛሬም ከነበሩበት ኢንች ያለመንቀሳቀሳቸውን ‹‹ ለሕገ መንግስቱ በተሟላ መንገድ መተግበር የአቅሜን ያህል እታገላለሁ፡፡ ምክንያቱም ሕገ – መንግስቱ የአገራችንን ችግር የሚፈታና የሁሉም ሕጐች የበላይ በመሆኑ የማክበርም ግዴታ ስላለብኝ ነው፡፡ በተጨማሪም ከወጣትነቴ ጀምሮ የታገልኩለትን ዓላማ የሚያንፀባርቅና የህዘቦች መስዋእትነት ውጤት ነው፡፡ በተለይም እኔ ስታገልበት የነበረው በህወሓት መሪነት የትግራይ ህዝብ በከፈለው እጅግ ከፍተኛ መስዋእትነት እንዲሁም፣ በተሰውት ጀግኖች፣ (በተደጋጋሚ በተቃጠሉ መንደሮች፣ በአውሮፕላን ድብደባ ወዘተ) የመጣ ውጤት በመሆኑ ሕገ መንግስቱን የማስጠበቅ ጉዳይ እንደሌላው ታጋይ ሞራላዊ ግዴታ አለብኝ ስለምል ነው፡፡››….. ቀጥለውም ለህዝቡ ‹‹ለዚሁም ሁሉም እንቅስቃሴ በሰላም እንዲሆን እና የነሱ ዴሞክራሲያዊ ጥያቄዎች ለግላቸው ለመጠቀም ሁከት የሚጥሩትን ለመንግስት አሰልፎ በመስጠት ጭምር እንደታገሉ ነው፡፡ ›› ህዝቡ መንግስት የሚፈርጃቸውን ከጎኑ ቆሞ እንዲታገል ጥሪ በማቅረብ አረጋግጠዋል፡፡ ‹‹ያደቆነ ሠይጣን…..›› 7. በጽሁፋቸው ሻዕቢያ መወገድ አለበት ፣እንዲያውም የመፍትሄው ሁሉ መጀመሪያ ይህ ነው በማለት የሚከራከሩትና ፖለቲካዊ፣ ወታደራዊና ዲፕሎማሲያዊ የተቀናጀ ትግል ያስፈልጋል ብለው የሚመክሩት ጆቤ፣ ህወኃት/ኢህአዴግ ህገመንግስቱን እንዲያከብርና ተጠናክሮ እንዴት መውጣት እንደሚችል እንጂ ስለፈጸመው የመብት ጥሰትና ህዝቡ ስለሚያነሳው የዲሞክራሲ ጥያቄ ተገቢ፣ ቀጣይና ዘላቂ አስተማማኝ ፍትሃዊ ልማትና ሰላም ለማምጣት ህወኃት ማድረግ ስላለበት በፍጹም አያነሱም፡፡ የችግሩ ቁልፍ ያለበትን እንደማያውቁ ሆነው መንግስትና ኢህአዴግ እያሉ ያደባብሳሉ፡፡.. …፣ (ሌሎችም በርካታ አሉ፣ሁኔታው ታይቶ በክፍል ሁለት ይቀጥላል) ይህ ለምን ያደርጋሉ ብለን ስንጠይቅ የእኔ መላምቶች ፣ በነጠላም ሆነ በተደማማሪነትና በመተመጋጋቢነት፡- 1. ህወኃት ቢወገድ ከተጠያቂነት አላመልጥም በሚል ስጋት ያለውን ዲክታተርሺፕ ማጠናከር የግድ መስሎኣቸው፣ 2. በህወኃት ወታደራዊ አደረጃጀት በመደበኛነት ባይሆንም እንደ ጄ/ል ፃድቃን እንደ አማካሪ ሆነው ለመቀጠል፣ 3. በዋናው የሙስና ዘመን ‹ያባረሩዋቸውን› ወታደራዊ ከፍተኛ ሹማምንት በተለይም ጄ/ል ሳሞራን በህወኃት ውስጥ ቦታ በማሳጣት ለመበቀል፤ ነው፡፡. ከሶስቱ መነሻው የቱም በተናጠልም ሆነ በጥምረት ይሁን እንዲሳኩ ህወኃት/ኢህአዴግ መቀጠል አለበትና ነው፡፡ የዛሬው ማጠቃለያ ‹‹ እኔ ከመጀመሪያውኑ ስታገልላቸው ለነበሩ አላማዎች፣አሁንም በፅናት ቆሜያለሁ ነው የምለው፡፡ ገዥው ፓርቲ ነው ከትግሉ አላማዎች ወደ ኋላ እየተንሸራተተ ያለው፡፡ የ25 ዓመት ጉዟችንን ስናየው፣ ይሄን ልንገመግም እንችላለን፡፡ ›› ያሉትን ወስደን በዚህና ከላይ ባነሳኋቸው ምክንያቶችና የዚህን ምላሽ አይቼ በክፍል 2 የምመለስባቸው ያልተጠቀሱ ምክንያቶች ጥረታቸው በሙሉ ዛሬም ስለጥገናዊ ለውጥ ለመስበክና የህወኃት/ኢህአዴግን አገዛዝ አጠናክረው ስለማስቀጠል ይመክራሉ፣ ይሞክራሉ፡፡ ጆቤ ይምከሩም ይሞክሩም የተነሳው ህዝባዊ የነጻነትና የመብት ጥያቄ ደጋግመን እንዳልነው ከማይቀለበስበት ደረጃ ደርሷልና ምክሩም አይሰራም፣ ሙከራውም አይሳካም፣ ለዘላቂና አስተማማኝ ሰላምና ልማት ፣ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ አያገለግልም፡፡ አዋጪ መፍትሄው– ሁሉን ተጠቃሚ የሚያደርግ አካታች፣ ከጠቅላይና አግላይ ፖለቲካና በኃይል ላይ የተመሰረተ የሥልጣን ሽግግር ወደ ዘላቂና አስተማማኝ ሰላማዊ የሥርዓት ለውጥ መሸጋገር ነው፡፡ በብሄራዊ መግባባት፣ ዕርቅና የሽግግር መንግስት በኩል፡፡ ስለዚህ በዚህና በመሳሰሉት ማሰናከያና ማሳሳቻቻ አቀራረቦች ሳንዘናጋ ከፊታችን ባለው የቤት ሥራ ላይ እናተኩር መልዕክቴ ነው፡፡ ለአገራችንና ህዝቧ የሚበጀውን ያሰማን፣ ያሳስበን፣ ያስተግብረን፡፡ በቸር ያገናኘን፡፡ ሰኔ 12/2008. UNITE.

10 Comments on “የጆቤ በጥናት ላይ የተመሰረተ ምሁራዊ ትንታኔ በወፍ -በረር ሲፈተሽ// Girma Bekele”

  1. U think ur smart but no one can be surprised by ur incompetence since people like u are so shallow and transparent thus Without you telling us, everbody knows who ur, what ur background is, why ur spewing this, what ur dream is. This former decorated General could turn into an Angel tomorrow but as long as he ethnically belongs to the gallantry people of tigray, u ears r clogged and eyes r blinded to see the good in him. The good news is, no matter how much u preach, everbody knows by now that ur hollow minded subhuman who’s beyond cure.
    Elelelele!!!!

  2. If Jobe and others are aware of the importance of port for one independent country after leading Ethiopia for 25 years, anybody can judge them that they were doing everything without any knowledge for 25 years. This is true because any illiterate person doesn’t any advise to make exit/gate for his hut while is building it. Jobe and his group specially “visionary leader” Meles Zenawiw were telling us similarity of port with any commodity in the market. Meles told us repeatedly that port can not be our problem if we have money to pay for it just like we pay money for any commodity.So where were Intellectual Jobe when this issue was the main discussion point of every Ethiopian people? I the big problem of Jobe and his group is that they do not know the knowledge limit of Ethiopian people. Cheating can not be a knowledge to lead a country. It is only helpful to win once or twice like a gambler wins. The methods of gambling planed by “visionary leader” Meles are all expired at this time. That is why Jobe and his groups are standing on the crossway like blind without guide.

  3. Dear our friend Girma Bekele i appreciate your broad minded response for the destorted and twisted poor analysis of the woyanes Abebe Jobbe. What ever he shout the has gone no one can listen his dead propagation. Ato Jobbe enough is enough. Ato we are eager to see in justice house:

  4. በጣም አመሰግናለሁ በዝርዝር የጀኔራሉን ሀሳብ የመሰዘናጊያ ሀሳቦችን በዝርዝር አሳይተኸናል ለመሆኑ የማነው እሱ ቅቤ ጋጋሪ ለመሆኑ መከላከያ ስንት ጀኔራል አለ እነማን ናቸው እስኪ በራሳቸው ተማምነው የሚመሩት; መጥቀስ ይቻላል መከላከያ ሎጀስቲክስ አንድ ኦሮሞ ጀኔራል አለ ይተፋ የሚባል የሚታዘዘው ግን በሌተናል ኮረኔል ትግሬ ነው ያ ወረም ከጥብቅ ክትትል ጋር ይህን ሀቅ የትግሬው ጀኔራል የቢሄር ተዋጦ አለ ሚለን ደሮን ሲያታልሏት በመጫኛ ጣሏት ይባል የለ እኛም እንዳንታለል ጎበዝ

  5. ግርም የሚል ነገር ነው። መቼም ጆቤ ዳር ዳሩን ቢሄዱም ራስን ከተጠያቂነት ነጻ ለማውጣት አሊያም ለወደፊት ለይቅርታ ወይም ለምህረት እንደ አስተዋጽኦ እንዲቆጠርላቸው ያቀረቡት እንጂ ከውስጣቸው ቢሰማቸውም በግልጽ ግን የአቋም ለውጥና ኑዛዜ አላደረጉም። ካፈርኩ አይመልሰኝ ነውና።

    እኔን የሚገርመኝ የጆቤ አይደለም ። የሳቸው ነገር ” ያቦን መገበሪያ የበላ ….” እንደሚባለው ነውና። የመንግስት ነኝ ተብዬው ነው

    በስብሻለሁ ሲለን ከርሞ
    በድያለሁ ሲለን ከርሞና ባጅቶ
    ነቅዣለሁ እያለን ደጋግሞ
    የመልካም አተዳደር ችግር ለሩብ ምዕት አመት ያህል አድርሻለሁ እያለ
    አላግባብ በቢልዮኖች ተሰርቀዋል ና አጓጉል ባክነዋል እያለ
    እየገደለና በዘፈቀደ እያሰረ

    ” እንዲህ ያልኩትን ቀጣፊ ስለወደደኝ መረጠኝ ” እያለ ይቀልድብናል፤ቀልዶም ያስረናል ይገርፈናል ይገለናል።

    እኛ እሱ ያለውን ስንል የነበረውን መሆኑን ረስቶ”፤ የአደሬ ህዝብ ጉዳይ ሲሆን ” ህዝቦች ሁሉ እኩል ናቸው። አደሬዎች ግን የበላይ እኩሎች ናቸው፡፤ ይለናል። ቢሰርቁም ሌሎችን ” እኩል ” ህዝቦች ቢበድሉም ቢገሉም ዝም ይሏቸዋል። ኮንሶ፡ ቅማንት እና ሌሎች ግን ብህገ መንግስት ሰፍሮልናል ብለው መብታቸውን ሲጠይቁ ይገደላሉ ይታሰራሉ ይደበደባሉ የአውሮፓውያንን ይባሪያ ንግድ ብሚያስታውስ መልኩ እርስ በርስ በገመድ ተቆላልፈው ይወሰዳሉ ” የት እንደገቡም እግዜር ይወቀው፡
    በራሳቸውና ባመኑት ንቅዘትና ብልሽት ምክንያት እነርሱ ሄክታሮች አላግባብ ወስደው በስልጣናቸው ተጠቅመው ብዙ ካርታ አውጥተው መሬቱን እንዳሻቸው እየሸጡና እየለወጡ ሲጫወቱበት ፤ እኛ መድረሻ ስናጣና ሲጨንቀን ከነሱም ሆነ ከህጋዊዎቹ የጥንት የጠዋት ባለርስቶች ኩርማን መሬት ገዝተን መጠለያ በንቀልስ” የመሬት ዝርፊያ፡ የከተማውን ፕላን ያበላሽ፡ የመሬት ወረራና ወራሪዎች ” እያለ በዝናብ መጠለያችንን ያፈርስብናል። የትም ተጥለን ስንቀር ዞር ብሎ የሚአየን የለምና ከነ ህጻናቶቻችን የጎዳና ተዳዳሪዎች ሆነናል። ልጆቻችንን ለህጻን ሴትኛ አዳሪነት ዳርጎብናል።

    ስንቱ ተወርቶ ስንቱ ተነግሮ ያልቃል። ግን መርጣችሁኛል ይለናል። እየሰደበን እኮ ነው። ” ዱላና መበደል መደህየትና መታሰር መገደል ስለምትወዱ መረጣችሁኝ እያለን እኮ ነው።

    መቼም የማይቀረው አይቀር። “ዞሮ ዞሮ አህያ የጂብ ነች” ነው የተባለው።

    ወየው ምን ይሻላል?

  6. እባካችሁ እኚህ ጀነራል ዶሮ ብታልም ጥሪዋን እንደሚባለው ተረት ነው አስተያየታቸውን ያስቀመጡት ህወሃት ሲጀመር የትግሪ ነጻ አውጭ እንጂ ኢትዮፒያዊ አለመሆኑ ኢትዮፒያን ወግቶ የመጣ የኢትዮፒያ ጠላት ከትግሪና ከኢርትሪያ የተውጣጡ ባንዳዎች ናቸው::የትግሪን ዘር ነጻ ለማውጣት ለኢርትሪያ ነጻነት የሞትን የሚሉና የትግሪን ነጻነት ለማውጣት ኢትዮፒያን ማጥፋት አለብን ብለው ኢትዮፒያ ቁንጭላይ ተቀምጠው በኢትዮፒያ አንጡራ ሃብት የትግሪን ነጻነትና የትግሪን መንግስት እንመሰርታላን ኢርትሪያም እራሳችንን ስንችል ከኛጋ ትጠቃለላለች ኢርትሪያ ለዘላቂ ነጻነታ ህወሃት የሚያደርገውን የትግሪዎች ጠላቶች ኢትዮፒያዊያኑን ማለትም አምሃራውን ,ኦሮሞውን,ጋቢላውን, ደቡቡን አጥፍቶ እስከሚያረጋግጥ ኢትዮፒያ የምትባል አገር አጠገባችን እንዳትኖር አድርገን እስክናረጋግጥ የትግሪን ነጻነት ማምጣት ማለት የኢርትሪያም ነጻነት ስለሆነ እኛ በምንለው ኢርትራዊያኑ መኖር አለባቸው ኢሳያስ ኢርትሪያን እንዲገዛ ያበቃነው እኛ ነን እንጂ በኢርትሪያ መወሰን የለበትም የትግሪ ዘር ጠላቶቻችንን ኢርትራውስጥ ማስገባት የለበትም ስለዚህ ኢሳያስ የሚያደርገው የኢትዮፒያ ነጻ አውጭዎችን እርዳታ የኢርትሪያም የትግሪም ህልውና ነጻነት የሚጻረር ስለሆነ ይህ ደግሞ የህልውናችን ጉዳይ ስለሆነ አርፎ መቀመጥ አለበት አለበለዚያ የኢትዮፒያን ህዝብ እኛ ወደቡ ለኢርትሪያ ይገባታል ያልነው ኢርትሪያ የራሳችን ስለሆነች እንጂ ኢትዮፒያዊያኑን ኢርትሪያን ማስመለስ አለብን ካልነው ይነሳባችሃል አይነት ነው ስለዚህ ህወሃት የትግሪ ባንዳ ኢርትሪያን ኢትዮፒያን በዘር ከፋፍዪ አምሃራና ኦሮሞ እንዲሁም ሊሎቹንም እንካን በኢትዮፒያዊነት በዘራቸውም እንዳይቆሙ አድርጊ ለትግሪ ዘር ነጻነት እየሰራሁ ስላለው ግዚ ስለሚያስፈልገኝ ኢርትሪያኑ ምንም አይነት ነገር ከሊላው ኢትዮፒያኖች ጋራ ግንኙነት ማድረግ የለባቸውም በሚል ህወሃት ኢርትሪያ የኛነች አይነት ነው ::ለ ኢሳያስ እና ኢርትራዊ ለሆነው ህዝብ ማስጠንቀቂያ የሚሰጠው:: ህወሃት በዚህ ምክንያት ኢትዮፒያን ዘርፎ ለመግደል አምሃራና ኦሮሞ ውስጥ የአምሃራ አሰፋፈር ኢትዮፒያዊነት ህገወጥ ነው ሲል ኦሮሞውን የኦሮሞ አሰፋፈር ትክክል ስለሆነ አምሃራ ወሮህ ክርስቲያን እያለ ጨፍጭፎህ ነው በሚል የፖለቲካ ቁማር ሁለቱ ህዝቦች እኒ ሠፍር አንተ የለህም አንተ ስትሰፍር እኒም አለው ብለው የታሪክ ቀውስ አንስተው ሲጨቃጨቁ የተቀሩትም ኢትዮፒያኖች የማንነት ጥያቂ ስለሚናጋ በታክቲክ እና በስትራቲጂ የኦሮሞ ክልል ያማራ ክልል በማለት እያጭበረበረ አንዱን ወዶ አንዱን ጠልቶ በሚመስል ሁኒታ ኢትዮፒያኑን ከፋፍሎ እያጠፋ እንደያዘው ኢርትራዊያኑንም ህወሃት በአሁኑ ግዚ ከኢሳያስ ጋር ባለው ግጭት የኢሳያስ እና የህወሃት ደጋፊ አድርጎ ከፋፍላል ምክንያቱም ኢርትራዊያኑ ህወሃት የኢርትሪያን ነጻነት ያጸደቀ አንድ ነን የሚሉና እንደ ህወሃት ኢርትራዊ ሆነው ኢትዮፒያውስጥ ለመጠቀም የሚፈልጉ ህወሃትን ዲሞክራሲ ነው ይላሉ የኢትዮፒያ ነጻነት ፈላጊዎች የኢርትሪያን መንግስት የተጠጉት አስብን እንመልሳለን የሚሉ የኢርትሪያን ነጻነት የማይቀበሉ ናቸው ኢሳያስ መንግስት ከኢትዮፒያ ይሻላል ብለው ህዝባችንን እያሰደደ ምንም ችግር እንደሊለ ያሞግሳሉ እያሉሉ ሲከሱ ነበር አሁን በምን ምክንያት ነው እኚህ ጀነራል ለኢትዮፒያ አስበው ወደብ የኢትዮፒያነው የሚሉት ኢርትራዊያኑን እኮ ህወሃት የያዘው ወደብ የኢርትሪያ ነው በማለት የኢርትሪያ ብቻኛ ተቆርቃሪ ትግሪ እንጂ ሊላው ጠላት ነው ሲሉ አልነበር ? ሊላው የህወሃት ደጋፊዎች ኢርትራዊያኖች ኢሳያስ አሰደደን በማለት ይከሳሉ ለመሆኑ ነጻነት ፈልጋችሁ በኢርትራዊነት ከኢትዮፒያ የተገነጠላችሁት ህወሃት የረዳቹ ኢርትሪያ የኢርትራዊያን ብቻ እንድትሆን ስንቱን ኢትዮፒያዊ ያለንብረት እራቁቱን ወደ ኢትዮፒያ ሰዳችሃል እንካን ኢትዮፒያዊያኑን ኢርትራዊያን ከአምሃራ የወለደች በሚል ስም ከኦሮሞም ሆነ ከሊላው ኢትዮፒያዊ የወለደች እናት አሽቀንጥራችሁ የዘር ማጥፋት በህወሃት ተባባሪነት አስፈጽማችሃል ኢሳያስ ኢርትሪያ ለኢርትሪያ ብሎ ነጻ ሲያወጣችሁ ኢትዮፒያን አሸነፍን ያላችሁ ጀግኖች ለምን ዲሞክራሲ ስረአት ለማምጣት ታዲያ እንዳትሰደዱ ምክንያት ከሆነ ማድረግ ምን አቃታችሁ ? ህወሃት ለኢትዮፒያ ህዝብ ጠላት መሆኑን እናተ አይደላችሁም የምትነግሩን የኢትዮፒያ ህዝብ ነጻነቱን በህወሃት ሲነጠቅ የኢርትሪያ ህዝብ ነጻነቱን በህውሃት አገኘ እያላችሁ እኮ የምትመሰክሩ ነበራችሁ:: መለስ ከኢሳያስ ጋር ሲጣላነው ኢርትሪያኑን ይውጡ ያለው እንጂ አገርማ ነጻነትማ በኢሳያስ ይዛችሁ ሊላውን ስታባርሩ አልነበር ? ህወሃት የውጭ ሃይሎችን ወደራሱ ለመሳብ ከኢርትሪያጋ እንደተጣላ አስመስሎ ህዝብ አስጨርሶ የፖለቲካ ቁማሩን ከተጫወተ በሃላ ኢርትራዊያኑን ኑና ንብረታችሁን ውሰዱ በማለት እንደገና መልሶ ስለሰጣችሁ የሰው ህይወት ሳይሆን እናተ የጥቅም ሰዎች በመሆናችሁ ህወሃትን ከ ኢሳያስ ጋራ ስታወዳድሩ አታፍሩም ? የኢትዮፒያ ህዝብ ነቂ ብላል አምሃራ ኦሮሞ እየተባለ የተከፋፈለበት ምክንያት ለማ ጥቅም እንደሆነ ባትነግሩትም የኢትዮፒያ ህዝብ አውቆታል ኢትዮፒያኖች የምንፈልገው እንደናተ ዲሞክራሲ ብቻ ሳይሆን ከዲሞክራሲ ያለፈ የአገር ጉዳይ ነው አገር ነው ኢትዮፒያ ለኢትዮፒያኖች እንድትሆን ነው ያለፉ የኢትዮፒያ ስራቶች ኢትዮፒያዊያኖች ነበሩ ዲክታተሮች ቢሆኑም እየሰሩ የነበረው የኢትዮፒያን ህዝቦች ህልውና ለማስጠበቅ እንጂ በዘር ከፋፍለው ኢትዮፒያን ለማጥፋት ለዘሮቻቸው ነጻነትና አገር እንመሰርታለን አላሉም የኢትዮፒያ ህዝቦች እንደየታሪካቸው ሰፍረው እንዳሉበት እንደተገኙበት ኢትዮፒያዊነታቸውን ለማጠናከር ከባእድጋር የሚሰሩትን ስራ ለኢትዮፒያ ህውና ነው የተጠቀሙት :: ኢትዮፒያ ኢትዮፒያን ወግቶ የመጣ የባንዳ ህወሃት ከኢርትሪያና ከትግሪ የተውጣጡ ጠላቶቻ ቁንጮአችን ላይ በኢትዮፒያ ስም ተቀምጠው የትግሪን ህዝብ ነጻነት ለማምጣት ኢትዮፒያን ማጥፋት በሚል ስም የተቀመጡ እንጂ እንደ ኢርትሪያኑ ኢርትሪያ ለኢርትሪዊያን ብሎ የሚል ኢሳያስን የመሰለ መንግስት የላትም ዲሞክራሲና አገር የተለያዩ ናቸው የናተና የኢትዮፒያኖች ማወዳደር እናታ ገበያ የሂደችባት እና የሞተችባት እኩል ያለቅሳሉ አይነት ነው ኢርትራዊያኑ እናታቸውን ይዘው ነው የሚያለቅሱት ኢትዮፒያኑ እውነተኛ እናታቸው እየሞተችባቸው አገራቸው እየጠፋች ስለሆነ ልዩነቱ እዚህ ላይ ነው:: ስለዚህ የኢትዮፒያ ህዝብ የኢርትሪያ ጠላት አይደለም ኢርትሪያም የኢትዮፒያ ጠላት አይደለችም የኢትዮፒያኖች ጠላት ህወሃት ነው ኢትዮፒያን እያተራመሰ የሚዘርፈውን ግዚ ለማራዘም ሲፈልግ ኢርትራዊያኑን ያተራምሳል ይህ ደግሞ ለውጭ ሃይሎች የሚደረግ ጨዋታ ነው ትናት በባድሚ ዛሪ ደርሞ በጾረና ገና ደግሞ በወደብ በማለት ኢርትራዊያኑን ህወሃት ያስረከበውን እንደ ህጻን ልጅ የሰጠሁሽን አምጭ አይነት ፖለቲካ ምን ያነት ሃላቀር ባንዳ ዎች መሆናቸውን ነው የሚያሳየው ህወሃት የውጭ ሃይሉ እንደ አሚሪካ እንግሊዝ …የመሳሰሉት ከኢሳያስ ጋር ግንኙነት እንዳይፈጥሩ እኒ አሁንም ትልቃን አገር ኢትዮፒያን ስለያዝኩኝ ግንኙነታችሁ ከኒጋ ብቻ ከሆነ የምትፈልጉትን አደርጋለው ዋናው ኢትዮፒያን ለማጥፋት የትግሪን ነጻነት ለማስከበር በኢትዮፒያ ስም እርዳታችሁ ለህወሃት ይሁን ነው:: ኢርትሪያ ትንሽ አገር ስለሆነች ከኢርትሪያ ምንም አታገኙም እኛ አምሃራውን ,ኦሮሞውን, ጋቢላውን…..ለ ቲሮስሪስት መከላከያ ሰተን የትግሪን ህዝብ ጠላት የምናጠፋበት አንዱ ሲስተማችን ነው ኢትዮፒያም ትልቅ አገር ስለሆነች የትግሪን ግዛት እያሰፋን ሊላውን እንሸቅልላችሁ አለን በሚል ኢትዮፒያን በተለያየ ታክቲክ ከፋፍለው በውስጥ በዘር ፖለቲካ ልዩነት እንደሚጠቀሙበት አንዱ መጠቀሚያ ምንጫቸው የውጭ ሃይሎችን ማባበያ በዋነኛነት ኢትዮፒያ ነች ስለዚህ ህወሃት ማለት በዘርፈ ብዙ ታክቲክ የኢትዮፒያ ጠላት አምሃራና ኦርቶዶክስ ብሎ የመጣበት ዋናው እስትራቲጂ የትግሪን ህዝብ ነጻነት እና አገር ለማስረከብ ኢትዮፒያ የምትባል አገር አጠገባችን መኖር የለባትም በሚል ጽኑ እምነት በፋሺስት ሲስተም ግዚውን እያራዘመ ኢትዮፒያ ላይ ለመቀመጥ የሚያደርገው እስትራቲጂ ነው እንደሰማነው ከሆነ አሚሪካም ሆነች ሊላው ሃያላን አገር ሁለት ጎረቢት አገሮች ከተጣሉ በህጉ መሰረት ከአንዱጋ እንጂ ከሁለቱም ጋር መስራት አይችልም ስለዚህ ህወሃት ከኢርትራዊያኑጋር የውጭ ሃይሎች እንዳይሰሩ በየግዚው ግጭት በመፍጠር ትልቃን አገር እኒ ስለያዝኩኝ ጥቅም ያለው ከኒጋነው በሚል ኢትዮፒያን ይዞ በውጭ ሃይሎች ተጠቅሞ ለትግሪ ህልውና ነጻነት የትግሪ ነጻ አውጭ ሆኖ እየሰራበት ነው ለዚህ ነው ህወሃት ለህልውናችን ስንል የውጭውንም የውስጡንም ፖለቲካ ቀይረነዋል የሚለው የሚሉ አስተያየቶች አሉ ለዚህም ነው ኢትዮፒያዊያን በኢትዮፒያዊነት እንዳይደራጁ ትልቅ ጠላቲ ብሎ የሚፈርጀው በዘር ማንነት ደግሞ ዋናውን ስለያዝኩኝ ምንም አያመጡም ስለሚል የማይቆጣጠረው የዘር ልሂቃን እንዲነሳ አይፈልግም ግን ወደፊት ለመገንጠል የትግሪን ነጻነት አመጣለው ብሎ በአላማው ስላለ የዘር ልሂቃኑን እየፐወዘ መጠቀም እንደሚፈልግ እና በአገር ውስጥ ላለው ፖለቲካ ግዚ ማራዘሚያው ናቸው:: ሞት ለትግሪ ህወሃት ለኢትዮፒያ ጠላት!!!

  7. ግርማ በቀለ ስለሰጡት አስተያየት ጥቂት ማለት ቢያስፈልግ፤
    አንድ ሰው መቼስ ሁሌ እንደተሳሳተ መኖር ያለበት አይመስልኝም፣ ከነበረበት ሁኔታ በተለያየ መንገድ ሲባንን እንኳን ወደ ጤነነትህ መለሰህ ተብሎ ነው መበረታታት ያለበት እንጅ፣ አይ፦ ቀድሞ እንደዚህ ነበርክ፣ ያኔ የት ነበርክ፣ ወዘተ ጥያቄዎችን እያዥጎደጎድን መልሰን ወደነበርክበት አዘቅት ተመለስ ማለቱ፣ አግባብ ያለው መስሎ አልተሰማኝም።
    ምናለበት የገዥው አመራሮች እንደ ጄኔራል ጆቤ (አበበ) ድፍረት አግኝተው ለመወያየት ቢመጡ፦ ይህን ባለማድረጋቸውና የሙግታቸውን ጭብጥ አውጥተው መከራከር ስላቃታቸው መሰለኝ፣ ከነርሱ የተለየውን ሁሉ እንደ ጠላት እየፈረጁ ወኅኒ እየወረወሯቸው ያሉት።
    ችግሩ መስሎ የሚሰማኝ ያለው፣ ጆቤ ለምን እንደሌሎቻችን ተቃዉሞኣቸውን ሲያቀርቡ አልታሰሩም ይመስለኛል።
    እንደዚህ ገልጠህ በመውጣት ሃሳባቸውን ለሚገልጹ ሰዎች፣ አይዞአችሁ በርቱ ነው መባል የሚገባቸው። እንጅ ጠላትን እያበዛህ መሄድና ከዚያኛው ጎራም ወደራስህ ለመሳብ ጥረት ያለማድረግ ጥሩና ብስለት ያለው ፖለቲከኛ አያደርግም። አንድ ወታደራዊ መሪ፣ ከዉጊያው ባሻገር ከጠላት ወገን በተቻለ መጠን እጁን እንዲሰጥ ለማድረግ፣ ወይም የመሹለኪያ በር ከፍቶ ጉዳትን በመቀነስ ድል የሚያደርግበትን ዘዴ ይፈጥራል እንጅ በውጊያው ውስጥ ያለውን ወታደር ካልገደልኩኝ አይልም። ታክቲክ መሆኗ ነው መሰለኝ ደግሞ፣ ጄኔራል ሳሞራን ከጆቤ ጋር ለማጋጨት የተጠቀሙባት ፈገግ አድርጋኛለች። ምክንያቱም ከግርማ በቀለ አሳቢነት በመነሳት ሳሞራ ከረጅም ጊዜ የትግል ጓዳቸው ጋር ይጣሉ መስሎዎት ከሆነ በጣም ተሳስተዋል። ከሁኔታዎ እንደተረዳሁት ከሆነም የብአዴን ድጋፍ ያለዎትና የቀድሞዎቹ የህወሓት ባለስልጣኖች እንዳይመለሱና ፓርቲው እንዳይጠናከር ከሚፈልጉት ይመስላሉ እንጅ ለኢትዮጵያችን መፍት ሄ እየሰሩ እንዳልሆነ ጽሁፍዎ ያሳብቅብዎታል።
    ህወሓት ደግሞ እያንዳንዷን አካሄድ መርምሮ የትኛው ነው ለኔ አሳቢው እና ቅርብ ብሎ በሚዛኑ ሲመዝነው፣ የርስዎን ሃሳብ ያዛኝ ቅቤ አንጓች ሊያደርገው ይችል እንደሁ እንጅ፣ በርስዎ ሚጢጢ ተንኮል የሚጠመዘዝ አይሆንም። ያሉት ጥርጣሬ ማለትም የቀድሞዎቹን አመራሮች ለመመለስ የጎንዮሽ ጥረት እንዳለ ምንም አያጠራጥርም ልክ ከየትኛውም የፖለቲካ ድርጅቶች ያሉ ሰዎችን እንደሚያነጋግሩት ማለት ነው። ስለዚህ ውጤቱ ገና ሳይሳካ ለማሰናከል ከሆነ የፈለጉት፣ ወደፊት እናየዋለን።
    ስለዚህ እንደዚህ የሚመጡትን ወገኖች እያበረታታን ሌሎችንም መሳብ ያስፈልጋል ባይ ነኝ። የአለቃ ገብረሃና ጽሁፍ እስኪመስል ድረስ ግን የእንቆቅልሽና የምሳሌ ድርደራው ጽሁፍን ለማሳመር ካልሆነ በስተቀር፣ ትችትን በሚገባ መልኩ አይገልጹም። ጆቤ ራሳቸው ለሰጧቸው ትንተናዎች እንኳን ሃሳብን በሃሳብ የሚረታ ጽሁፍ ሆኖ አላገኘሁትም። ምናልባት ዋናውን ቃለ ምልልስ መረጃ ዳት ኮም፣ ቆራርጦ አቅርቦት ከሆነ አላውቅም።
    ጥላቻ የትም አያደርስም።

  8. @ Bezbiz,

    you are a retarded tigre extremist tribalist subhuman who has the mind of a 13 years old kid at the age of 60.

  9. Subhuman Bezbiz,

    you sound mad in your comment above, is the piece below why you are mad ?

    ” የእኔ ድምዳሜ—ጆቤ እነ ሪፖርተርና አዲስ አድማስ ሊሰብኩን እንደሚሞክሩት፣ እርሳቸውም ሊያሳምኑን እንደሚታትሩት ቅንጣት የፖለቲካ አመለካከትም ሆነ የአቋም ለውጥ አላደረጉም፤ የጽሁፎቹ ዓላማ ህወኃት/ኢህአዴግ ተጠናክሮ እንዲቀጥል፣ በህዝብ የተነሳውን ፖለቲካዊ የለውጥ ትግል ለማዘናጋት አቅጣጫ የማስቀየሪያ ስልት ምክረ ኃሳብ ነው፡፡ መነሻዬ — ጆቤ ጽሁፉን በጥናት ላይ የተመሰረተ ምሁራዊ ትንታኔ ለማስመሰል ያደረጉት ጥረት በግልጽ ይታያል፡፡ግን አልተሳካም፡፡ እንዴት ቢሉ ከሁሉም በአጭሩ ‹‹ …እንግዲህ 25 ዓመት ነው የቆየነው፡፡ በእነዚህ ጊዜያት ውስጥ የሰራዊቱ የብሄር መመጣጠን እየተስተካከለ መጥቷል የሚል ግምት ነው ያለኝ።›› የሚለው የአደባባይ ምስጢር የሆነውን ጥናቱ ያለመመልከቱን ‹‹ ግምት›› በመስጠት ሊሸፍኑ መሞከራቸውን በግልጽ ያሳያል፡፡ ሌላ ዝርዝር ውስጥ መግባት አያስፈልግም፡፡ ምክንያቱም ይህን እንኳንስ ‹ጄ/ል› ጆቤ እኔስ/ማንም በእርግጠኝነት አይናገረውም ? ከ95 % በላይ ጄነራሎች እነማን መሆናቸው ጆቤ ጠፍቶኣቸው ከሆነ ይህን ያሉት /የገመቱት አንባቢ ይፍረድ፡፡ “

  10. @ melkam,

    this is wise: ” ግርማ በቀለ ስለሰጡት አስተያየት ጥቂት ማለት ቢያስፈልግ፤
    አንድ ሰው መቼስ ሁሌ እንደተሳሳተ መኖር ያለበት አይመስልኝም፣ ከነበረበት ሁኔታ በተለያየ መንገድ ሲባንን እንኳን ወደ ጤነነትህ መለሰህ ተብሎ ነው መበረታታት ያለበት እንጅ፣ አይ፦ ቀድሞ እንደዚህ ነበርክ፣ ያኔ የት ነበርክ፣ ወዘተ ጥያቄዎችን እያዥጎደጎድን መልሰን ወደነበርክበት አዘቅት ተመለስ ማለቱ፣ አግባብ ያለው መስሎ አልተሰማኝም።
    ምናለበት የገዥው አመራሮች እንደ ጄኔራል ጆቤ (አበበ) ድፍረት አግኝተው ለመወያየት ቢመጡ፦ ይህን ባለማድረጋቸውና የሙግታቸውን ጭብጥ አውጥተው መከራከር ስላቃታቸው መሰለኝ፣ ከነርሱ የተለየውን ሁሉ እንደ ጠላት እየፈረጁ ወኅኒ እየወረወሯቸው ያሉት።
    ችግሩ መስሎ የሚሰማኝ ያለው፣ ጆቤ ለምን እንደሌሎቻችን ተቃዉሞኣቸውን ሲያቀርቡ አልታሰሩም ይመስለኛል። ”

    In general we should encourage and welcome the likes of Jobe (TPLF “generals”) to come and criticize the TPLF regime.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*